Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Electric Utility

የቴሌግራም ቻናል አርማ eeuethiopia — Ethiopian Electric Utility E
የቴሌግራም ቻናል አርማ eeuethiopia — Ethiopian Electric Utility
የሰርጥ አድራሻ: @eeuethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.11K
የሰርጥ መግለጫ

EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-04-12 19:02:00
የኘሮግራም ጥቆማ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚያከናውናቸውን የስራ እንቅስቃሴዎች እና በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እየተከናወኑ የሚገኙትን የስራ እንቅስቃሴዎች ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅ ከዋልታ ሚዲያና ኮሙንኬሽን ኮርፖሬት ጋር በመተባበር #አውደ ኤሌክትሪክ የተሰኘ ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም በማዘጋጀት ሐሙስ ሚያዝያ 12 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 2:20 ጀምሮ ማስተላለፍ ይጀምራል፡፡

ስለሆነም ውድ ደንበኞቻችን ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ዘወትር ሐሙስ ከምሽቱ 2:20 እስከ 2:40 በዋልታ ቴሌቪዥን እንድትከታተሉ በአክብሮት እንጋብዛለን።


#የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
1.9K views16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 14:15:47
በመጪው የትንሳዔ በዓል ሊከሰት የሚችለውን የኃይል መቆራረጥ ችግር ለመከላከል የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በመጪው የትንሳዔ በዓል ላይ የኃይል መቆራረጥ እንዳያጋጥም ለማድረግ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን ዛሬ ባካሄዱት የጋራ ውይይት ገልፀዋል፡፡

በውይይቱም ከኃይል ማመንጫ ጀምሮ እስከ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችንና ትራንስፎርመሮች ብልሽቶች ሲያጋጥሙ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የጋራ ኮሚቴ መዋቀሩም ተመላክቷል፡፡

በዋዜማውና በበዓሉ ዕለት የኤሌክትሪክ ኃይል ሳይቆራረጥና ሳይዋዥቅ በተገቢው ሁኔታ ለማድረስና ችግሩ ከተከሰተም በአፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆናቸው ገልፀዋል፡፡

በውይይቱም በተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥ የሚስተዋልባቸውን አካባቢዎች በመለየት በመካከለኛና በዝቅተኛ መስመሮች ላይ ጭነት የማመጣጠንና የቅድመ መከላከልና የጥገና ስራዎችን በመሰራት ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከበዓሉ ጋር ተያይዞ በሚኖር የሃይል መጨናነቅ የኃይል መቆራረጥ ችግር እንዳያጋጥም ደንበኞች የኤሌክትሪክ ኃይል ጭነት በማይበዛበት ሰዓታት በተለይ ከምሽቱ 3፡00 እስከ ንጋቱ 11፡00 ባሉት ጊዜያት ቢጠቀሙ የተሻለ የኤሌክትሪክ ኃይል ከማግኘት ባለፈ የኤሌክትሪክ መቆራረጥን እንደሚቀንስ ተመላክቷል፡፡

ደንበኞች ከተቋሙ ጋር በተያያዘ ማንኛውንም መረጃዎች ለመጠየቅ፣ ጥቆማዎችና አስተያይቶች ለማቅረብ ወደ አቅራቢያቸው የሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በአካል ወይም ስልክ በመደወል እንዲሁም በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ያሉ ደንበኞች ደግሞ ወደ በ905 ነፃ የጥሪ ማዕከል በመደወል ማሳወቅ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
2.7K views11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 15:05:00
የሐረር ማከፋፈያ ጣቢያ የማስፋፊያ ስራ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
በሐረር ቁጥር 2 የማከፋፈያ ጣቢያ ሲከናወን የነበረው የማስፋፊያ ስራ ተጠናቆ ጣቢያው በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
የማስፋፊያ ስራው የማከፋፈያ ጣቢያውን ኃይል የማከፋፈል አቅም በ5 ነጥብ 04 ሜ.ዋ ለማሳደግ ያግዛል፡፡

ለዚህም በጣቢያው አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩት ሶስት ባለ 6 ነጥብ 3 ኤም.ቪ.ኤ ፓወር ትራንስፎርመሮች በተጨማሪ በማስፋፊያ ስራው አንድ ባለ 6 ነጥብ 3 ኤም.ቪ.ኤ ፓወር ትንስፎርመር እንዲተከል ተደርጓል፡፡

የተከናወነው የማስፋፊያ ስራ ለሐረር ከተማ ኃይል በሚያሰራጩ ባለ 15 ኪ.ቮ መስመሮች ላይ ያለውን ጭነት የሚያቃልል ሲሆን በከተማው የሚከሰተውን የኃይል መቆራረጥ ችግርም የሚቀርፍ ይሆናል፡፡

