Get Mystery Box with random crypto!

ከዋናው ግሪድ ርቀው የሚገኙ ከ200 በላይ የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ | Ethiopian Electric Utility

ከዋናው ግሪድ ርቀው የሚገኙ ከ200 በላይ የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተጣለበትን ሃገራዊ ሃላፊነት እውን ለማድረግ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን በብሄራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ከዋናው ግሪድ 65 በመቶ እንዲሁም በአማራጭ የኃይል ምንጭ 35 በመቶ የሚሆነውን የህብረተሰብ ክፍል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡

ተቋሙ በዘርፍ ከተሰማሩ የግል ድርጅቶችና ማህበራት ጋር በመሆን በአዴል ፕሮግራም ከዋናው ግሪድ ርቀው የሚገኙ ከ200 በላይ የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡

ለፕሮጀክቱ የተያዘው አጠቃላይ በጀት 400 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን የፕሮጀክቱ ዋና አላማ ከዋናው ግሪድ ርቀው በሚገኙ የሃገሪቱ አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ለማድረግ እና የኑሮ ሁኔታቸውን ለማሻሻል ነው፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ሙሉ መረጃውን ለማግኝት ይህን ማስፈንጠሪያ ተጭነው ያንብቡ: -

http://www.ethiopianelectricutility.gov.et/contents/news