2023-02-23 11:12:34
ከ116 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመካከለኛ መስመር መልሶ ግንባታና ማስፋፊያ ስራ እየተከናወነ ነው
የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ116 ሚሊየን ሦስት ሺህ 709 ብር በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ላይ የመካከለኛ መስመር መልሶ ግንባታና ማስፋፊያ ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
የመካከለኛ መስመር መልሶ ግንባታ የሚከናወነው ከሚሴ እስከ ቦሩ ሃራዋ፣ ከመሃልሜዳ እስከ ዘመሮ፣ ከባህር ዳር እስከ አዴት፣ ከሊብሶ ጎራርባ ወረቃሉ እስከ ዉርጌሳ፣ ከሐሮ እስከ ድሬሎቃ እና ከብቸና ሰብስቴሽን እስከ የዕድ ውሃ ባሉ አካባቢዎች በተዘረጉ መስመሮች ላይ ነው፡፡
እንዲሁም የመካከለኛ መስመር ማስፋፊያ ከኮምቦልቻ ሰብስቴሽን እስከ ካርቪኮ፣ ከሞጆ ሰብስቴሽን-እጀሬ፣ ከእጀሬ እስከ አረርቲ፣ ከጣና በለስ ሰብስቴሽን እስከ ቁንዝላ ባሉ ቦታዎች ላይ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ በሶስተኛ ወገን አማካኝነት እየተከናወነ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ 149 ነጥብ 95 በኪ.ሜ መዘርጋት ተችሏል፡፡
የመካከለኛ መስመር መልሶ ግንባታና ማስፋፊያ ስራ መከናወኑ በከተሞቹ ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አስተማማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት ከማድረጉም ባሻገር የማህበረሰቡን የእለት ተእለት ኑሮና የከተሞቹን የእድገት ለማሻሻል የሚያግዝ ፕሮጀክት ነው፡፡
በተጨማሪም ለኢንዱስትሪ፣ ለውሃ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ለሚሰጡ ተቋማት መስፋፋት አይነተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡
ከስድስት ወር በፊት የተጀመረው ይህ የመካከለኛ መስመር መልሶ ግንባታ ፕሮጀክት 72 ነጥብ 45 ፐርሰንት እንዲሁም የማስፋፊያ ስራው ደግሞ 86 ነጥብ 28 ፐርሰንት ተጠናቋል፡፡ በተያዘው በጀት አመትም ስራው ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ ይጎብኙ፡- http://www.eeu.gov.et
2.2K viewsedited 08:12