Get Mystery Box with random crypto!

ከአራት ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የራዲዮ ኮሙዩንኬሽን ፕሮጀክት ስራ በመከናወን ላይ ነው የ | Ethiopian Electric Utility

ከአራት ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የራዲዮ ኮሙዩንኬሽን ፕሮጀክት ስራ በመከናወን ላይ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የውስጥ እና የውጭ አሰራሩን ለማሻሻል የሚያግዝ የሁለተኛው ምዕራፍ የዲጅታል የራዲዮ ኮሙዩንኬሽን ፕሮጀክት ትግበራ በ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በሆነ ወጪ በመከናወን ላይ ነው፡፡

የሬዲዮ ኮሙዩኒኬሽን ፕሮጀክቱ የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴና የአስቸኳይ ጥገና ስራ ቀልጣፋ ለማድረግ፣ ከማከፋፈያ ጣቢያ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሳለጥ፣ በግንኙነት ክፍተት ሊፈጠሩ የሚችሉ የንብረት እና የሰው አደጋ ለመቀነስ የሚያግዝ ነው፡፡

በተጨማሪም አገልግሎቱ በየደረጃው ያሉ የስራ መሪዎች ስራ ለመምራትና መልዕክት ለማስተላለፍ፣ ችግር ሲያጋጥም በቀጥታ ገብቶ የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ፣ የሰራተኞችን እና የደንበኞችን ደህንነት ለመጠበቅ እና ከከፍተኛ መስመር ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችንም ቀድሞ ለመከላከል ያስችላል፡፡

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ምስፈንጠሪየውን ይጫኑ http://www.ethiopianelectricutility.gov.et/news/detail/484