Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Electric Utility

የቴሌግራም ቻናል አርማ eeuethiopia — Ethiopian Electric Utility E
የቴሌግራም ቻናል አርማ eeuethiopia — Ethiopian Electric Utility
የሰርጥ አድራሻ: @eeuethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.11K
የሰርጥ መግለጫ

EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-15 09:44:44
ውድ ደንበኞቻችን፤ የተጠቀማችሁበትን የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በተዘረጉ የክፍያ አማራጮች በመጠቀም ይፈፅሙ፡፡ #ዘመናዊ የክፍያ አማራጮችን ሲጠቀሙ አስፈላጊ ካልሆነ ወጪና እንግልት ያድናል! ኑሮንም ያቃልላል! በጥሬ ገንዘብ ለመክፈል ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በመምጣት ጊዜዎትን፣ ጉልበትዎትንና ገንዘብዎትን አያባክኑ፡፡ ካሉበት ሆነው በተዘረጉ ቀላልና ዘመናዊ የክፍያ አማራጭ ብቻ ይጠቀሙ!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ ይመልከቱ፡ http://www.eeu.gov.et
4.6K viewsedited  06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 11:52:26
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ንብረት የሆኑ የተለያዩ ያገለገሉ 118 ተሸከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታ መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ ይመልከቱ፡ http://www.eeu.gov.et
5.3K views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 10:44:18
የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥን ስለማሳወቅ

በዳውርና ኮንታ ዞኖች ላይ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ የኤሌክትሪክ ኃይል ሲያስተላልፍ የነበረው የአባ ሰብስቴሽን ትራንስሚሽን መስመር ከትናንት ምሽት ጀምሮ በመበላሸቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል፡፡

በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን ያጋጠመውን ብልሽት ለማስተካከል በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ጥረት እየተደረገ ሲሆን ችግሩ ተቀርፎ መደበኛው አገልግሎት እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ በአክብሮት እናሳውቃለን።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
4.7K viewsedited  07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 14:01:11 በክልሉ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት በክልሉ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርግ የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ገ/መድህን ገለፁ፡፡

በክልሉ በተካሄደው ጦርነት በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ቢሆንም ችግሮችን በመቋቋም አገልግሎቱ እንዳይቋረጥ ለማድረግ ክፍተኛ ጥረት ተደርጓል ብለዋል፡፡

በዚህ በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራትም ስድስት ሺ በላይ አዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ስራ አስፈፃሚው ገልፀው ከኃይል ሽያጭ ገቢ 230 ሚሊዮን 585 ሺ 358 ብር እንዲሁም ከልዩ ልዩ ገቢ ደግሞ 102 ሚሊዮን 805 ሺ 811 ብር መሰብሰቡን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም በነበረው ውስን ግብዓት ጉዳት የደረሰባቸውን የኤሌክትሪክ መስመሮች ለማሻሻል የኮንክሪት ምሰሶ ተከላ ማከናወን፣ የተቋረጠውን የሲስተም አሰራር ለማስቀጠል የዝግጅት ስራ ማከናወን፣ የማስፋፊያ ግንባታ ማከናወን፣ በሶስት የገጠር መንደሮች የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት መገንባት የመሳሰሉ ስራዎች አቅም በፈቀደ መጠን ለማከናወን ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ በክልሉ አንፃራዊ ሰላም በመስፈኑ በሚቀጥለው ጊዜ ባለፉት ዓመታት የተፈጠረውን ክፍተት ሊያካክስ የሚችል ስራ ለማከናወን ጥረት ይደረጋል ያሉት አቶ መስፍን በአሁኑ ወቅት የክልሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ የሚያጠና በዋናው ቢሮ የተዋቀረ የቴክኒክ ቡድን ስራ መጀመሩንም ጠቁመዋል፡፡

አክለውም በቀጣይ የአገልግሎቱን ማዕከላት ሙሉ በሙሉ መልሶ በሲስተም ማስተሳሰር፣ ከሲስተም ውጪ ሲሰሩ የነበሩትን ስራዎች ወደ ሲስተም መመለስ፣ የሰው ሀይሉን ክፍተቶች መሙላት፣ የተቋሙን አዲስ መመሪያዎች፣ አደረጃጀት ወዘተ ተግባራዊ ማድረግ የመሳሰሉ ስራዎች የሚከናወኑ ይሆናል ብለዋል፡፡

