Get Mystery Box with random crypto!

በብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት በጋምቤላ ከተማ ንፋስ ቀላቀቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ | Ethiopian Electric Utility

በብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት

በጋምቤላ ከተማ ንፋስ ቀላቀቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ከጋምቤላ ተነስቶ ለደምብዶሎ ኃይል ማሰረጫ ኃይል የሚሰጥ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ፡- ደምብዶሎ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ቄሌም ወለጋ ዞን ስር የሚገኙ ቦታዎች ደምቢዶሎ፣ ሙጊ፣ ሀዋ ገላን፣ መቻራ፣ ጫንቃ፣ ቃቄ፣ ቄቤ፣ ጅማ ሆሮ ከተሞችና በአካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል፡፡

ስለሆነም በተጠቀሱ ቦታዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን አገልግሎቱን ወደ ቦታው ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አውቃችሁ፤ የጥገና ስራው ተጠናቆ ወደ መደበኛ አገልግሎቱ እስከሚመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠባበቁ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ ይመልከቱ፡ http://www.eeu.gov.et