የማከፋፈያ ጣቢያው ለሐረር ከተማ፣ ለድሬ ጠያራ፣ ባቢሌና ጉርሱም ወረዳዎች ኃይል የማከፋፈል አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም የባቢሌ የማከፋፈያ ጣቢያ የማስፋፊያ ስራ በቅርቡ ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት ስራ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን ስራው ሲጠናቀቅ በአካባቢው ያለውን የኃይል መቆራረጥ በከፍተኛ ደረጃ ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.5K views12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 17:07:24
ውድ የድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን፤ የተጠቀማችሁበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ቀላልና ምቹ በሆነው #የቴሌ_ብር መተግበሪያ ይክፈሉ፡፡ *127# አጭር ቁጥር በመጠቀም ብቻ ሳይጉላሉና ሳይንገላቱ የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ካሉበት ሆነው በቀላሉ ይክፈሉ፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
2.1K views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 12:10:41
ውድ ደንበኞቻችን #እናስታውስዎ ነገ #ቅዳሜ_መጋቢት_30 ቀን 2015 ዓ.ም ዋናው መስሪያ ቤትን ጨምሮ የክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤቶች፣ ዲሰትሪክቶች እና በየደረጃው የሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
3.0K views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 09:09:29
ውድ #የድህረ_ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኛችን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታዎን በቴሌ ብር ለመክፈል የሚከተሉትን ቅደም ተከተሎች ይጠቀሙ

በመጀመሪያ ወደ *127# በመደውል የቴሌ ብር ደንበኛ ይሁኑ፤ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆኑ ካረጋገጡ በኋላ ከታች ያለውን መመሪያዎች ይጠቀሙ፡፡

1. መልሰው ወደ *127# ይደውሉ፣
2. ከሚያመጣሎት መዘርዝር # በማስገባት ምላሽ ይስጡ፣
3. በመቀጠል ቁጥር 8 በማስገባት በቴሌ ብር ለመክፈል ብለው ምላሽ ይስጡ፣
4. በቴሌ ብር ለመክፈል በሚል ዝርዝር ከሚቀርብሎት መዘርዘር የአገልግሎት ክፍያ ለመፈፀም የሚለውን አማራጭ ቁጥር 2 ይምረጡ፣
5. በድርጅት ስም የሚለውን ለመምረጥ 1ን ያስገባሉ፣
6. 1ን በማስገባት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚለውን ይምረጡ፣
7. ከዛም የውል ቁጥሮን ማለትም ደረሰኝዎ ላይ ያለውን /Contract Account Number/ (10000*******) የሚለውን ያስገቡ፣
8. ለማረጋገጥ 1ን የሚለውን ያስገቡ፣
9. ምክንያትዎን ያስገቡ፣
10. በመጨረሻም የሚስጥር ቁጥርዎን ያስገባሉ፣

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
3.3K views06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 21:02:45
የመኖሪያ ቤት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኛ ከሆኑ፤ ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳቦትን በቀላሉ ለማስላት ያመችዎት ዘንድ ይህንን #የታሪፍ መረጃ ይጠቀሙ፡፡ ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብዎትንም በወቅቱ ይፈፅሙ!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
3.8K viewsedited  18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 22:35:04
በማሻሻያ ፕሮጀክቱ 150 ሺ አዲስ ደንበኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአገሪቱ በሚገኙ ስድስት ከተሞች በሚያከናውነው የኤሌክትሪክ ማሰራጫ መስመሮች መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት 150 ሺ አዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡

እነዚህ አዲስ ደንበኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሚሆኑት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ካለፈው ዓመት ጀምሮ በወላይታ ሶዶ፣ ሐረር፣ ሻሸመኔ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ጎንደርና ኮምቦልቻ ከተሞች እያከናወነ በሚገኘው የመስመሮች መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት አማካኝነት ነው፡፡

የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሚሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች የኤሌክትሪክ መስመር በአካባቢያቸው ተዘርግቶ ነገር ግን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ያልሆኑ እንዲሁም ከተዘረጋው መሰረተ ልማት እስከ 2.5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኙትን የሚያካትት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በከተሞች ያለውን የኃይል አቅርቦት አስተማማኝና ጥራት ያለው ለማድረግና የኃይል መቆራረጥ ለመቀነስ ያረጁ የኤሌክትሪክ መስመሮችን መልሶ ለመገንባትና ለማሻሻል የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን በከፍተኛ ወጪ ተግባራዊ እደረገ ይገኛል፡፡

