Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ሺ 609 የገጠር ቀበሌ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኑ በአማራ ክልል ኤሌክ | Ethiopian Electric Utility

አንድ ሺ 609 የገጠር ቀበሌ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኑ

በአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም በደብረ ብርሀን ዲስትሪክት ማስተባበሪያ ቢሮ ስር የሚገኙ አንድ ሺ 609 የአምስት የገጠር ቀበሌ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኑ፡፡

የደብረ ብርሀን ማስተባበሪያ ቢሮ በ2015 በጀት ዓመት ስምንት የገጠር ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ አቅዶ 5 ቀበሌዎችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን ካለፈው ዓመት ያልተጠናቀቁ 11 ቀበሌዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 16 ቀበሌዎችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል፡፡

አገልግሎቱን ተደራሽ ለማደፍረግ 208 ነጥብ 69 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመርና 103 ነጥብ 26 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ የተከናወነ ሲሆን 31 የተለያየ አቅም ያላቸው ትራንስፎርመሮች የተከላ ስራ ተከናውኗል፡፡

ያልተጠናቀቁ የሶስት ቀበሌዎች ግንባታን በቅርቡ በማጠናቀቅ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው።

የግንባታ ስራው በሚከናወንበት ወቅት መሰረተ ልማቱን ከስርቆት በመጠበቅ ረገድ የአካባቢው ህብረተሰብ ያበረከተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ማስተባበሪያ ቢሮው ገልፆ በቀጣይም ይህንን በጎ ስራ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲል አሳስቧል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ ይመልከቱ፡ http://www.eeu.gov.et