Get Mystery Box with random crypto!

በትረማርያም አበባው

የቴሌግራም ቻናል አርማ betremariyamabebaw — በትረማርያም አበባው
የቴሌግራም ቻናል አርማ betremariyamabebaw — በትረማርያም አበባው
የሰርጥ አድራሻ: @betremariyamabebaw
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.25K
የሰርጥ መግለጫ

አቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-23 12:38:19
1.6K views09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 12:03:07
_____መምህር ሐዋዝ ሐጎስ____
ከጦርነቱ ወዲህ የኔታን ማግኘት አልቻልኩም። ቅኔን ያስተማሩኝ እሳቸው ነበሩ። የታላቁ ገዳም የደብረ ሊባኖስ ገዳም የቅኔ መምህር ነበሩ። ከጦርነቱ በፊት ወደክፍለ ሀገራቸው ወደ ትግራይ ከሄዱ በኋላ በኋላ ስልካቸውም ጠፋኝ እሳቸውም ጠፉኝ። ይደውሉልኝ ነበረ።

የኔታ ጸሎትን የሚያበዙ ደግ መምህር ናቸው። ይህ ክፉ ጦርነት አልፎ ወደፊት እንደምንገናኝ ተስፋ አደርጋለሁ። ኢትዮጵያን ወደ መቀመቅ የከተታት ጦርነት በታሪክ በክፉ ሲወሳ ይኖራል። የሀገራችንን ቀውስ ያበዛነው እኛ ልጆቿ ነን። ሁሉም ራስ ወዳድ ነው። ለሀገር ለእውነት ለፍቅር የሚቆም የለም። በሌላው ጉዳት መጠቀምን የሚፈልጉ ፖለቲከኞች ሀገራችንን አደቀቋት። የሀገር መሪ ሆነው ለተወለዱበት ክልል የሚሠሩ ድኩማን ለዚህ አበቁን።

ሀገራችንን ማዳን ከሁላችንም ይጠበቃል።
1.6K views09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 11:28:08 __የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፭__
#ትእዛዝ #ሲኖዶስ
ትእዛዝ ፵፪:- ከካህናት መካከል ከኃድያንን ከመፍራት የተነሣ ቢክድ የካደው የክርስቶስን ስም ከሆነ ይባረር። የካደው ክህነትን ከሆነ ይሻር። ንስሓ ከገባ ይቀበሉት እንደ ሕዝብ ሆኖም ይግባ።

ትእዛዝ ፵፫:- ከካህናት አንዱ ደም ያለው ወይም ያልታረደ ወይም አውሬ የነከሰው ወይም በክት ከበላ ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነም ይለይ።

ትእዛዝ ፵፬:- ከቀዳም ስዑር በስተቀር በሰንበትና በዕለተ እሑድ ከካህናት መካከል አንዱ ሲጾም ቢገኝ ይሻር።

ትእዛዝ ፵፭:- ከካህናት መካከል በከኃድያን ቦታ ይጸልይ ዘንድ ቢገባ ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነም ይባረር።

ትእዛዝ ፵፮:- ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ሁለት ጊዜ ተሹሞ ቢገኝ እርሱም የሾመውም ይሻር።

ትእዛዝ ፵፯:- ደዌ ሕመም ካልከለከለው በስተቀር ጾመ አርብዓን፣ ረቡዕና ዓርብን የማይጾም ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ወይም አናጉንስጢስ ወይም መዘምር ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነ ደግሞ ይባረር።

ትእዛዝ ፵፰:- ከካህናት አንዱ ከአይሁድ ጋር ቢጾም ወይም ፋሲካን ከእነርሱ ጋር ቢያደርግ ወይም ለበዓላቸው ስጦታ ቂጣ ቢቀበል ወይም ይህን የመሰለ ቢያደርግ ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነ ይባረር። ሕዝባዊ ሆኖ ዘይትና መብራት ወደ አይሁድ ምኵራብና ወደ አሕዛብ ምኵራብ ቢወስድ ከምእመንነቱ ይሻር።