ከነዚህ መካከል የስድስቱ ከተሞች ፕሮጀክት አንዱ ሲሆን እስካለፈው ጥር ወር ድረስ አፈፃፀሙ 74.35 በመቶ ደርሷል፡፡

በአሁኑ ወቅት በፕሮጀክቱ የኮንክሪት ምሰሶ ተከላ፣ የዝቅተኛና የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ፣ መስመር ላይ የሚገጠሙ መሳሪያዎችን ማሰር፣ ቀሪ ግብዓቶችን ወደ ግንባታ ቦታዎች ማጓጓዝ፣ የተመረቱ ግብዓቶች ፍተሻ ማከናወን የመሳሰሉ ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ቴሌግራም ቻናል ይጎብኙ፡ t.me/eeuethiopia
3.0K viewsedited  19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 13:48:05
ውድ የድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን፤ የተጠቀማችሁበትን የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ተቋሙ በዘረጋቸው ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች በመጠቀም ይፈፅሙ፡፡ #ዘመናዊ የክፍያ አማራጮችን መጠቀም አስፈላጊ ካልሆነ ወጪና እንግልት ያድናል! ኑሮንም ያቃልላል! በጥሬ ገንዘብ ለመክፈል ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በመምጣት ጊዜዎትን፣ ጉልበትዎትንና ገንዘብዎትን አያባክኑ፡፡ ካሉበት ሆነው በተዘረጉ ቀላልና ዘመናዊ የክፍያ አማራጭ ብቻ ይጠቀሙ!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ዝርዝር መረጃዎቻችን ለማግኘት ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.etውድ የድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን፤ የተጠቀማችሁበትን የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ተቋሙ በዘረጋቸው ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች በመጠቀም ይፈፅሙ፡፡ #ዘመናዊ የክፍያ አማራጮችን መጠቀም አስፈላጊ ካልሆነ ወጪና እንግልት ያድናል! ኑሮንም ያቃልላል! በጥሬ ገንዘብ ለመክፈል ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በመምጣት ጊዜዎትን፣ ጉልበትዎትንና ገንዘብዎትን አያባክኑ፡፡ ካሉበት ሆነው በተዘረጉ ቀላልና ዘመናዊ የክፍያ አማራጭ ብቻ ይጠቀሙ!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ዝርዝር መረጃዎቻችን ለማግኘት ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.2K views10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 12:47:42
በሌላ ሰው ስም ያለን ቆጣሪ ወደ ሌላ ሰው እንዴት #ማዛወር እንደሚቻል ያውቃሉ እንግዲያውስ እንሳውቀዎ !!
የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ከአንድ ሰው/ድርጅት ወደ ሌላ ሰው/ድርጅት ስም የሚተላለፈው ተጠቃሚው በሞት ሲለይ ወይም የይዞታው ባለቤትነት ወደ ሌላ ሰው /ድርጅት ሲተላለፍ ሲሆን የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ሊሟሉ ይገባል፡፡

• የስም ማዛወሪያ ማመልከቻ፣ በእለቱ ያለ የቆጣሪ ንባብና የመጨርሻ የቆጣሪ ፍጆታ ክፍያ በአመልካቹ ተከፍሎ ሲቀርብ፣
• ህጋዊ ወራሽነትን የሚገልፅ ማስረጃ፣ ተያያዥ ክፍያዎችን እንዲሁም ከእዳ ነጻ ስለመሆኑ የሚገልፅ ማስረጃ ሲቀርብ፣
• በህጋዊ ውርስ እና ሽያጭ ለሚደረግ የስም ዝውውር ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ እና ውርስ ወይም ሽያጭ የተደረገበት ህጋዊ ውል/ማስረጃ ሲቀርብ፤ ነገር ግን የውርስ እና ሽያጭ ማስረጃዎች መቅረብ በማይችሉበት ጊዜ በህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ መስተናገድ ይችላል፡፡
• የይዞታ ማረጋገጫ በባንክ ወይም በሌላ ሁኔታ ከተያዘ ወይም የዕዳ እገዳ ካለበት ካርታውን ከያዘው አካል ማስረጃ ሲቀርብ፣
• የይዞታ ማስረጃው በሚዘገይበት ጊዜ የዘገየበትን ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ሲቀርብ የስም ማዛወር ስራው በሽያጭ ውሉ እና በህጋዊ የውርስ ማስረጃ ሊስተናገድ ይችላል፡፡
• ተቋሙ በልዩ ሁኔታ ያስቀመጣቸው ደንበኞችን በተመለከተ ከሚመለከተው የመንግስት አካል መረጃ ከተገኘ በኋላ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
• በአጠቃላይ ቆጣሪው የሚተላለፍለት ወይም እንዲዛወርለት ያመለከተው ህጋዊ ወራሽ የሚጠበቅበትን ማስረጃ አሟልቶ ከቀረበ በ3 ቀናት ውስጥ አዲስ የውል ስምምነት ፈርሞ የስምምነቱን ቅጅ እንዲደርሰው ይደረጋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
1 view09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