Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Electric Utility

የቴሌግራም ቻናል አርማ eeuethiopia — Ethiopian Electric Utility E
የቴሌግራም ቻናል አርማ eeuethiopia — Ethiopian Electric Utility
የሰርጥ አድራሻ: @eeuethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.11K
የሰርጥ መግለጫ

EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-03-11 16:23:23
በሶማሌ ክልል ስምንት ከተሞች የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኑ

በሶማሌ ክልል ስምንት የዞን እና ወረዳ ከተሞች የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለጸ።

የአገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑት ከተሞች ዶሎ፣ ቆረሃይ፣ ሸበሌና ፋፈን ዞኖች የሚገኙ ዋርዴር፣ ኩዱንቡር፣ ይዒብ፣ ገርሎጉበይ፣ ዋፍዱብ ኢልሓር፣ በራጂሳሌ እና አፉፍሌይ ናቸው ።

በኢትዮጵያ ኤልክትሪክ አገልግሎት የሶማሌ ክልልፕሮጀክት አስተዳደር ኃላፊ አቶ አሊ ሰዒድ ከመንግስት በተመደበ 200 ሚሊዮን ብር ባለፉት ስድስት ወራት የሙሉ ቀን የኤሌትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።

እንደ አቶ አሊ ሰዒድ ገለጻ 18 ትራስፎርመርም ፣ 207 ኪሎ ሜትር መስመር በመዘርጋት እና 2 ሺህ 217 ምሶሶ ተከላ ስራ ተከናውኗል።

የኃይል አቅርቦቱን በሌሎች 11 ከተሞች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል ብለዋል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ ይጎብኙ፡- http://www.eeu.gov.et
3.6K viewsedited  13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 14:45:15
ውድ ደንበኞቻችን #ነገ_ቅዳሜ_መጋቢት_02 ቀን 2015 ዓ.ም ዋናው መስሪያ ቤትን ጨምሮ የክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤቶች፣ ዲሰትሪክቶች እና በየደረጃው የሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ ይጎብኙ፡- http://www.eeu.gov.et
2.0K viewsedited  11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 09:28:55
የቅድመ ጥንቃቄ ማሳሰቢያ

ዕሁድ መጋቢት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 7፡00 ድረስ፤ በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ የጥገና ስራ ስለሚከናወን በአሰላ እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡

ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንን በመገንዘብ ከወዲሁ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ ይጎብኙ፡- http://www.eeu.gov.et
2.3K viewsedited  06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 12:20:08
አዲስ ሃይል ፈላጊ ደንበኞች ማሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

ውድ ደንበኛችን አዲስ ቆጣሪ ለማግኘት ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላችን ሲመጡ ከዚህ በታች የተገለፁትን ቅድመ ሁኔታዎች እንዲያሟሉ እንጠይቃለን፡፡
"ለነጠላ ፌዝ ቆጣሪ አዲስ ኃይል ጠያቂዎች "
• የአመልካቹ የቀበሌ መታወቂያ፣ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ፣
• አንድ ጉርድ ፎቶ /3በ4/፣
• የኪራይ ቤት ከሆነ ከባለቤቱ የተሰጠ የስምምነት ደብዳቤ፣
• ለኃይል ማሻሻያ ወይም ለተጨማሪ ቆጣሪ ከሆነ የኤሌክትሪክ ፍጆታ የመጨረሻ ክፍያ ደረሰኝ፣
• ጥያቄው ለሽርክና ማህበር ከሆነ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የሽርክና ማረጋገጫ ሰነድ ኮፒ፤
"ለሶስት ፌዝ እና ለከፍተኛ ኃይል ጠያቂዎች"
• የሃይል ጥያቄው ከ14 ኪሎ ዋት እና በላይ ከሆነ ከላይ ለነጠላ ፌዝ አገልግሎት ከተጠቀሱት ማስረጃዎች በተጨማሪ በኤሌክትሪክ ነክ ሥራዎች ፈቃድ ባለው ተቋራጭ የተሰራ የኤሌክትሪክ ዲዛይን ፕላን፣
• ክፍያዎች (በየጊዜው የሚደረገው የዋጋ ክለሳ እንደተጠበቀ ሆኖ አገልግልቱን ለመስጠት ለሚከናወኑ የኢንስፔክሽን እና ለማስገመቻ ፣
• ለባለ ሶስት ፌዝ ቆጣሪ 300 ብር፣
• ከ24 ኪሎ ዋት እስከ 120 ኪሎ ዋት 500 ብር፣
• ከ121 ኪሎ ዋት እስከ 1 ሜጋ ዋት 5000 ብር፣
• ከ 1 ሜጋ ዋት በላይ 10 ሺህ ብር ብር መክፈል ይጠበቅባችኋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ሙሉ መረጃውን ለማግኝት ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ:- http://www.ethiopianelectricutility.gov.et/.../getting...
3.8K viewsedited  09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 18:27:40
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በድምቀት ተከበረ