ትእዛዝ ፵፱:- የተሾመ ካህን ከቤተክርስቲያን ሠም ወይም ቅባት ቢሰርቅ ይባረር። የሰረቀውንም አምስት እጥፍ አድርጎ ይክፈል።

ትእዛዝ ፶፩:- በኤጲስ ቆጶስ ላይ የከኃድያንን ምስክርነትና የአንድን ኤጲስ ቆጶስ ምስክርነት አይስሙበት። ኤጲስ ቆጶስነትን ይዋረሱ ዘንድ ትክክል አይደለም። ኤጲስ ቆጶስ የቤተክርስቲያንን ሀብት ለፈለገው ሰው አይስጥ። አንድ ዓይኑ የታወረ ወይም አንድ እግሩ አንካሳ የሆነ ሰው ኤጲስ ቆጶስነት የሚገባው ቢሆን ይሾም። ነውረ ነፍስ እንጂ ነውረ ሥጋ አያረክስምና። መስማት የተሳነውና ዐይነ ስውር ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ አይሾም።

ትእዛዝ ፶፪:- ጋኔን ያደረበት ካህን ሆኖ አይሾም። ከምእመናን ጋርም አብሮ አይጸልይ።ጌቶቹ እንዳያዝኑ ነጻ ያልወጣ ሰው ካህን ሆኖ ይሾም ዘንድ አናዝም።

ትእዛዝ ፶፫:- ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ዓለማዊ ሹመትንና ክህነትን ሁለቱን ለመሥራት ወታደር ሆኖ ማገልገል ቢፈልግ ይሻር። [መንግሥትነት] ንጉሥን ወይም መኮንንን የሚያቃልል ይበቀሉት። ካህን ከሆነ ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነ ደግሞ ይባረር።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፮ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
1.6K views08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 09:36:49 __የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፬__
#ትእዛዝ #ሲኖዶስ
ትእዛዝ ፳:- ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን መማለጃ በመስጠት የሹመት መዓርግ ቢይዝ ይሻር። የሾመውም ይሻር። ከክህነት ሥርዓትም እስከ መጨረሻው ይባረር።

ትእዛዝ ፳፩:- ኤጲስ ቆጶስ ቤተክርስቲያንን በዚህ ዓለም የአገዛዝ ሥርዓት ለመግዛት የሚፈልግን ሰው ከረዳ ይሻር።

ትእዛዝ ፳፪:- ቄስ ኤጲስ ቆጶስን ቢንቅ ይለይ።

ትእዛዝ ፳፫:- ኤጲስ ቆጶስ ያባረረውን ቄስ ወይም ዲያቆን ራሱ ካልፈቀደ በስተቀር ሌላ ኤጲስ ቆጶስ እንዲመለስ አያድርገው።

ትእዛዝ ፳፬:- ሊቀ ጳጳሳት የሁሉንም ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶሳት ያውቅ ዘንድ ይገባል።

ትእዛዝ ፳፭:- ኤጲስ ቆጶስ የሀገረ ስብከቱ ኤጲስ ቆጶስ ካልፈቀደለት የእርሱ ባልሆነ ሀገረ ስብከት ላይ ለመሾም አይደፋፈር። ተደፋፍሮ የተገኘ ካለ እርሱም የሾማቸውም ይሻሩ።

ትእዛዝ ፳፯:- የኤጲስ ቆጶሳት ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ ይደረግ። በቤተክርስቲያን ላይ ስለአለ ስሕተትና እንቅፋት ስለሚሆኑ ነገሮችም ይተርጕሙ። የመጀመሪያው ጉባኤ በበዓለ ኃምሳ መካከል ይሁን። ሁለተኛው ጉባኤ ጥቅምት 12 ይሁን።

ትእዛዝ ፳፰:- ኤጲስ ቆጶስ የእግዚአብሔርን ገንዘብ ለዘመዱ ልጆች መስጠት የለበትም።

ትእዛዝ ፳፱:- ከቀሳውስት ወይም ከዲያቆናት ማንም ኤጲስ ቆጶሱን ሳያማክር ምንም አያድርግ።

ትእዛዝ ፴፩ [የጦር ሠራዊት]:- የንጉሥ ሠራዊትም ከጠላት ጋር ጦርነት የሚያደርጉት በራሳቸው ምግብ አይደለም።

ትእዛዝ ፴፪:- ወደ ጭፈራ ቤት የሚሔድና የሚዞር ስካርም የሚያበዛ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ይተው። አልተውም ካለ ግን ይባረር። ሕዝባውያንም ቢሆኑ እንደዚሁ ይሁኑ።

ትእዛዝ ፴፫:- ወደ ከኃድያን ጥምቀት ወይም ወደ ቁርባናቸው የሚሔድ ካህን ይሻር።

ትእዛዝ ፴፬:- ሥጋ መብላት፣ ጋብቻ፣ ወይን መጠጣት እንደ ርኩስ የሚቆጥር ቢኖር ይህን ሐሳቡን ይተው ዘንድ ይንገሩት። ካልተወ ግን ይሻር። ሕዝባዊ ቢሆንም እንዲሁ ይደረግ።

ትእዛዝ ፴፭:- ከኃጢአት ንስሓ የሚገቡትን አልቀበልም የሚል ካህን ቢኖር ይሻር።

ትእዛዝ ፴፯:- ከካህናት መካከል በገበያ የሚበላ ወይም የሚጠጣ ቢገኝ ከካህናት አንድነት ይለይ። ከካህናት መካከል አንዱ ኤጲስ ቆጶስን ቢሳደብ ይሻር። በሕዝብ ላይ በተሾመ ሰው ላይ መጥፎ ቃል አትናገር ይላልና። ቄስን ዲያቆንን የሚሳደብም ይባረር።

ትእዛዝ ፴፰:- ካህናትን ወይም ሕዝብን የሚንቅና የእግዚአብሔርን መልእክት የማያስተምር ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ይባረር። በንቀቱ ቢቀጥልበት ይሻር።

ትእዛዝ ፴፱:- ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ከካህናት የተቸገረን አይቶ ቸል ቸል ካለ የሚፈልገውን ነገርም ባይሰጠው ይለይ። በዚሁ በቸልታው ከቀጠለም ወንድሙን እንደገደለ ይቆጠራልና ይሻር።

ትእዛዝ ፵:- ከኃድያን በውሸት የጻፉትን መጽሐፍ ያሳየ ሕዝብንና ካህናትንም ለማጥመድ እንደ ቅዱሳት መጻሕፍት ቆጥሮ ወደ ቤተክርስቲያን ያስገባ ሰው ቢኖር ይሻር።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፭ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
1.9K views06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 17:58:15 _የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፫____
#ትእዛዝ #ሲኖዶስ
ትእዛዝ ፩:- ኤጲስ ቆጶስ ሁለት ወይም ሦስት ኤጲስ ቆጶሳት በተገኙበት ይሾም። ቄስ ዲያቆንና የቀሩት ሹማምንት በአንድ ኤጲስ ቆጶስ ሥልጣን ብቻ ይሾሙ።

