Get Mystery Box with random crypto!

በሀዋሳ ከተማ በአጋንሳ መንደር 454 አባወራዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ በሲዳማ ክልል በሀዋሳ | Ethiopian Electric Utility

በሀዋሳ ከተማ በአጋንሳ መንደር 454 አባወራዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ

በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ በቱላ ክፍለ ከተማ በዳቶ ቀበሌ ሲከናወን የነበረው የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት የማስፋፊያ ፕሮጀክት ስራ በመጠናቀቁ 454 አባወራዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ፡፡

በተከናወነው የኤሌክትሪክ የማስፋፊያ ስራ አንድ ባለ 630 እና አንድ 800 ኪ.ቪ ትራንስፎርመሮችን ፣ 307 የኤሌክትሪክ ምሶሶዎች፣ 6.7 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር እና 0.2 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ ስራ ተከናውኗል፡፡

የማስፋፊያ ፕሮጄክቱን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ስድስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡

በተመሳሳይ የግንባታ ስራቸው ተጠናቆ በኮሚሺኒንግ ስራ ላይ ያሉ 10 ፕሮጄክቶች ያሉ ሲሆን በቀጣይ ለአዲስ ደንበኞች አገልግሎት መስጠት የሚጀምሩ ይሆናል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et