Get Mystery Box with random crypto!

በአካል፣ በንበረትና በህይወት ላይ ሊደርስ የሚችለውን #የኤሌክትሪክ አደጋ እንዴት መከላከል እንችላ | Ethiopian Electric Utility

በአካል፣ በንበረትና በህይወት ላይ ሊደርስ የሚችለውን #የኤሌክትሪክ አደጋ እንዴት መከላከል እንችላለ?

ኤሌክትሪክ አስፈላጊ የመሆኑን ያክል በአጠቃቀም ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ ካላደረገ ህይወትን ወይም ንብረትን በቅፅበት ሊያሳጣ ይችላል፡፡ ከዚህ በታቸ የተዘረዘሩት ለኤሌክትሪክ አደጋ መከሰት ምክንያት ስለሚሆኑ መሰል ተግባራትን ከማከናወን መቆጠብ ያስፍልጋል፡፡

• በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች አቅራቢያ ልጆች ጨዋታ እንዲጫወቱ ከመፍቀድ፣
• በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች አቅራቢያ በጣም ተጠግቶ የንግድ ሥራዎች ከማከናወን፣
• በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች በዕርጥብ ጨርቅ ወይም በእንጨት ከመነካካት፣
• ያልተሸፈነ መስመር በብረት ወይም በእርጥብ እንጨት መነካካትና ከማገናኘት፣
• እሳት ሲፈጠር ለሚመለከተዉ አካል በአፋጣኝ ከማሳወቅ ይልቅ በእንጨት፣ በውሀ፣ በአፈር በብረት ወዘተ…..ለማጥፋት ከመሞከር፣
•የኤሌክትሪክ መስመር ሲበጠስ፣ ምሰሶ ሲወድቅ ወዲያዉኑ ለሚመለከተው አካል ከማሳወቅ ይልቅ በእንጨት፣ በብረት ለማንሳት መሞከር ለአደጋ ይዳርጋል፡፡ ስለሆነም ሁላችንም ይህንን ተገንዝበን መሰል ተግባራትን ከማከናወን እንድንቆጠብና ራሳችን እንዲሁም በዙሪያችን ያሉትን ሁሉ ከአደጋ ልንጠብቅ ይገባል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et