ትእዛዝ ፪:- ጌታችን ካዘዘው (ስንዴ፣ የወይን ፍሬ፣ መብራት፣ ዘይት፣ ንጹሕ ዕጣን) ውጭ ቁርባን ያሳረገ ይሻር።

ትእዛዝ ፫:- ካህን በአገልግሎት ምክንያት ሚስቱን አይፍታ። ከፈቱ ይለዩ። ካልመለሷት ግን ይሻሩ።

ትእዛዝ ፬:- ካህናት ቀንና ሌሊቱ እኩል ከመሆኑ በፊት ከአይሁድ ጋር ቅድስት ፋሲካ እንድትውል ካደረጉ ይሻሩ።

ትእዛዝ ፭:- ኤጲስ ቆጶስ፣ ቄስና ዲያቆን ከዚህ ዓለም ተግባር ውስጥ አይግቡ። ገብተው ከተገኙ ግን ይለዩ።

ትእዛዝ ፮:- ኤጲስ ቆጶስ ወይም ከካህናት አንዱ ምክንያቱን ሳይናገር በቅዳሴ ግን ቁርባን ባይቀበል የማይገባው ሆኖ ከተገኘ ይቅር ይበሉት። ምክንያቱን ካልተናገረ ግን ይባረር። በአሳረገው መሥዋዕት ላይም በንጽሕና እንዳላሳረገው ሆኖ ለሕዝብ እንቅፋት ሆኗልና።

ትእዛዝ ፯:- ወደ ቤተክርስቲያን የሚገባ አማኝ ሁሉ መጻሕፍትንም የሚሰማ ነገር ግን ጸሎት እስከሚያደርጉ ድረስ የማይቆም ቁርባንም የማይቀበል ከሆነ በላዩ ላይ አይጸልዩለት። ሊባረርም ይገባዋል። በቤተክርስቲያን ክርክርንና ብጥብጥን ፈጥሯልና።

ትእዛዝ ፰:- ከቤተክርስቲያን ከተባረረ ሰው ጋር አይጸልዩ።

ትእዛዝ ፲:- ካህን ከተባረረ ካህን ጋር ቢጸልይ እርሱም ይባረር።

ትእዛዝ ፲፩:- ኤጲስ ቆጶስ የሹመት ቦታውን ትቶ በሌላ ሀገረ ስብከት ሊሾም አይገባም።

ትእዛዝ ፲፪:- ያለ ኤጲስ ቆጶሱ ሥልጣን የሥራ ቦታውን ቢተውና ወደሌላ የሥራ ቦታ ቢሄድ እንዳያገለግል እኛ እናዛለን። በይበልጥም ኤጲስ ቆጶስ ወደቦታው እንዲመለስ ቢልክበትና ባይሰማው ከሹመቱ ይባረር። ባለበት ቦታ እንደ ሕዝባዊ ሆኖ ይቁረብ።

ትእዛዝ ፲፫:- ወደ ተውኔት ቤት የምትሔደውን ያገባ ክህነት ሊሾም አይገባውም።

ትእዛዝ ፲፬:- ዋስ የሚሆን ካህን ይሻር።

ትእዛዝ ፲፭:- በራሱ ፈቃድ ራሱን የሰለበ ክህነት አይሾም።

ትእዛዝ ፲፮:- በዝሙት፣ በሐሰት መማል፣ በመስረቅ የሚገኝ ካህን ይሻር።

ትእዛዝ ፲፯:- ክህነት ወደሚገቡበት ጊዜ አናጉንስጢስና መዘምራን ማግባት ቢፈልጉ ያግቡ። ከተሾሙ በኋላ ግብ ማግባት አይገባቸውም።

