Get Mystery Box with random crypto!

አገልግሎቱ የ10 ከተሞች የዲስትሪቢዩሽን ኔትወርክ ማሻሻያ ፕሮጀክት ሊያከናውን ነው ********* | Ethiopian Electric Utility

አገልግሎቱ የ10 ከተሞች የዲስትሪቢዩሽን ኔትወርክ ማሻሻያ ፕሮጀክት ሊያከናውን ነው
*****************
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ10 ከተሞች የዲስትሪቢዩሽን ኔትወርክ የማሻሻያ ፕሮጀክት ስራ ሊያከናውን ነው፡፡

ፕሮጀክቱ በነቀምት፣ አምቦ፣ አሶሳ፣ ቢሾፍቱ፣ ደብረብርሃን፣ ሱሉልታ፣ ጅጅጋ፣ ሆሳዕና፣ አሰላ እና ዲላ ከተሞች በሶስት ሎት ተከፍሎ የሚከናወን ይሆናል፡፡

በፕሮጀክቱ 1278 የመካከለኛ መስመር (15ኬ.ቪ) ማሻሻያ ግንባታና ነባር መስመሮችን የማንሳት እና 2168 ነባር የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮች ማሻሻያ ሥራ ይከናወናል፡፡

ስራው የሚከናወነው ከዓለም ባንክ በተገኘ 47 ሚሊየን 500 ዶላር የፋይናንስ ምንጭ እና 17 ሚሊየን 892 ሺህ 740 ብር በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተመደበ በጀት ነው፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በማሰራጫ መስመሮች ላይ የሚታየውን የኃይል መቆራረጥ፤ መዋዠቅንና ኃይል ማነስን በማሻሻል በከተሞቹ እያደገ የመጣውን የደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት በመጠንና በጥራት ለሟሟላት ያስችላል፡፡

በተጨማሪም አዳዲስ ደንበኞችን ማገናኘት የሚያስችል የኔትዎርክ አቅምን ይፈጥራል፣ የዲስትሪቢዩሽን የቴክኒካል ኃይል ብክነትን ይቀንሳል፣ በከተሞቹ በ100 ኪሎ ሜትር በመካከለኛ መስመሮች ላይ የሚታየውን አማካይ የመቆራረጥ ድግግሞሽ 45 በመቶ እንዲሁም በ100 ኪ.ሜ አማካይ የማቋረጥ ቆይታ 50 በመቶ ይቀንሳል፡፡

ፕሮጀክቱ በተያዘው በጀት አመት ተጀምሮ በ2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et