እንዲሁም ተቋርጠው የነበሩ የመልሶ ግንባታ፣ የገጠር የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግንባታ፣ ከዋና መስመር ርቀው በሚገኙ አካባቢዎች አነስተኛ የኃይል አማራጮች ግንባታ፣ ሶስት ሺ ቆጣሪዎችን በስማርት ቆጣሪዎች መቀየር፣ የተጎዱ ቢሮዎች ጥገናና ግንባታ፣ የመካከለኛ መስመር ማሻሻያ፣ አዲስ ደንበኛ የማገናኘት ወዘተ አንኳር ስራዎች ይከናወናሉ ሲሉ ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም በክልሉ ያለውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ለሚደረገው ጥረት ሁሉም አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
7.7K viewsedited  11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 14:01:06
6.2K views11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 09:39:29
ውድ የድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን በየትኛውም ቦታ ሆነው በተቀመጠው የመክፈያ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብዎን በቀላሉ በቴሌ ብር፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል በሲቢኢ ብር፣ በሞባይል ባንኪንግ ወይም በኢንተርኔት ባንኪንግ ይፈፅሙ! ጊዜዎትንና ጉልበትዎንም ይቆጥቡ!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
7.8K views06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 17:03:16
የኤሌክትሪክ ኃይል መሙያ ካርድ ሲጠፋም ሆነ ሲበላሽ ምን መደረግ አለበት?

የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ አገልግሎት በአሁኑ ወቅት ካሉት አጠቃላይ ደንበኞች መካከል 20 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆኑት የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ናቸው፡፡

እነዚህ ደንበኞቻችን የሚገለገሉበት የኤሌክትሪክ ኃይል መሙያ ካርድ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ሲጠፋባቸው አለያም ሲበላሽባቸው ይስተዋላል፡፡

ክቡራን ደንበኞቻችን ይህ ችግር ሲያጋጥምዎ በመጨረሻ ጊዜ የከፈሉበትን ደረሰኝ ወይም ከተቋሙ ጋር ውል የተፈራረሙበትን ማስረጃ በመያዝ አቅራቢዎ ወደሚገኝ ማዕከል በመሄድ አስፈላጊውን ክፍያ በመፈፀም ምትክ ካርድ ማግኘት ይችላሉ፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
5.7K views14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 21:17:53 በታወር ስርቆት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት

ዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ከቆቃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለኢላላ ገዳ ማከፋፈያ ጣቢያ እና ለቢሾፍቱ ቁጥር 2 ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የኤሌክትሪክ ኃይል በሚሰጠው ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ተሸካሚ መስመር የብረት ታወር ላይ ስርቆት ተፈፀሟል።

በስርቆቱ ምክንያት ታወሩ በመውደቁ በአዱላላ ፣ በድሬ ከተሞችና አከባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ተቋርጧል።

ያጋጠመውን ብልሽት ለማስተካከል በኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ጥረት እየተደረገ ሲሆን ችግሩ ተቀርፎ መደበኛው አገልግሎት እስኪመለስ ድረስ ክቡሯን ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁ በአክብሮት እናሳውቃለን።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
5.5K viewsedited  18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 21:16:29
5.1K views18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 21:15:59 የቅድመ ጥንቃቄ ማሳሰቢያ

ግንቦት 02 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለ72 ሰዓታት የከፍተኛ መስመር የማሻሻያ ስራ ስለሚከናወን በሶዶ ከተማ፣ ቦዲቲ ከተማና አካባቢው፣ ሁምቦ ከተማና አካባቢው፣ በዴሳ ከተማና አካባቢው፣ ብላቴ ጦር ካምፕ፣ ጉልጉላና ሆቢቻ ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚቋረጥ ይሆናል።

በመሆኑም ከላይ በተገለጹት አካባቢዎች የምትገኙ ደንበኞቻችን ከወዲሁ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
5.0K viewsedited  18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