ትእዛዝ ፲፰:- ሰዎች ይፈሩት ዘንድ የሚደባደብ ካህን እንዲሻር እናዛለን።

ትእዛዝ ፲፱:- በታወቀ ኃጢአት ምክንያት በትክክል የተሻረ ኤጲስ ቆጶስም ቢሆን ቄስም ቢሆን ዲያቆንም ቢሆን ከተደፋፈረና ሥልጣን ባለው ጊዜ ይሠራውን የነበረውን መሥራት ከጀመረ ፈጽሞ ከቤተክርስቲያን ይራቅ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፬ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
2.4K views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 16:13:32
አርኬን፣ መልክዕን፣ እንዲሁም ቅኔን ሐሳቡ ሳይዛነፍ በልዩ ተሰጥኦ በግጥም መልኩ የሚያቀርብልን ውድ ወንድማችን ኤፍሬም የኔሰው ጠቢበ ጠቢባን የተሰኘውን ድንቅ መጽሐፍ በትርጉም በግጥም አዘጋጅቶልናል። እንዳያመልጥዎ።
2.2K views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 13:48:20 _የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፪_
#ግጽው
ትእዛዝ ፲፫ ሕግና ሥርዓትን የማያውቅ ሰው በምእመናን ላይ አይሾም። በምእመናን ላይ ሊሾም የሚገባው በጠባዩ ቸር፣ ታጋሽ፣ በጉዞው ሁሉ ጥሩና ትሑት ይሁን። ይህን ካላደረገ ይሻር። ቃሉንና ትእዛዙንም አይቀበሉት። በአሠራሩ ታማኝ አይደለምና።

ትእዛዝ ፲፬:- ሐሰተኛን እና ሐሜተኛን ሰው ከሹመት ይከልክሉት።

ትእዛዝ ፲፭:- በኮከብ ቆጠራ የሚታመንና በጥንቆላ የሚያምን ሁሉ ከሹመት ይወገድ። ክርስቲያኖችን እግዚአብሔርን ከማያውቁት ጋር የሚያስተካክል ከክህነት ሥልጣን ይሻር።

ትእዛዝ ፲፯:- በዝሙትና በስስት የሚታወቅ እንዲሁም የዚህን ዓለም ጥቅም የሚፈልግ ቄስም ሆነ ዲያቆን ከሹመቱ ይሻር።

ትእዛዝ ፳:- የዚህን ዓለም ሥራ የሚሠራን ሰው በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ላይ እንዲያዝዝ ሹም አያድርጉት። ጸሎት የያዘ ቄስም ሆነ ዲያቆን ጸሎቱን አቋርጦ ወደሌላ ነገር አይሂድ። እንደዚህ የሚያደርግ ከሆነ ወደቀድሞ ቦታው መመለስ አይሆንለትም (አይገባውም)።

ትእዛዝ ፳፩:- ለቅዱሳን ሰማዕታት በሞቱበት ቀን መታሰቢያ ያድርጉላቸው።

ትእዛዝ ፳፩:- መዝሙረ ዳዊትን ቀንም ሌሊትም ይጸልዩት። መዝሙረ ዳዊት ተአምኖ ኃጣውእ፣ ጸሎት፣ ምስጋና አለበትና። ችግር፣ ሐዘንና፣ መከራ በአጋጠማቸው ጊዜ ከጥፋት ያመልጡ ዘንድ ይጸልዩ።

ትእዛዝ ፳፫:- በቤተመቅደስ ለማገልገል ከሕዝብ የተመረጡ ካህናት ሰባት ይሁኑ።

ትእዛዝ ፳፬:- ዐመፀኛውን ጻድቅ የሚያደርግ፣ ንጹሑን የሚያበሳጭ የተወገዘና ርጉም ይሁን። እንደዚህ የሚያደርገውን ከሹመቱ ይከልክሉት። ስለዐመፀኛነቱም ይመስክሩበት። ዐመፀኛ ከሆነ ጵጵስናው አያስፈራህ። (በእንተ ዐመፃሁ ወኢያፍርህከ ጵጵስናሁ)።

ትእዛዝ ፳፭:- በሰዎች ላይ የሚኩራራና በራሱ የሚታበይ ወደ ሹመት አይቅረብ። ከሌሎች ሰዎች እንደሚበልጥ እንደሚከብርና እንደሚሻል ራሱን የሚያይ፣ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በንቀት ዓይን የሚመለከት በሹመት ላይ አይቀመጥ።

ትእዛዝ ፳፮:- በየአውራጃው ባሉ ቀሳውስት ላይ በመካከላቸው ሆኖ የሚያዛቸውና የሚገሥጻቸው ሊቀ ካህናት ይሹሙ።

ትእዛዝ ፳፯:- በጸሎት ጊዜ ንጉሥ በሰው ሁሉ ፊት ከምእመናን ጋር ይሁን። ለቁርባን ወደ መሠውያው ቦታ ይግባ። መቆሚያውም ከሊቃውንትና ከተሾሙ ካህናት ጋር በዚያ ይሁን።

