Get Mystery Box with random crypto!

የሐረር ማከፋፈያ ጣቢያ የማስፋፊያ ስራ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ በሐረር ቁጥር 2 የማከፋፈ | Ethiopian Electric Utility

የሐረር ማከፋፈያ ጣቢያ የማስፋፊያ ስራ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
በሐረር ቁጥር 2 የማከፋፈያ ጣቢያ ሲከናወን የነበረው የማስፋፊያ ስራ ተጠናቆ ጣቢያው በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
የማስፋፊያ ስራው የማከፋፈያ ጣቢያውን ኃይል የማከፋፈል አቅም በ5 ነጥብ 04 ሜ.ዋ ለማሳደግ ያግዛል፡፡

ለዚህም በጣቢያው አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩት ሶስት ባለ 6 ነጥብ 3 ኤም.ቪ.ኤ ፓወር ትራንስፎርመሮች በተጨማሪ በማስፋፊያ ስራው አንድ ባለ 6 ነጥብ 3 ኤም.ቪ.ኤ ፓወር ትንስፎርመር እንዲተከል ተደርጓል፡፡

የተከናወነው የማስፋፊያ ስራ ለሐረር ከተማ ኃይል በሚያሰራጩ ባለ 15 ኪ.ቮ መስመሮች ላይ ያለውን ጭነት የሚያቃልል ሲሆን በከተማው የሚከሰተውን የኃይል መቆራረጥ ችግርም የሚቀርፍ ይሆናል፡፡

የማከፋፈያ ጣቢያው ለሐረር ከተማ፣ ለድሬ ጠያራ፣ ባቢሌና ጉርሱም ወረዳዎች ኃይል የማከፋፈል አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም የባቢሌ የማከፋፈያ ጣቢያ የማስፋፊያ ስራ በቅርቡ ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት ስራ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን ስራው ሲጠናቀቅ በአካባቢው ያለውን የኃይል መቆራረጥ በከፍተኛ ደረጃ ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et