Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ሃይል ፈላጊ ደንበኞች ማሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ውድ ደንበኛችን አዲስ ቆጣሪ ለማግኘ | Ethiopian Electric Utility

አዲስ ሃይል ፈላጊ ደንበኞች ማሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

ውድ ደንበኛችን አዲስ ቆጣሪ ለማግኘት ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላችን ሲመጡ ከዚህ በታች የተገለፁትን ቅድመ ሁኔታዎች እንዲያሟሉ እንጠይቃለን፡፡
"ለነጠላ ፌዝ ቆጣሪ አዲስ ኃይል ጠያቂዎች "
• የአመልካቹ የቀበሌ መታወቂያ፣ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ፣
• አንድ ጉርድ ፎቶ /3በ4/፣
• የኪራይ ቤት ከሆነ ከባለቤቱ የተሰጠ የስምምነት ደብዳቤ፣
• ለኃይል ማሻሻያ ወይም ለተጨማሪ ቆጣሪ ከሆነ የኤሌክትሪክ ፍጆታ የመጨረሻ ክፍያ ደረሰኝ፣
• ጥያቄው ለሽርክና ማህበር ከሆነ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የሽርክና ማረጋገጫ ሰነድ ኮፒ፤
"ለሶስት ፌዝ እና ለከፍተኛ ኃይል ጠያቂዎች"
• የሃይል ጥያቄው ከ14 ኪሎ ዋት እና በላይ ከሆነ ከላይ ለነጠላ ፌዝ አገልግሎት ከተጠቀሱት ማስረጃዎች በተጨማሪ በኤሌክትሪክ ነክ ሥራዎች ፈቃድ ባለው ተቋራጭ የተሰራ የኤሌክትሪክ ዲዛይን ፕላን፣
• ክፍያዎች (በየጊዜው የሚደረገው የዋጋ ክለሳ እንደተጠበቀ ሆኖ አገልግልቱን ለመስጠት ለሚከናወኑ የኢንስፔክሽን እና ለማስገመቻ ፣
• ለባለ ሶስት ፌዝ ቆጣሪ 300 ብር፣
• ከ24 ኪሎ ዋት እስከ 120 ኪሎ ዋት 500 ብር፣
• ከ121 ኪሎ ዋት እስከ 1 ሜጋ ዋት 5000 ብር፣
• ከ 1 ሜጋ ዋት በላይ 10 ሺህ ብር ብር መክፈል ይጠበቅባችኋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ሙሉ መረጃውን ለማግኝት ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ:- http://www.ethiopianelectricutility.gov.et/.../getting...