ትእዛዝ ፴:- ቁርባንን በዕለቱ ያቀብሉት እንጂ ለነገ አያሳድሩ።

ሊቃነ ካህናቱ ኒቆዲሞስና ገማልኤል፣ ሐና፣ ቀያፋ፣ ሊቃነ ካህናት ሌሊት ወደክርስቶስ ይመጡ ነበር። በክርስቶስም ያምኑ ነበር። ነገር ግን አይሁድን ፈርተው ይህንን አልገለጹም። ከክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ ሁላቸውም አምነዋል።

የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እርስ በእርሳቸው ይተባበራሉ።

ሐዋርያት ከጠንቋዮች ጋር ይጋደሉ ነበር። ስለ ሃይማኖታቸው ችግር ባጋጠማቸው ጊዜ እኛም የፈጠረንን አስቆጥተነዋልና ይህች የደረሰችብን ችግር ታስታርቀናለች ይሉ ነበር። ከእነርሱ መካከል ብዙ ጊዜ ንብረቱ የተዘረፈበት አለ፣ ከገንዘቡ ከልጆቹና ከቤቱ የራቀም አለ፣ የሰቀሉትም አለ። እስኪሞቱ ድረስ በፈቃዳቸው ይታገሡ ነበር።

ምእመናን ለአማልክት የተሠዋንና በክት የሆነውን ከመብላት፣ ደምን ከመጠጣት፣ ለባዕድ አምላክም ከመሳል እንዲታቀቡ ያዝዟቸው ነበር።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፫
መ/ር በትረማርያም አበባው
2.5K views10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 08:37:27 _የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፩_
ሲኖዶስ የግሪክ ቋንቋ ሲሆን ትርጉሙ ጉባኤ፣ ሸንጎ፣ የጳጳሳትና የሊቃውንት ማኅበር ማለት ነው።
፩) የሐዋርያት ሲኖዶስ የሚባሉት አራት መጻሕፍት ናቸው። እነዚህም:-
√ ግጽው (ረስጠጅ)
√ ትእዛዝ (ረስጠብ)
√ ሥርዓተ ጽዮን (ዓይን)
√ አብጥሊስ (ረስጣ/ረስጠአ)
ናቸው። የሲኖዶስ ውሳኔ የቤተክርስቲያኗ ሕግ እና ሥርዓት ሆኖ ይሠራል።
π
፪) በቤተክርስቲያን ታሪክ እንደሚታወቀው ኤጲስ ቆጶስ ድንግል መሆን እንዳለበት የተወሰነው በአልቪራ ጉባኤ ስፔን በ305/6 ዓ. ም ነው። በኋላ በኒቅያው ጉባኤ ቀርቦም ጸድቋል።
π
፫) የኒቅያ ጉባኤ አርዮስን ካወገዘ በኋላ ሌሎች የሥርዓት ጉዳዮችንም ወስኗል።
π
፬) አንዳንድ ሲኖዶሶች ወቅትንና አካባቢን መሠረት አድርገው የተደነገጉ ናቸው።
π
#ግጽው #ሲኖዶስ
ቁጥር ፲፭:- በቅዱስ ጴጥሮስ ጸሎትና ልመና እግዚአብሔር ጠንቋዩን ሲሞንን አጠፋው።
√√√
ትእዛዝ ፩:- ጸሎታችን ወደ ምሥራቅ ይሁን። ምጽአቱ ከምሥራቅ እንደሚሆን በዚህ አወቅን።
√√√
ሰንበት በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል የቃል ኪዳን ምልክት ነው።
√√√
ትእዛዝ ፪:- ለጸሎት፣ መጻሕፍትን ለማንበብና ቁርባን ለማቅረብ በየእሑዱ በሦስት ሰዓት ይሰብሰቡ። በዚህች ቀን መልአኩ ክርስቶስን እንደምትፀንስ ለማርያም አብሥሯታልና። ጌታ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶበታልና።
