2022-09-30 18:13:54
የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
****
የአዲስ ሃይል ጠያቂ ደንበኞች አገልግሎት ለማግኘት ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ከመሄዳችሁ በፊት የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላታችሁን ማረጋገጥ ይጠበቅባችኋል፡፡
"ለነጠላ ፌዝ ቆጣሪ አዲስ ኃይል ጠያቂዎች "
1. የአመልካቹ የቀበሌ መታወቂያ፣ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ፣
2. አንድ ጉርድ ፎቶ /3 በ4/፣
3. የኪራይ ቤት ከሆነ ከባለቤቱ የተሰጠ የስምምነት ደብዳቤ፣
4. ለኃይል ማሻሻያ ወይም ለተጨማሪ ቆጣሪ ከሆነ የኤሌክትሪክ ፍጆታ የመጨረሻ ክፍያ ደረሰኝ፣
5. ጥያቄው ለሽርክና ማህበር ከሆነ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የሽርክና ማረጋገጫ ሰነድ ኮፒ፤
6. የሃይል ጥያቄው በመንግስት ለሚተዳደሩ ቤቶችና ቦታዎች ከሆነ፡-
• የሃይል ጥያቂውን ያቀረበው ቤቱን በመንግስት ስም የተዋዋለ ተከራይ ከሆነ በሚመለከተው የመንግስት አካል ፍቀድ ማግኘት እና ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ሲያቀርብ አገልግሎቱ የሚፈቀድለት ሲሆን ማንኛውም ኃላፊነት ቤቱን የሚያስተዳድረው የመንግስት አካል ይሆናል፡፡
• የመንግስት /የቀበሌ ቤት/ ተከራይ የኪራይ ውል አያይዞ ሲያቀርብ አገልግሎቱን በተከራዩ ስም ሊያገኝ ይችላል፤ነገር ግን ለሚሰጠው ኃላፊነትም ሙሉ ኃላፊነት የተከራዩ ይሆናል፡፡
7. የሃይል ጥያቄው ኃላፊነቱ ለተወሰነ የግል ድርጅት ከሆነ ከላይ ከላይ በተራ ቁጥር የተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች እንዳሉ ሆኖ የድርጅቱ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የድርጅቱን ዋና ስራ አስኪያጅ ማንነትን የሚገልፅ መታወቂያ፣
• ኢንስፔክሽን /ማስገመቻ ለነጠላ ፌዝ 90 ብር፣
"ለሶስት ፌዝ እና ለከፍተኛ ኃይል ጠያቂዎች"
1. የሃይል ጥያቄው ከ14 ኪሎ ዋት እና በላይ ከሆነ ከላይ ለነጠላ ፌዝ አገልግሎት ከተጠቀሱት ማስረጃዎች በተጨማሪ በኤሌክትሪክ ነክ ሥራዎች ፈቃድ ባለው ተቋራጭ የተሰራ የኤሌክትሪክ ዲዛይን ፕላን ማቅረብ ይጠበቅበታል፣
2. አገልግልቱን ለመስጠት ለሚከናወኑ የኢንስፔክሽን እና የማስገመቻ ክፍያዎች (በየጊዜው የሚደረገው የዋጋ ክለሳ እንደተጠበቀ ሆኖ፣
• ለባለ ሶስት ፌዝ ቆጣሪ 300 ብር፣
• ከ24 ኪሎ ዋት እስከ 120 ኪሎ ዋት 500 ብር፣
• ከ121 ኪሎ ዋት እስከ 1 ሜጋ ዋት 5000 ብር፣
• ከ 1 ሜጋ ዋት በላይ 10 ሺህ ብር ብር መክፈል ይጠበቅባችኋል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
5.6K views15:13