2023-02-16 09:10:39
የኤሌክትሪክ #አደጋን እንዴት መከላከል ይቻላል?
• ያልተሸፈነ የኤሌክትሪክ ገመድ ወይንም ሽቦ ከመንካት መቆጠብ፣
• የኤሌክትሪክ ሽቦዎች ከቆሮቆሮ አጥር፤ ከልብስ ማስጫ ሽቦዎች ጋር እንዳይገናኙ ማድረግ፣
• ተበጥሶ መሬት ላይ የወደቀን ወይንም የተንጠለጠለን ኤሌክትሪክ ሽቦ ከመንካት መቆጠብና ሪፖርት ማድረግ፣
• በኤሌክትሪክ የተያዘን ሰው ህይወት ከአደጋ ለማዳን የኤሌክትሪክ መስመሩን ከመቆጣጠሪያው ማጥፋት፣
• ውሃ ውስጥ፤ እርጥብ መሬትና ኤሌክትሪክ አስተላላፊ ነገር ላይ ቆሞ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎቹን ከመንካት መቆጠብ፣
• ማንኛውም በኤሌክትሪክ የሚሰራ መሳሪያን ለማጽዳትና ለመጠገን ሲያስፈልግ ከኤሌክትሪክ መስመር ማላቀቅ፣
• በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መሳሪያዎች ላይ ቃጠሎ ከተነሳ በውሃ ለማጥፋት አለመሞከር፣
• ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከአንድ ቤት ወደ ሌላ ቤት የሚዘረጋ የኤሌክትሪክ መስመር አደጋ ስለሚያስከትል ከዚህ ድርጊት መቆጠብ፣
• በማንኛውም ቦታና ጊዜ የኤሌክትሪክ አደጋ የሚያስከትል ምልክት ከታየ ወዲያውኑ በአቅራቢያው ለሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማሳወቅ፣
• የኤሌክትሪክ ስራ ሙያን የሚጠይቅ በመሆኑ በቸልተኝነት የሚሠራ ስራ ለህይወትም ሆነ ለንብረት መጥፋት መንስኤ ስለሚሆን መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
2.4K viewsedited 06:10