Get Mystery Box with random crypto!

በሌላ ሰው ስም ያለን ቆጣሪ ወደ ሌላ ሰው እንዴት #ማዛወር እንደሚቻል ያውቃሉ እንግዲያውስ እንሳው | Ethiopian Electric Utility

በሌላ ሰው ስም ያለን ቆጣሪ ወደ ሌላ ሰው እንዴት #ማዛወር እንደሚቻል ያውቃሉ እንግዲያውስ እንሳውቀዎ !!
የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ከአንድ ሰው/ድርጅት ወደ ሌላ ሰው/ድርጅት ስም የሚተላለፈው ተጠቃሚው በሞት ሲለይ ወይም የይዞታው ባለቤትነት ወደ ሌላ ሰው /ድርጅት ሲተላለፍ ሲሆን የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ሊሟሉ ይገባል፡፡

• የስም ማዛወሪያ ማመልከቻ፣ በእለቱ ያለ የቆጣሪ ንባብና የመጨርሻ የቆጣሪ ፍጆታ ክፍያ በአመልካቹ ተከፍሎ ሲቀርብ፣
• ህጋዊ ወራሽነትን የሚገልፅ ማስረጃ፣ ተያያዥ ክፍያዎችን እንዲሁም ከእዳ ነጻ ስለመሆኑ የሚገልፅ ማስረጃ ሲቀርብ፣
• በህጋዊ ውርስ እና ሽያጭ ለሚደረግ የስም ዝውውር ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ እና ውርስ ወይም ሽያጭ የተደረገበት ህጋዊ ውል/ማስረጃ ሲቀርብ፤ ነገር ግን የውርስ እና ሽያጭ ማስረጃዎች መቅረብ በማይችሉበት ጊዜ በህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ መስተናገድ ይችላል፡፡
• የይዞታ ማረጋገጫ በባንክ ወይም በሌላ ሁኔታ ከተያዘ ወይም የዕዳ እገዳ ካለበት ካርታውን ከያዘው አካል ማስረጃ ሲቀርብ፣
• የይዞታ ማስረጃው በሚዘገይበት ጊዜ የዘገየበትን ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ሲቀርብ የስም ማዛወር ስራው በሽያጭ ውሉ እና በህጋዊ የውርስ ማስረጃ ሊስተናገድ ይችላል፡፡
• ተቋሙ በልዩ ሁኔታ ያስቀመጣቸው ደንበኞችን በተመለከተ ከሚመለከተው የመንግስት አካል መረጃ ከተገኘ በኋላ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
• በአጠቃላይ ቆጣሪው የሚተላለፍለት ወይም እንዲዛወርለት ያመለከተው ህጋዊ ወራሽ የሚጠበቅበትን ማስረጃ አሟልቶ ከቀረበ በ3 ቀናት ውስጥ አዲስ የውል ስምምነት ፈርሞ የስምምነቱን ቅጅ እንዲደርሰው ይደረጋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት