Get Mystery Box with random crypto!

ለጥገና ሥራ የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት በተለያዩ አካባቢዎች ***** የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል | Ethiopian Electric Utility

ለጥገና ሥራ የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት በተለያዩ አካባቢዎች
*****
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እሁድ መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀን 9፡00 ሰዓት ድረስ በደብረብርሃን 2 የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ የጥገና ሥራ እንደሚያከናውን አሳውቋል፡፡

በዚህ መሰረት በእነዋሬ፣ በሸኖ፣ በጁኒፕር፣ በመስታወት ፋብሪካ፣ በቦርት ማልት ፋብሪካ፣ በደብረብርሃን ኢንዱስትሪ ፋብሪካ፣ በመንዲዳ፣ በሃገረማርያም፣ በዋን ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ፣ ደብረብርሃን ከተማ እና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡

ስለሆነም ከላይ በተጠቀሱት አከባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንን ተገንዝባችሁ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et