Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Electric Utility

የቴሌግራም ቻናል አርማ eeuethiopia — Ethiopian Electric Utility E
የቴሌግራም ቻናል አርማ eeuethiopia — Ethiopian Electric Utility
የሰርጥ አድራሻ: @eeuethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.11K
የሰርጥ መግለጫ

EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-19 14:25:49
የባህርዳር ከተማ የውሀ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ መስመር ግንባታ ተጠናቀቀ

የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለባህርዳር ከተማ የውሀ ፕሮጀክት ሲያከናውን የነበረውን ባለ 15 ኪ.ቮ የኤሌክትሪክ መስመር ግንባታ አጠናቀቀ፡፡

ግንባታው የተከናወነው የከተማው ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በከፈለው ዘጠኝ ሚሊዮን 676 ሺ 081 ብር ከ22 ሳንቲም ነው፡፡

በከተማው ቀበሌ 11 ልዩ ቦታው ጨረጨራና አሽረፍ በተገነባው በዚህ መሰረተ ልማት በጨረጨራ አራት እንዲሁም በአሽረፍ ደግሞ ሁለት ከ100 እስከ 1250 ኪ.ቮ አቅም ያላቸው ትራንስፎርመሮች ተተክለዋል፡፡

ለፕሮጀክቱ የተዘረጋው መስመር ባለ 15 ኪ.ቮ መስመር ሲሆን 1.52 ኪ.ሜ የከፍተኛ መስመር እንዲሁም 100 ሜትር ዝቅተኛ መስር ዝርጋታ ተከናውኗል፡፡

የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቱ ከፕሮጀክቱ ባሻገር ለተለያዩ ተቋማትና ነዋሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ ነው፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
1.7K views11:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 11:26:59
ከዋናው ግሪድ ርቀው የሚገኙ ከ200 በላይ የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተጣለበትን ሃገራዊ ሃላፊነት እውን ለማድረግ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን በብሄራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ከዋናው ግሪድ 65 በመቶ እንዲሁም በአማራጭ የኃይል ምንጭ 35 በመቶ የሚሆነውን የህብረተሰብ ክፍል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡

ተቋሙ በዘርፍ ከተሰማሩ የግል ድርጅቶችና ማህበራት ጋር በመሆን በአዴል ፕሮግራም ከዋናው ግሪድ ርቀው የሚገኙ ከ200 በላይ የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡

ለፕሮጀክቱ የተያዘው አጠቃላይ በጀት 400 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን የፕሮጀክቱ ዋና አላማ ከዋናው ግሪድ ርቀው በሚገኙ የሃገሪቱ አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ለማድረግ እና የኑሮ ሁኔታቸውን ለማሻሻል ነው፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ሙሉ መረጃውን ለማግኝት ይህን ማስፈንጠሪያ ተጭነው ያንብቡ: -

http://www.ethiopianelectricutility.gov.et/contents/news
1.9K viewsedited  08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 09:20:28 የኘሮግራም ጥቆማ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዋልታ ሚዲያና ኮሙንኬሽን ኮርፖሬት ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀውን ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ከሚያዝያ 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ሐሙስ ከምሽቱ 2:20 ጀምሮ ማስተላለፍ ይጀምራል፡፡
ስለሆነም ውድ ደንበኞቻችን ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ዘወትር ሐሙስ ከምሽቱ 2:20 እስከ 2:40 በዋልታ ቴሌቪዥን እንድትከታተሉ በአክብሮት እንጋብዛለን።

2.2K views06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 16:43:20
የኘሮግራም ጥቆማ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዋልታ ሚዲያና ኮሙንኬሽን ኮርፖሬት ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀውን ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ከሚያዝያ 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ሐሙስ ከምሽቱ 2:20 ጀምሮ ማስተላለፍ ይጀምራል፡፡

ስለሆነም ውድ ደንበኞቻችን ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ዘወትር ሐሙስ ከምሽቱ 2:20 እስከ 2:40 በዋልታ ቴሌቪዥን እንድትከታተሉ በአክብሮት እንጋብዛለን።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
2.1K views13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 20:39:59
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በሀረር ከተማና አካባቢው እንዲሁም በጅግጅጋና አካባቢው የኤሌክትሪክ አቅርቦት ተቋርጧል

ዛሬ ከቀኑ 10:00 ሰአት ጀምሮ ከድሬዳዋ ሐረር የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ውጪ በሆኑ ባለ 132 ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በሀረር ከተማና አካባቢው እንዲሁም በጅግጅጋ ከተማና አካባቢው የሚገኙ ከተሞች የኤሌክትሪክ አቅርቦት ተቋርጧል፡፡

በምሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል የጥገና ስራው እየተከናወነ ስለሆነ እንደተጠናቀቀ አገልግሎቱን መልሰን ምናገኛኝ መሆኑን አውቃችሁ በትዕግስት እንድትጠባበቁ በክብሮት እናሳውቃለን፡፡
2.5K viewsedited  17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 12:05:58
በድጋሚ #እናስታውስዎ

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ሁሉም የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት #የካርድ_መሙላት አገልግሎት እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ የሚሰጡ መሆኑን እየገለፅን፣ ነገ እሁድ በበዓሉ ዕለት ደግሞ ካዛንቺስ የሚገኘው የአገልግሎት መስጫ ማዕከላችን እስከ ቀኑ 6፡00 ድርስ አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

መልካም በዓል!!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
250 views09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 19:09:26
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ደንበኞቻችን በሙሉ እንኳን ለ2015 ዓ.ም የፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

በዓሉን የሰላም፣ የደስታ፣ የፍቅር እና የጤና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!!

ሽፈራው ተሊላ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ
575 views16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 16:38:32 ተቋማችን ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2015 ዓ.ም የትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡

1.4K views13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 15:11:19 በበዓል ወቅት ሊኖር ሚችለውን የሃይል መቆራረጥ ችግር ለመቀነስ ሲደረግ የቆየው የቅድመ-ዝግጅት ስራ ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመጪው በትንሳዔ በዓል ወቅት የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ችግር እንዳይከሰት እና ሲከሰትም አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የአስቸኳይ ጥገና ግብረ-ሃይል አዋቅሮ የተለያዩ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

ግብረ-ሃይሉ በተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ ችግር የሚስተዋልባቸውን አካባቢዎች በመለየት የመስመር ፍተሻ፣ በመካከለኛና በዝቅተኛ መስመሮች ላይ የኃይል ጭነት የማመጣጠንና ሌሎች የቅድመ-ጥገና ስራዎችን አከናውኗል፡፡

ተቋሙ በበዓሉ ዋዜማ እና በዕለቱ በሁሉም ማዕከል 24 ሰዓት የአስቸኳይ ጥገና የሚያከናውን ግብረ ሃይል አዋቅሮ ለስራ ዝግጁ አድርጓል፡፡

ይሁን እንጂ በበዓሉ ዋዜማና በዕለቱ የሚኖረው የሃይል አጠቃቀም ከፍተኛ ስለሚሆን የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ችግር ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ስለሆነም ከኤክስፖርትና ሲምንቶ አምራች ኢንዱስትሪዎች ውጪ የሆኑ ከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች በትንሳዔ በዓል ዋዜማ ከሰአት በኋላ እና በዕለቱ ቀኑን ሙሉ ከዋናው ግሪድ ኤሌክትሪክ ሃይል እንዳይጠቀሙ ተጠይቋል፡፡

ደንበኞችም በቤት ውስጥ የሚገለገሉባቸውን የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች ኃይል ቆጣቢና ለአደጋ የማያጋልጡ መሆናቸውን ማረጋገጥና በቂ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ኃይል ጭነት በማይበዛበት ሰዓት በተለይ ከምሽቱ 3፡00 እስከ ንጋቱ 11፡00 ባሉት ጊዚያት ቢጠቀሙ የተሻለ የኤሌክትሪክ ኃይል ከማግኘት ባለፈ ሊኖር የሚችለውን የሃይል መቆራረጥ ችግር ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡
የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞችም በዓሉ ሲደርስ የሚኖረውን አላስፈላጊ እንግልት ለማስቀረት እንዲችሉ ከወዲሁ የሚበቃቸውን ያህል የኤሌክትሪክ ኃይል አስቀድመው እንዲገዙ /ካርድ እንዲሞሉ እናሳስባለን፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይል በሚቋረጥበት ጊዜ የጥገና ስራ ለማከናወን የተቋማችንን መታወቂያ የያዙ የቴክኒክ ባለሞያዎቻችን በተለያዩ አካባቢዎች ለስራ ጉዳይ እንደሚንቀሳቀሱ የሚታወቅ ሲሆን የጥገና ሰራተኞች በመምሰል መሠረተ-ልማቱ ላይ ስርቆትና ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ አካላት ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ የኤሌክትሪክ ማሰራጫ መስመሮችን በመጠበቅ እንዲተባበርና እኩይ ተግባራት ሲፈፀሙ ሲመለከትም ለሚመለከተው የህግ አካላትና ለተቋሙ ማሳወቅ ይገባዋል፡፡

በመጨረሻም ማንኛወንም አስተያየትና ጥቆማ ለመስጠት ወደ አቅራቢያ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በአካል በመሄድ ወይም ወደ 905 ነፃ የጥሪ ማዕከል መደወል ማሳወቅ እንደሚያስፈልግ እንጠቁማለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
1.8K views12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 15:11:11
1.6K views12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