2022-09-24 10:42:40
የኢኤአ የሳምንቱ አበይት መረጃዎች ሲታወሱ
**************
• የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የከፍተኛ ማኔጅመንት አባላት፣ የመሰረታዊ ሠራተኛ ማህበር ስራ አመራሮች፣ ከዋናው መስሪያ ቤት ጀምሮ እስከ ማዕከላት ድረስ የሚገኙ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ ማካሄዱን፣
• በየደረጃው የሚገኝ የተቋሙ አመራርና ሰራተኛ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀት እንዳለበትና አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እንዲቻል በርካታ የአሰራር ስርዓቶችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ መግለፃቸውን፣
• በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚያጋጥሙ ቁልፍ ችግሮችን ሊፈታ የሚችል የሶስት ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ለከፍተኛ ማኔጅመንት አባላት እና በየደረጃው ለሚገኙ የስራ ሃላፊዎች መቅረቡን፣
• ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት ቀልጣፋ፣ አስተማማኝና ጥራቱን የጠበቀ በማድረግ የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማርካት እንዲቻል በቀረቡት የሶስት ዓመት ስትራቴጂክና በ2015 በጀት አመት ዕቅድና በ2014 በጀት ዓመት አፈፃፀም ላይ የተቋሙ አመራሮች የቡድን ውይይት ማካሄዳቸውን፣
• የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ማኔጅመንት አባላትና በየደረጃው የሚገኙ የስራ ሃላፊዎች ለሶስት ተከታታይ ቀናት ባካሄዱት የውይይት መድረክ ላይ ለብልሹ አስራር ምክንያት የሆኑ ምንጮችን በማስወገድ የደንበኞችን የእርካታ ደረጃ ማሳደግ እንደሚገባ መገለፁ፣
• የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ለአንድ ሃገር ሁለንተናዊ እንቅስቃሴና ኢኮኖሚዊ ዕድገት የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ማሻሻልና የደንበኞችን የእርካታ ደረጃ ማሳደግ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን መግለፃቸው፣
• በተቋሙ ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት የህፃናት ማቆያ ማዕከላት የሴት ሠራተኞችን ተደራራቢ የሥራ ጫና እየቀነሱ መሆኑን፣
• በደብረ ማርቆስ ከተማ የመንገድ መብራት ገመድ ስርቆት ሲፈፅም የነበረው ተጠርጣሪ ግለሰብ በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉንና ምርመራ እየተካሄደበት መሆኑን የሳምንቱ አበይት መረጃዎቻችን ነበሩ፡፡
ሠናይ ቅዳሜና ዕሁድ እንዲሆንላችሁ ተመኘን!
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
1.7K views07:42