Get Mystery Box with random crypto!

በመጪው የትንሳዔ በዓል ሊከሰት የሚችለውን የኃይል መቆራረጥ ችግር ለመከላከል የተለያዩ የቅድመ ዝግ | Ethiopian Electric Utility

በመጪው የትንሳዔ በዓል ሊከሰት የሚችለውን የኃይል መቆራረጥ ችግር ለመከላከል የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በመጪው የትንሳዔ በዓል ላይ የኃይል መቆራረጥ እንዳያጋጥም ለማድረግ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን ዛሬ ባካሄዱት የጋራ ውይይት ገልፀዋል፡፡

በውይይቱም ከኃይል ማመንጫ ጀምሮ እስከ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችንና ትራንስፎርመሮች ብልሽቶች ሲያጋጥሙ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የጋራ ኮሚቴ መዋቀሩም ተመላክቷል፡፡

በዋዜማውና በበዓሉ ዕለት የኤሌክትሪክ ኃይል ሳይቆራረጥና ሳይዋዥቅ በተገቢው ሁኔታ ለማድረስና ችግሩ ከተከሰተም በአፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆናቸው ገልፀዋል፡፡

በውይይቱም በተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥ የሚስተዋልባቸውን አካባቢዎች በመለየት በመካከለኛና በዝቅተኛ መስመሮች ላይ ጭነት የማመጣጠንና የቅድመ መከላከልና የጥገና ስራዎችን በመሰራት ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከበዓሉ ጋር ተያይዞ በሚኖር የሃይል መጨናነቅ የኃይል መቆራረጥ ችግር እንዳያጋጥም ደንበኞች የኤሌክትሪክ ኃይል ጭነት በማይበዛበት ሰዓታት በተለይ ከምሽቱ 3፡00 እስከ ንጋቱ 11፡00 ባሉት ጊዜያት ቢጠቀሙ የተሻለ የኤሌክትሪክ ኃይል ከማግኘት ባለፈ የኤሌክትሪክ መቆራረጥን እንደሚቀንስ ተመላክቷል፡፡

ደንበኞች ከተቋሙ ጋር በተያያዘ ማንኛውንም መረጃዎች ለመጠየቅ፣ ጥቆማዎችና አስተያይቶች ለማቅረብ ወደ አቅራቢያቸው የሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በአካል ወይም ስልክ በመደወል እንዲሁም በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ያሉ ደንበኞች ደግሞ ወደ በ905 ነፃ የጥሪ ማዕከል በመደወል ማሳወቅ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት