Get Mystery Box with random crypto!

የባህርዳር ከተማ የውሀ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ መስመር ግንባታ ተጠናቀቀ የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ | Ethiopian Electric Utility

የባህርዳር ከተማ የውሀ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ መስመር ግንባታ ተጠናቀቀ

የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለባህርዳር ከተማ የውሀ ፕሮጀክት ሲያከናውን የነበረውን ባለ 15 ኪ.ቮ የኤሌክትሪክ መስመር ግንባታ አጠናቀቀ፡፡

ግንባታው የተከናወነው የከተማው ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በከፈለው ዘጠኝ ሚሊዮን 676 ሺ 081 ብር ከ22 ሳንቲም ነው፡፡

በከተማው ቀበሌ 11 ልዩ ቦታው ጨረጨራና አሽረፍ በተገነባው በዚህ መሰረተ ልማት በጨረጨራ አራት እንዲሁም በአሽረፍ ደግሞ ሁለት ከ100 እስከ 1250 ኪ.ቮ አቅም ያላቸው ትራንስፎርመሮች ተተክለዋል፡፡

ለፕሮጀክቱ የተዘረጋው መስመር ባለ 15 ኪ.ቮ መስመር ሲሆን 1.52 ኪ.ሜ የከፍተኛ መስመር እንዲሁም 100 ሜትር ዝቅተኛ መስር ዝርጋታ ተከናውኗል፡፡

የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቱ ከፕሮጀክቱ ባሻገር ለተለያዩ ተቋማትና ነዋሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ ነው፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et