Get Mystery Box with random crypto!

ስፖርት ክለቡ ከጎፈሬ ትጥቅ አምራች ድርጅት ጋር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራረመ ********** | Ethiopian Electric Utility

ስፖርት ክለቡ ከጎፈሬ ትጥቅ አምራች ድርጅት ጋር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራረመ
******************
የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ከጎፈሬ ትጥቅ አምራች ድርጅት ጋር የብራንድ ትጥቅ አቅራቢነት ስፖንሰርሺፕ ስምምነት ትላንት በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል ተፈራርሟል፡፡

ሥምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮ- ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጫላ አማን እና የጎፈሬ ትጥቅ አምራች ደርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሳሙኤል መኮንን ናቸው።

ለሶስት አመት በሚቆየው በዚህ ስምምነትም፤ ለወንዶች እና ለሴቶች ዋና ቡድን፣ ለ21 ዓመትና ለ17 ዓመት በታች ቡድኖች እንዲሁም ክለቡን ወክለው በተለያየ የስፖርት ዘርፍ ለሚሳተፉ የክለቡ አባላት ድርጅቱ ትጥቅ እንሚያቀርብ ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጫላ አማን በዚህ ወቅት፡- ስምምነቱ የውጭ ምንዛሬ ለማስቀረትና የሀገር በቀል ምርት የሚያቀርቡ የትጥቅ አምራች ድረጅቶችን ለማበረታታት ጉልህ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡

ድርጅቱም የተመረጠውም የኢትዮ-ኤሌክትሪክን ክብርና አንጋፋነት የሚመጥን ምርት ማቅረብ የሚችል መሆኑን በመረጋገጡ ነው ብለዋል፡፡

የጎፈሬ ትጥቅ አምራች ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሳሙኤል መኮንን በበኩላቸው ድርጅታቸው ለአራት ዓመታት ያክል በኢትዮጵያ ውስጥ እና በውጭ ሃገር ከሚገኙ የስፖርት ክለቦች ጋር በኮንትራትና በግዢ በሚደረጉ ስምምነቶች ትጥቅ እያቀረበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከኢትዮ-ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብም ጋር የተፈረመው ስምምነት የዚህ አንድ አካል እንደሆነና ልዩ የሚያደረገውም ለሶስት ዓመታት በቋሚነት የሚቆይ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም በስምምነቱ ላይ ከትጥቅ አቅርቦት በተጨማሪ ለአስልጣኞች፣ ለተጫዋቾችና ለደጋፊዎች የተለያዩ የእውቀት ደረጃን ለማሳደግ የሚረዱ ስልጠናዎችን ጎፈሬ ድርጅት እንደሚያመቻችና እንደሚያዘጋጅ በስምምነቱ ወቅት ተጠቁሟል፡፡

በመጨረሻም አንጋፋውን የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ደጋፊ ማህበር ለማበረታት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ጫላ፤ ለደጋፊዎች የሚሆን መለያዎችም እየተዘጋጁ እንደሆነ እና በቅርብ ቀን ለገበያ እንደሚቀርብ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ጎን ለጎን በዕለቱ ክለቡ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የክፍሌ ቦልተናን ውል ለተጨማሪ አንድ ዓመት አራዝሟል፡፡

ሥምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ እጅጉ እና አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ናቸው።

የሁለት ጊዜ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫ ባለቤቱ አይበገሬውና አንጋፋው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እግር ኳስ ክለብ፣ በአንጋፈው አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና እየተመራ የ2014 የከፍተኛ ሊግ የምድብ "ሀ" አሸናፊ በመሆን ፕሪሜየር ሊጉን ከ አራት ዓመታት በኋላ ዘንደሮ መቀላቀሉ ሚታወስ ነው፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et