Get Mystery Box with random crypto!

260 የመካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የ | Ethiopian Electric Utility

260 የመካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ 260 የመካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ፡፡

ኢንዱስትሪዎቹ የተገነቡት በቃሊቲ ወርቁ ሰፈርና በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ አካባቢዎች ሲሆን ሁሉም የኢንዱስትሪ ሸዶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

ሸዶቹን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያየ አቅም ያላቸው ሰባት ትራንስፎርመሮች እና 283 የዝቅተኛ መስመር መሰሶዎች ተተክለዋል፡፡

በተጨማሪም 230 ቆጣሪዎች የተገጠሙ ሲሆን 400 ሜትር የመካከለኛ መስመርና 10 ነጥብ 8 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ተከናውኗል፡፡

ግንባታውን ለማከናወን 12 ሚሊየን 673 ሺህ 383 ወጪ የተደረገ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ኢንዱስትሪዎቹ ምርት በማምረት ላይ
ይገኛሉ፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et