Get Mystery Box with random crypto!

በኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማት ላይ በተፈፀመ ውደመት የሃይል አቅርቦት ተቋርጧል በደቡብ ምዕራብ | Ethiopian Electric Utility

በኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማት ላይ በተፈፀመ ውደመት የሃይል አቅርቦት ተቋርጧል

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከቦንጋ የኤሌክትሪክ ሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ /ሰብስቴሽን/ በመነሳት ለጠሎ ወረዳ እና አጎራባች አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው 33Kv ከፍተኛ መስመር ተሸካሚ መስመር በህገ ወጦቹ በመውደሙ አካባቢው ለጨለማ ተዳርጓል።

ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን በተከሰተው ችግር ምክንያት ለተቋረጠው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ይቅርታ እየጠየቅን ስራው ተሰርቶ ወደነበረበት እስከሚመለስ ድረስ አማራጭ የኃይል ምንጮችን በመጠቀም በትዕግስት እንድትጠባበቁ እንጠይቃለን።

ከዚህ በተጨማሪ ወረዳው ተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ስርቆት የሚፈፀምበት በመሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶችን እንደራሱ ንብረት አድርጎ ሊጠብቅና ወንጀለኞቹን አድኖ በመያዝ ለፀጥታ አካላት በማቅረብ ህገ-ወጦችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የበኩሉን አስተዋፆ ሊያበረክት ይገባል እንላለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ለበለጠ መረጃ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et