Get Mystery Box with random crypto!

ውድ #የድህረ_ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኛችን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታዎን በቴሌ ብር ለመክፈል የሚከተሉ | Ethiopian Electric Utility

ውድ #የድህረ_ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኛችን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታዎን በቴሌ ብር ለመክፈል የሚከተሉትን ቅደም ተከተሎች ይጠቀሙ

በመጀመሪያ ወደ *127# በመደውል የቴሌ ብር ደንበኛ ይሁኑ፤ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆኑ ካረጋገጡ በኋላ ከታች ያለውን መመሪያዎች ይጠቀሙ፡፡

1. መልሰው ወደ *127# ይደውሉ፣
2. ከሚያመጣሎት መዘርዝር # በማስገባት ምላሽ ይስጡ፣
3. በመቀጠል ቁጥር 8 በማስገባት በቴሌ ብር ለመክፈል ብለው ምላሽ ይስጡ፣
4. በቴሌ ብር ለመክፈል በሚል ዝርዝር ከሚቀርብሎት መዘርዘር የአገልግሎት ክፍያ ለመፈፀም የሚለውን አማራጭ ቁጥር 2 ይምረጡ፣
5. በድርጅት ስም የሚለውን ለመምረጥ 1ን ያስገባሉ፣
6. 1ን በማስገባት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚለውን ይምረጡ፣
7. ከዛም የውል ቁጥሮን ማለትም ደረሰኝዎ ላይ ያለውን /Contract Account Number/ (10000*******) የሚለውን ያስገቡ፣
8. ለማረጋገጥ 1ን የሚለውን ያስገቡ፣
9. ምክንያትዎን ያስገቡ፣
10. በመጨረሻም የሚስጥር ቁጥርዎን ያስገባሉ፣

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት