Get Mystery Box with random crypto!

በዚህ የክረምት ወቅት ወርሃዊ ክፍያ ለመፈፀም ብለው ስለምን ይጉላላሉ? **************** | Ethiopian Electric Utility

በዚህ የክረምት ወቅት ወርሃዊ ክፍያ ለመፈፀም ብለው ስለምን ይጉላላሉ?
******************
ወድ የድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን፡- በዚህ የክረምት ወቅት ወርሃዊ ክፍያ ለመፈፀም ብለው ስለምን ይጉላላሉ? ሳይንከራተቱ፤ ሳይጉላሉ ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብዎን ካሉበት ሆነው በቀላሉ በቴሌብር፣ በ CBE Birr /707070/፣ በሞባይል ባንኪንግና በኢንተርኔት ባንኪንግ ይክፈሉ!

እነዚህን ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች ተጠቅመው ክፍያዎትን በመፈፀም ካላስፈላጊ ወጪ ይዳኑ! ኑሮዎትንም ያቅልሉ!

በጥሬ ገንዘብ ለመክፈል ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላችን መምጣት ጊዜዎን፣ ጉልበትዎንና ገንዘብዎን ማባከን መሆኑን ይረዱ፡፡ ካሉበት ሆነው ቀላል አማራጭ ብቻ ይጠቀሙ!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et