Get Mystery Box with random crypto!

የኘሮግራም ጥቆማ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚያከናውናቸውን የስራ እንቅስቃሴዎች እና በ | Ethiopian Electric Utility

የኘሮግራም ጥቆማ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚያከናውናቸውን የስራ እንቅስቃሴዎች እና በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እየተከናወኑ የሚገኙትን የስራ እንቅስቃሴዎች ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅ ከዋልታ ሚዲያና ኮሙንኬሽን ኮርፖሬት ጋር በመተባበር #አውደ ኤሌክትሪክ የተሰኘ ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም በማዘጋጀት ሐሙስ ሚያዝያ 12 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 2:20 ጀምሮ ማስተላለፍ ይጀምራል፡፡

ስለሆነም ውድ ደንበኞቻችን ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ዘወትር ሐሙስ ከምሽቱ 2:20 እስከ 2:40 በዋልታ ቴሌቪዥን እንድትከታተሉ በአክብሮት እንጋብዛለን።


#የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et