2022-10-11 09:16:49
የኢኤአ በሳምንቱ ተደራሽ ያደረጋቸው አበይት መረጃዎች ሲታወሱ
*****************
• የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በዲስትሪቢዩሽን መስመሮች እርጅና ምክንያት የሚከሰተውን የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ችግር በዘላቂነት ለመቀነስ የሚያስችሉ የዲስትሪቢዩሽን መስመሮች ማሻሻያና ማስፋፊያ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን መገለፁ፣
• ላለፉት ስድሳ ዓመታት ሲያገለግል የቆየው የጎፋ ማዕከላዊ እቃ ግምጃ ቤት ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ፣የአገልግሎት ዘመናቸው ያለፈባቸው እና ጥቅም ላይ ውለው ተመላሸ የሆኑ ንብረቶችን ለይቶ በማስቀመጥ የንብረት አያያዙን ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን መቀነስ መቻሉን መገለፁ፣
• የኢቲዮ-ቴሌኮም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የሃገሪቱን የኤሌክትሪክ የኃይል ስርጭት መቆጣጠሪያ ማዕከልና የአዲስ አበባ ከተማን የኃይል ማሰራጫ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ ጎብኝት ማድረጋቸው፣
• የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮተቤ መካኒካል ወርክሾፕ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የሚያስችሉ አስፈላጊ ግብዓቶችን እያመረተና የጥገና ስራ እያከናወነ መሆኑ፤
• የኤሌክትሪክ መገልገያ ዕቃዎች አገልግሎት በማይሰጡበት ጊዜ አለማጥፋትና ሶኬቶቻቸውን አለመንቀል፣በቂ የፀሀይ ብርሃን ባለበት አምፑል ማብራት፣ኢነርጂ አባካኝ የሆኑ አምፑሎች እና ማሽነሪዎች መጠቀም ለኤሌክትሪክ ኃይል ብክነትና መንስዔ እንደሆኑ መገለጻቸው፣
• ተቋሙ 905 ነጻ የጥሪ ማዕከል ባጋጠመው ድንገተኛ የቴክኒክ ችግር ምክንያት አገልግሎት መስጠት ማቆሙንና የተፈጠረው የቴክኒክ ችግር ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን መገለፁ፣
• እሁድ መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀን 9፡00 ሰዓት ድረስ በደብረብርሃን 2 የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ለሚደረግ የጥገና ሥራ በተለዩ አንድንድ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ መገለፁ፣
• የመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት መተላለፉ፣
• የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኮተቤ ጋራዥ ውስጥ የሚገኙ አልሙንየሞችን እና ቁርጥራጭ ብረቶችን ለመሸጥና ለኪራይ አገልግሎት የሚውሉ ሱቆችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት እንደሚፈልግ እንዲሁም የተለያዩ የአይ.ሲ.ቲ/የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ መሆኑን መገለፁ፣
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
1.3K views06:16