Get Mystery Box with random crypto!

በታወር ስርቆት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት ዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ከቆቃ ኃይ | Ethiopian Electric Utility

በታወር ስርቆት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት

ዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ከቆቃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለኢላላ ገዳ ማከፋፈያ ጣቢያ እና ለቢሾፍቱ ቁጥር 2 ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የኤሌክትሪክ ኃይል በሚሰጠው ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ተሸካሚ መስመር የብረት ታወር ላይ ስርቆት ተፈፀሟል።

በስርቆቱ ምክንያት ታወሩ በመውደቁ በአዱላላ ፣ በድሬ ከተሞችና አከባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ተቋርጧል።

ያጋጠመውን ብልሽት ለማስተካከል በኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ጥረት እየተደረገ ሲሆን ችግሩ ተቀርፎ መደበኛው አገልግሎት እስኪመለስ ድረስ ክቡሯን ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁ በአክብሮት እናሳውቃለን።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et