Get Mystery Box with random crypto!

በመዲናዋ ለሁለት ሳምንታት ተከስቶ የነበረው የሃይል መቆራረጥ ችግር በተደረገው ጥገና ወደነበረበት | Ethiopian Electric Utility

በመዲናዋ ለሁለት ሳምንታት ተከስቶ የነበረው የሃይል መቆራረጥ ችግር በተደረገው ጥገና ወደነበረበት መመለሱ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ከተማ ለሁለት ሳምንታት ተከስቶ የቆው የሃይል መቆራረጥ ችግር በተደረገው አፋጣኝ ጥገና አገልግሎቱ ወደ ነበረበት መመለሱን የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ ገበየሁ ሊካሳ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

ስራ አስፈጻሚው ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ባለፉት ሁለት ሳመንታት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በግንባታ ፕሮጀክቶች፣ በአረጁ መስመሮች ላይ በደረሰ ጉዳት በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የሃይል መቆራረጥ ችግር ሲያጋጥም መቆየቱን ገልፀው ለተፈጠረው ችግርም ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

ችግሩን ለመፋታት በተደረገ ርብርብ ፈጣን ጥገናዎችን በማካሄድ አገልግሎቱን ወደነበረበት መመለስ መቻሉን እና በአንዳንድ የሃይል መቆራረጥ ችግር በሚስተዋልባቸውን መስመሮችንና የማከፋፈያ ጣቢያዎች የመጠገንና የግንባታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገበየሁ ሊካሳ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et