Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Electric Utility

የሰርጥ አድራሻ: @eeuethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.33K
የሰርጥ መግለጫ

EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 36

2022-10-06 15:04:21
3.3K views12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 09:00:07 የኢቲዮ-ቴሌኮም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የኤሌክትሪክ ማሰራጫ መቆጣጠሪያ ማዕከልን ጎበኙ
**************************
የስራ ኃላፊዎቹ ጉብኝቱን ያካሄዱት የሃገሪቱን የኤሌክትሪክ የኃይል ስርጭት መቆጣጠሪያ ጣቢያ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማን የኃይል ማሰራጫ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ ነው፡፡

የኮርፖሬት ዲስትሪቢውሽን ቴክኒካል ሰፖርት ኃላፊ የሆኑት አቶ ጥላሁን ለገሰ እና የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የዲስትሪቡሽን ኮንትሮል ሴንተር ስራ አስኪያጅ አቶ ባሳዝነዉ መኮንን ለጎብኝዎች ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡

የከፍተኛ የስራ ኃላፊዎቹ የጉብኝት አላማ በቀጣይ የሁለቱን ተቋማት አገልግሎት በተሻለ መልኩ ለህዝቡ ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግና የሁለትዮሽ የትብብር መስኮችን በመለየት በጋራ ለመስራት ነዉ፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.4K views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 09:00:04
2.3K views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 12:04:46 የማዕከላዊ እቃ ግምጃ ቤቱ ንብረት አያያዝ እየተሻሻለ መምጣቱ ተገለፀ
*****************
ላለፉት ስድሳ ዓመታት ሲያገለግል የቆየው የጎፋ ማዕከላዊ እቃ ግምጃ ቤት የንብረት አያያዝ በአሁኑ ወቅት ለውጥ ማሳየቱን የሎጅስቲክስና ዌርሃውስ ኃላፊ ቢኒያም ገ/እግዚአብሔር ገልፀዋል፡፡

አዲስ የሚገቡና የነበሩ፣ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ፣የአገልግሎት ዘመናቸው ያለፈባቸው፣ እና ጥቅም ላይ ውለው ተመላሸ የሆኑ ንብረቶችን ለይቶ በማስቀመጥ የንብረት አያያዙን ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን መቀነስ ተችሏል ብለዋል፡፡

በተቋሙ የግዢ፣ ሎጅስቲክስ፣ ንብረትና ፋሲሊቲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ደንድር በበኩላቸው ከዚህ ቀደም ይስተዋሉ የነበሩ በእቃ ግምጃ ቤት የሚቀመጡ ዝቅተኛ መጠን ያላቸው መጠባበቂያ ግብዓቶች አያያዝ ክፍተቶችን በማረምና የክትትል ስራዎችን በስፋት በመስራት ማሻሻል እንደተቻለ ገልፀዋል፡፡

በግምጃ ቤቱ አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን በማስወገድ፣ ጠቃሚዎቹንም በስርዓት በመደርደር፣ ቅጥሩን በማፅዳት፣ የተለያየ ስፋት ያላቸው መጋዘኖችን በመገንባት ከመጋዘን እጥረትና ከአቀማመጥ ችግር ጋር ተያይዞ የሚፈጠር የንብረት ብክነትን መከላከል መቻሉን አቶ ኢሳያስ ጨምረው አብራርተዋል፡፡

የንብረት ስርጭትን በተመለከተ ክልሎች በራስ አቅም ግብዓት የመግዛት ስልጣን ያላቸው መሆኑን የገለፁት አቶ ቢኒያም፤ከጎፋ ማዕከላዊ እቃ ግምጃ ቤት ለሚሰራጩ ንብረቶች እንደተቋም ተግባራዊ በተደረገው የኢ.አር.ፒ የአሰራር ስርዓት መሠረት ስርጭቱ በግልፅ እየተፈፀመ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ይህም በግምጃ ቤቱ ያሉ ንብረቶችን እና ወጪና ገቢን በቀላሉ ለመቆጣጠር ያስቻለ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም በነበረው የወረቀት አሰራር የሚመጣ የሰነድና የመረጃ መጥፋትን አስቀርቷል ብለዋል፡፡

ተቋሙ የማይጠቀምባቸው ንብረቶች በእርዳታ ወይም በሽያጭ እየተወገዱ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው፤ ባለፈው በጀት ዓመት በክልሎችና በኮርፖሬት ደረጃ ከተደረገ የንብረት ማስወገድ በአጠቃላይ 1 መቶ 11 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ገቢ ተገኝቷል ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ቢኒያም ገለፃ በአይነት ከ15 ሺህ በላይ ንብረቶችን በግምጃ ቤቱ የሚገኙ ሲሆን፤ ከነዚህ ውስጥ አገልግሎት መስጠት የሚችሉት ወደ 3 ሺህ የሚጠጉ ብቻ ናቸው፡፡

በመሆኑም የ2015 በጀት ዓመት አገልግሎት የማይሰጡ የተጠራቀሙ ንብረቶች ተወግደው የሚያልቁበት የመጨረሻ ዓመት ይሆናል ሲሉ አያይዘው ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የንብረት ደህንነትን ከማስጠበቅ አንፃር በቅጥሩ ከሚገኙ 24 የጥበቃ ማማዎች በተጨማሪ በቅጥር ግቢው የተገጠሙ የደህንነት ካሜራዎች ስርቆትን አስቀድሞ ለመከላከልና ድርጊቱ ከተፈፀመ በኃላም ወንጀለኛውን ተጠያቂ ለማድረግ ጉልህ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተቋሙን ንብረት በኃላፊነት እንዲጠብቅ አቶ ቢኒያም አሳስበዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.0K viewsedited  09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 12:04:28
1.8K views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 12:03:03 በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የምትገኙ ደበኞቻችን በሙሉ
************
የተቋማችን 905 ነጻ የጥሪ ማዕከል ባጋጠመው ድንገተኛ የቴክኒክ ችግር ምክንያት አገልግሎት መስጠት ማቆሙ እየገለፅን የተፈጠረው የቴክኒክ ችግር ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ክቡራን ደበኞቻችን የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ በትግዕስት እንድትጠባበቁና ከሃይል መቆራረጥ፣ ከፍጆታ ሂሳብ ክፍያ እና ሌሎች ተመሳሳይ ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር የተያያዙ ችግሮች ካጋጠማችሁ በአቅርቢያችሁ ወደ ሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በአካል በመሄድ ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.9K views09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 12:02:59
2.0K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 17:19:04 ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
***
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኮተቤ ጋራዥ ውስጥ የሚገኙ አልሙንየሞችን እና ቁርጥራጭ ብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፤ስለሆነም የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በመገኘት እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
1.5K views14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 17:18:03
1.4K views14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 16:16:06 የኤሌክትሪክ ኃይል ብክነትና መንስዔዎቹ
************
የኤሌክትሪክ ኃይል ብክነት ማለት እየተጠቀምን ባለነው የኃይል መጠን እና በትክክል ለማምረት የሚያስፈልገን ኃይል መካከል ያለው ልዩነት ወይም አንድ ምርት ለማምረት ከሚያስችለን በላይ ኢነርጂ መጠቀም ማለት ነው፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይል ከኃይል ማመንጫ እስከ ደንበኛው ድረስ በማስተላለፊያ መስመሮች አማካኝነት የሚሰራጭ ሲሆን የመነጨው ኃይል በሂደት ወደ ሙቀትና ሌላ ዓይነት ኢነርጂ ስለሚቀየር በመጨረሻ በሚፈለገው ቦታ ሲደርስ ከመነሻው ካለው የኢነርጂ መጠን አንሶ በምናገኝበት ጊዜ የኢነርጂ ብክነት ተከሰተ እንላለን፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በአጠቃቀም ችግርና የምንጠቀምባቸው የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ኃይል አባካኝ ሲሆኑም የሃይል ብክነት ይከሰታል፡፡ለምሳሌ የኤሌክትሪክ መገልገያ ዕቃዎች አገልግሎት በማይሰጡበት ጊዜ አለማጥፋትና ሶኬቶቻቸውን አለመንቀል፣ በቂ የፀሀይ ብርሃን ባለበት አምፑል ማብራት፣ ኢነርጂ አባካኝ የሆኑ አምፑሎች እና ማሽነሪዎች መጠቀም ለኢነርጂ ብክነት ምክንያት ይሆናሉ፡፡

የሃይል ብክነትን ለመቀነስ ኃይል ቆጣቢ የሆኑ የኤሌክትሪክ መገልገያ ዕቃዎችን መጠቀም፣ የኤሌክትሪክ መጠቀሚያ ዕቃዎችን ኃይል ቆጣቢ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣ ረዥም ጊዜ ያገለገሉ የኤሌክትሪክ ምጣድ፣ ምድጃ፣ ማሽን እና ሌሎች የኤሌክትሪክ መገልገያ ዕቃዎችን በአዳዲስ መቀየር እና የኃይል ጭነት በማይበዛበት ጊዜ ማለትም ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት መጠቀም የሃይል ብክነትን ለመቀነስ ከፍተኛ ጠቀሜታ አላቸው፡፡

በሀገራችን በተደጋጋሚ ለሚከሰተው የኃይል መቆራረጥ ችግር እንደ ምክንያት ከሚጠቀሱት መካከል የማስተላለፊያ መስመሮች እርጅና እና ኃይል አባካኝ የኤሌክትሪክ መገልገያ ዕቃዎች ሲሆን በየወቅቱ ያለው የኃይል አጠቃቀም ወጥ አለመሆኑ ሌላኛው ምክንያት ነው፤ ለዚህ ችግር እንደ መፍትሔ የሚቀመጠው የማስተላለፊያ መስመሮችን አቅም ማሻሻል፣ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እና ኃይል ቆጣቢ መሳሪዎችን መቆጠቀም ሊከሰት የሚችለውን የሃይል ብክነት ለመቀነስ ያስችላል፡፡


#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.1K views13:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