Get Mystery Box with random crypto!

የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት በተዘረጉባቸው አካባቢዎች ግንባታዎችን ማከናወን በህግ የሚያስቀጣ ከመሆኑ | Ethiopian Electric Utility

የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት በተዘረጉባቸው አካባቢዎች ግንባታዎችን ማከናወን በህግ የሚያስቀጣ ከመሆኑ በተጨማሪ ለሰዎች ህይወት መጥፋት፣ ለአካል መጉደል እና ለንብረት መውደም ምክንያት እየሆነና በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይም አሉታዊ ተፅኖ እያሳደረ ይገኛል፡፡

የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት በተዘረጋባቸው አካባቢ ግንባታዎችን ማከናወን፣ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎችን የአጥር አካል አድርጎ ማጠር፣ ንግድ ስራዎችን ማከናወን፣ ሙያዊ እውቀት በሌላቸው ግለሰቦች ማስጠገን፣ ጥራት የሌላቸው የኤሌክትሪክ መገልገያ መሳሪያዎችን መጠቀም፣ ማስታወቂያዎችን መለጠፍ እና ልብስ መስቀል ለከፍ የኤሌክትሪክ አደጋ ይዳርጋል፡፡

ስለሆነም መሰል ድርጊቶችን የምትፈፅሙ አካላት ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያሳሰብን ለኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት በተፈቀደ ወሰን ላይ ግንባታ በምታከናውኑ አካል ላይ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የምንገደድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et