Get Mystery Box with random crypto!

የኤሌክትሪክ ኃይል መሙያ ካርድ ሲጠፋም ሆነ ሲበላሽ ምን መደረግ አለበት? የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ | Ethiopian Electric Utility

የኤሌክትሪክ ኃይል መሙያ ካርድ ሲጠፋም ሆነ ሲበላሽ ምን መደረግ አለበት?

የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ አገልግሎት በአሁኑ ወቅት ካሉት አጠቃላይ ደንበኞች መካከል 20 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆኑት የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ናቸው፡፡

እነዚህ ደንበኞቻችን የሚገለገሉበት የኤሌክትሪክ ኃይል መሙያ ካርድ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ሲጠፋባቸው አለያም ሲበላሽባቸው ይስተዋላል፡፡

ክቡራን ደንበኞቻችን ይህ ችግር ሲያጋጥምዎ በመጨረሻ ጊዜ የከፈሉበትን ደረሰኝ ወይም ከተቋሙ ጋር ውል የተፈራረሙበትን ማስረጃ በመያዝ አቅራቢዎ ወደሚገኝ ማዕከል በመሄድ አስፈላጊውን ክፍያ በመፈፀም ምትክ ካርድ ማግኘት ይችላሉ፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት