Get Mystery Box with random crypto!

በከተሞች አካባቢ የሚስተዋለውን የሃይል መቆራረጥ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት እየተሰራ ነው ***** | Ethiopian Electric Utility

በከተሞች አካባቢ የሚስተዋለውን የሃይል መቆራረጥ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት እየተሰራ ነው
**********************
በዲስትረቡሽን መስመሮች እርጅና ምክንያት በከተሞች አካባቢ የሚስተዋለውን የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ የዲስትሪቡሽን መስመሮች መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡

በፕሮጀክት ዳይሬክቶሬቱ የዲስትሪቢዩሽን ሪሃቢሊቴሽን ፕሮግራም ጽ/ቤት ተደጋጋሚ የሃይል መቆራረጥ ችግር የሚስተዋልባቸውን አካባቢዎች በጥናት በመለየት የተለያዩ የዲስትሪቢዩሽን መስመሮች መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንና በዚህም እየጨመረ ከመጣው የሃይል ፍላጎት ጋር አብሮ የሚሄድ አስተማማኛ የዲስትሪቢዩሽን መስመር በመገንባ በተደጋጋሚ የሚስተዋለውን የኃይል መቆራረጥ ችግር መቀነስ መቻሉን በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

በከተሞች አካባቢ የሚስተዋለውን የሃይል መቆራረጥ ችግር በዘላቂናት ለመፍታት ተግባራዊ እየተደረጉ ከሚገኙ የመልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክቶች መካከል የአዲስ አበባ ዲስትሪቢዩሽን የመልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት፣ የስድስቱ ከተሞች ዲስትሪቢዩሽን መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት፣ የአዲስ አበባ ትራንስሚሽንና ዲስትሪቢዩሽን መልሶ ግንባታና የአቅም ማሳደግ ፕሮጀክት፣ የ10 ከተሞች ዲስትሪቢዩሽን ኔትዎርክ ማሻሻያ ፕሮጀክቶች እና ሌሎች ፕሮጀክቶችም እንደሚገኙበት ተገልፃል፡፡

በቻይና ኤግዚም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ብድር እየተከናወነ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዲስትሪቢዩሽን የመልሶ ግንባታና የአቅም ማሳደግ ፕሮጀክት የፊዚካል ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ የማስተካከያ ስራዎች፣ የቴስትና ኮሚሽኒንግ እና የርክክብ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ከቀረበው ሪፖርት መረዳት ተችሏል፡፡

በአፍሪካ ልማት ባንክ የገንዘብ ድጋፍ እየተከናወነ የሚገኘው የአዲስ አበባ ትራንስሚሽንና ዲስትሪቢዩሽን መልሶ ግንባታ እና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት 52.75 በመቶ መጠናቀቁንና ከመረጃ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ወይም ስካዳ ሲስተም በስተቀር ፕሮጀክቱን በሚቀጥለው በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ የእቅድ ክለሳ መደረጉን ተመላክቷል፡፡

የ6ቱ ከተሞች ዲስትሪቢዩሽን መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት አንድ አካል የሆኑት የወላይታ ሶዶ፣ የሐረር፣ የሻሸመኔ፣ የደብረማርቆስ፣ የጎንደር እና የኮምቦልቻ ከተሞች 69.38 በመቶ አፈጻፀም ላይ እንደሚገኝና ቀሪ ስራዎችን በሚቀጥለው በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል፡፡

በሎት አንድ እየተከናወነ የሚገኘው የወላይታ ሶዶ እና ሐረር ከተሞች የዲስትቡሽን ኔትዎርክ መልሶ ግንባታ ስራ 61.1% ላይ የደረሰ ሲሆን 5 ሺህ 3 መቶ 95 የኮንክሪት ምሰሶ ተከላ ስራ መከናወኑን ታውቋል፡፡

በሎት ሁለት እየተከናወነ የሚገኘው የሻሸመኔ እና ደ/ማርቆስ ከተሞች የዲስትቡሽን ኔትዎርክ መልሶ ግንባታ ስራ 79.47 % ላይ መድረሱንና እስካሁን 7 ሺህ 1 መቶ 32 የኮንክሪት ምሰሶ ተከላ ስራ መሰራቱን ከቀረበው ሪፖርት መረዳት ተችሏል፡፡

በሎት ሶስት እየተከናወነ የሚገኘው የጎንደር እና ኮምቦልቻ ከተሞች የዲስትቡሽን ኔትዎርክ መልሶ ግንባታ ስራ ደግሞ 50.6% የአፋጻፀም ደረጃ ላይ መድረሱንና እካሁን 2 ሺህ 2 መቶ 63 የኮንክሪት ምሰሶ ተከላ ስራ እንዲሁም የ12.49 ኪ.ሜ የዝቅተኛ ቮልቴጅ ኬብል ዝርጋታ ስራ መሰራቱን በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል፡፡

በአዴል (ADELE) ፕሮግራም ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ብድር ለሚሰሩ የመልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ስራዎች አስፈላጊ የሆኑ የጨረታ ሰነድ ዝግጅትና የአማካሪ ድርጅቶች ቅጥርና ሌሎች ተያያዥ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡

በዚህ ፕሮግራም ተካተው እየተሰሩ የሚገኙት 4ኛ ዙር የአዲስ አበባ ዲስትሪቢዩሽን ኔትዎርክ ማሻሻያ ፕሮጀክት እና የ10 ከተሞች ዲስትሪቢዩሽን ኔትዎርክ ማሻሻያ ፕሮጀክት ማለትም የቢሾፍቱ፣ የደብረብረሃን፣ የሱሉልታ፣ የአምቦ፣ የነቀምት፣ የአሶሳ፣ የሆሳእና፣ የዲላ፣ የአሰላ እና የጅጅጋ ከተሞች ዲስትሪቢዩሽን መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ስራ የኔትዎርክ መረጃ የማጥራትና ሎሎች ተያያዥ የዝግጅት ስራዎች መከናወናቸውን በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

በሃገሪቱ የተፈጠሩ የፀጥታ ችግሮች፣ ከወሰን ማስከበር ጋር የተያያዙ ችግሮች፣ የሲሚንቶ እጥረትና የዋጋ መናር፣ የኮንክሪት ምሰሶ አቅርቦት እጥረትና የመሳሰሉ ችግሮች እየተከናወኑ የሚገኙ የዲስትሪቢዩሽን ኔትዎርክ ማሻሻያ የስራ ሂደት ላይ ያጋጠሙ አሉታዊ ተፅኖ ያሳደሩ ችገርች መሆናቸውን ተገልጿል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et