Get Mystery Box with random crypto!

በህገ-ወጥ መንገድ የተገጠሙ ቆጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ በአዲስ አበባ ከተማ ገርጂ ጎሮ አካባቢ | Ethiopian Electric Utility

በህገ-ወጥ መንገድ የተገጠሙ ቆጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በአዲስ አበባ ከተማ ገርጂ ጎሮ አካባቢ ልዩ ስሙ አሳማ እርባታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አስራ ሰባት ቆጣሪዎች በህገ-ወጥ መንገድ ተገጥመው ተገኝተዋል፡፡

በህገ-ወጥ መንገድ ተገጥመው የተገኙት ቆጣሪዎች ከነፍጆታቸው አጠቃላይ ግምት ከሶስት መቶ አርባ ሶስት ሺ ብር በላይ ነው፡፡

የምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ህግ ክፍል ከፖሊስ ጋር በመተባበር በህገ-ወጥ መንገድ የተገጠሙትን ቆጣሪዎች፣ኬብልና ምሰሶ ተነስቶ ወደ ተቋሙ ገቢ እንዲሆን አድርጓል፡፡

የአካባቢው ፖሊስ ህገ-ወጥ ተግባሩ ላይ ምርመራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et