Get Mystery Box with random crypto!

400 አባወራዎችን ተጠቃሚ ለሚያደርግ የመስኖ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ዝርጋታ ስራ ተከ | Ethiopian Electric Utility

400 አባወራዎችን ተጠቃሚ ለሚያደርግ የመስኖ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ዝርጋታ ስራ ተከናወነ

በሀረሪ ክልል 400 አባወራዎችን ተጠቃሚ ለሚያደርግ የመስኖ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራ ተከናወነ፡፡

በ9 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የተገነባው ይህ ኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ወጪው ሙሉ በሙሉ የተሸፈነው በሀረሪ ክልል መንግስት ነው፡፡ በግንባታው 1.2 ኪሜ ከፍተኛ መስመር እና 9.1 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ስራ ተከናውኗል፡፡

የኤሌክትሪክ መስመሩ በመገንባቱ የአካባቢውን ልማት በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግና ለማዘመን እንደሚያግዝ የአካባቢው አርሶ አደሮች ገልፀዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በአካባቢው ያለውን የውሀ ሀብት ለማልማት የሚያስችል ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአካባቢው እየተመረተ ያለውን የእህል ሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት በከፍተኛ ደረጃ የሚጨምር ነው፡፡
ፕሮጅክቱም ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በቅርቡ ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡


#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et