Get Mystery Box with random crypto!

በሰሜን አዲስ አበባ ዲስትሪክት ስር ለምትገኙ የድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን በሙሉ የሰሜን አ | Ethiopian Electric Utility

በሰሜን አዲስ አበባ ዲስትሪክት ስር ለምትገኙ የድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን በሙሉ

የሰሜን አዲስ አበባ ዲስትሪክት ከዚህ በፊት በአራት ምድብ ሲጠቀምበት የነበረውን የንባብ እና የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ መክፍያ የጊዜ ሰሌዳ ወደ አንድ ለማምጣት ከመጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ መርሃ-ግብር በስራ ላይ አውሏል፡፡

በዚሁም መሰረት ወር በገባ ከ13ኛው ቀን ጀምሮ እስከ 26ኛው ቀን ድረስ የንባብ ጊዜ ሲሆን ወር በገባ ከ28ኛው ቀን እስከሚቀጥለው ወር 4ኛ ቀን ድረስ ደግሞ ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ ክፍያ መክፈያ የጊዜ ሰሌዳ እንዲሆን አድርጓል፡፡

ስለሆነም በዲስትሪክቱ ስር የምተገኙ ደንበኞቻችን ይህንኑ አውቃችሁ ለቆጣሪ አንባቢዎች የተለመደ ትብብራችሁን እንድታደርጉና ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳባችሁን ተቋሙ በዘረጋቸው ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች ማለትም በቴሌ ብር፣ ሞባይል ባንኪንግ፣ ሲ.ቢ.ኢ ብር እና በኢንተርኔት ባንኪንግ እንድትፈፅሙ እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et