የኢትዮጵያ ኤሌከትሪክ አገልግሎት ዛሬ የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም በሃገር አቀፍ ደረጃ ለ47ኛ ጊዜ የሚከበረውን አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 በድምቀት አክብሯል፡፡

ክብረ በዓሉ የተከበረው “እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ቃል ሲሆን የኢትዮጵያ ኤሌከትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላን ጨምሮ የሰራተኛ ማህበር ሊቀ መንበር፣ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች፣ ሰራተኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው ዕንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በዕለቱ የተሻለ አፈጻፀም ያስመዘገቡ ሴት ሰራተኞች የዕውቅና የሰርተፍኬት እና የማበረታቻሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ ይጎብኙ፡- http://www.eeu.gov.et
2.0K views15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 09:53:14
ውድ የድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን፤ የተጠቀማችሁበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ቀላልና ምቹ በሆነው #የቴሌ_ብር መተግበሪያ ይክፈሉ፡፡ *127# አጭር ቁጥር በመጠቀም ብቻ ሳይጉላሉና ሳይንገላቱ የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ካሉበት ሆነው በቀላሉ ይክፈሉ፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ ይጎብኙ፡- http://www.eeu.gov.et
3.3K viewsedited  06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 11:23:41
የ25 የገጠር ከተሞች የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አፈጻፀም 24.1 በመቶ ደረሰ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፍትሃዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት እውን ለማድረግ በተቀረፀው ብሄራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፍኖተ ካርታ መሰረት ከዋናው ግሪድ ርቀው የሚገኙ 25 የገጠር ከተሞችን በፀሃይ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ ፕሮጀክት ቀርፆ በመንቀሳቀስ ላይ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ የገንዘብ ምንጭ የአፍሪካ ልማት ባንክና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሲሆኑ፤ አጠቃላይ ወጪው 20 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እና 161 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ነው፡፡

ፕሮጀክቱ በስምንት ክልሎች በተመረጡ የገጠር ከተሞች በመገንባት ላይ ሲሆን፤ በ6 ሎት ተከፍሎ በአራት ኮንትራክተሮች በመከናወን ላይ ነው፤ አጠቃላይ አፈጻፀሙም 24.1 በመቶ ደርሷል፡፡

በግንባታ 2.84 ኪ.ሜ የመካከለኛ ሃይል መስመር 16.91 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር እና 4 ትራንስፎርመሮች ተከላ ስራ ተከናውኗል፡፡

8 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ይህ ፕሮጀክት፤ 68 ነጥብ 7 የመካከለኛና 233 ነጥብ 3 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ይከናወንበታል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የዕውቀት ሽግግርንና ሰፊ የስራ ዕድል የሚፍጥር ሲሆን፤145 ሺህ 169 አዳዲስ ደንበኞችም የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡


#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ ይጎብኙ፡- http://www.eeu.gov.et
2.4K views08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 15:54:57 ቀልጣፋና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተግባራዊ እያደረገው በሚገኘው የሶስት አመት በስትራቴጂክ ዕቅድ መሰረት የተሳለጠ አገልግሎት ለደንበኞቹ ለመስጠት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ ገልፀዋል፡፡

ይህ የተገለፀው ዛሬ የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ተቋሙ ከቁልፍ ደንበኞችንና ባለድርሻ አካላትን ጋር በሂልተን ኢንተርናሽናል ሆቴል በተካሄደ የግማሽ ቀን ምክክር መድርክ ላይ ነው፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም ተግባራዊ እየተደረገ በሚገኘው ስትራቴጂ ዕቅድ መሰረት ለደንበኞች ቀልጣፋና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የመተግበር፣አገልግሎቱን የማስፋፋት፣ መሰረተ-ልማትን የማሻሻል የመሳሰሉ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የሀይል መቆራረጥና መዋዥቅ፣ የሰራተኞች ስነ-ምግባር ችግር፣ የመሰረተ ልማት ስርቆት፣ የአስቸኳይ ጥገና አገልግሎት መዘግየት፣ የንባብ ችግር፣ ለኢንዱስትሪ ደንበኞች ተገቢው ትኩረት አለመስጠት፣ የፓወር ፋከተር ኮሬክተር አጠቃቀም ችግር እና የማከፋፈያ ጣቢዎች አቅም መዳከም ችግር እንደሚስተዋል ጠቁመዋል፡፡

የተቋሙ ኃላፊዎች በበኩላቸው በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለማስወገድ የሚያስችሉ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን ዝርጋታ፣ አዲስ የጥሪ ማዕከል ግንባታ፣ የሰራተኞ የስነ-ምግባርና የአቅም ችግሮችን መቅርፍ፣ አዳዲስ የክፍያ አማራጮችን መዘርጋት፣ የማከፋፈያ ጣቢያዎችን አቅም የማሳደግ እና ሌሎች ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.5K viewsedited  12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 15:54:08
2.4K views12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 15:54:07
2.3K views12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