√√√
ትእዛዝ ፫:- በዕለተ ረቡዕ ተሰብስበው ጸሎት ያድርጉባት። በዚህች ቀን አይሁድ ይዘው እንደሚሰቅሉትና እና በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ ነግሯቸዋልና። በዚህም ቀን አዝነዋል ተክዘዋልና።
√√√
ትእዛዝ ፬:- በዕለተ ዓርብ በዘጠኝ ሰዓት ተሰብስበው ጸሎት ያድርጉ። ክርስቶስ መከራ ተቀብሎበታልና።
√√√
ትእዛዝ ፭-፮:- ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳት፣ ኤጲስ ቆጶሳት ለምእመናን ሊቃውንትን ይሹሙላቸው። ቀሳውስትን፣ ዲያቆናትን፣ ንፍቅ ዲያቆናትን፣ አናጉንስጢሶችን ይሹሙላቸው።
√√√
ትእዛዝ ፰:- የጌታችንን የልደት በዓል በተወለደባት ቀን ታኅሣሥ ፳፱ን አክብሩ። እስመ ውእቱ ርእሰ ኵሉ በዓላት።
√√√
ትእዛዝ ፱:- የጌታችንን የጥምቀት በዓል ጥር 11 ቀን ያድርጉ። የምስጋና ቀን ናትና።
√√√
ትእዛዝ ፲:- በየዓመቱ ፵ ቀን ይጹሙ። የክርስቶስን ሕማሙን፣ ስቅለቱን፣ ሞቱንና ወደ መቃብር መውረዱን ያስቡ። በትንሣኤው ቀንም ፋሲካን ያድርጉ። ከሰንበታት በስተቀር ቅዳሜና ዓርብን ጨምሮ ፵ ቀን ጾመው ሲጨርሱ በዓል ያድርጉ። እሑድ ትንሣኤው ነው። ከእነዚህ ቀናት በኋላ እስከ ኃምሳኛው ቀን መጨረሻ ድረስ ጾም የለም።
√√√
ትእዛዝ ፲፩:- ከትንሣኤው በኋላ በ፵ኛው ቀን ጌታችን ወደ ሰማይ ያረገበትን በዓል አክብሩ።
√√√
ትእዛዝ ፲፪:- ከኦሪት ከነቢያት መጻሕፍት ሁሉ እና የሐዋርያትን ዜና በቤተክርስቲያን በታላቅ አትሮንስ ላይ ያንብቡ። ከዚያ በኋላም የመጻሕፍት ሁሉ ፍጻሜ ነውና ከወንጌል ያንብቡ። ሕዝቡም ሁሉ በእግሩ ቆሞ ይስማ። የሕይወትና የመድኃኒት የምሥራች ነውና።
√√√
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፪ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
2.8K views05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 18:58:51 ማንኛውም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለፍርድ እንደሚቆም ማሰብ አለበት። በሰው ፊት ጻድቅ ለመምሰል መሞከር ጥሩ አይደለም። ሰው እንደሆነ ለዐቢይም፣ ለወያኔም አጨብጭቧል።
1.2K views15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 18:42:04
በትረ 9ኛ ክፍል ሳለ።
ይህን ኩታራ ሙልጭ አድርጋችሁ ገሥጹትማ። አበዛውኮ ጎበዝ። በጣም ወበራ።

በእርግጥ በዚህ ምድር ከምታመሰግኑኝ እና ከምታከብሩኝ ይልቅ ብሞት ይሻለኛል። እከብር ባይ ልቡናን ጥሎ እውነትን መናገር የተሻለ ነው። የእናንተ ምስጋና ከንቱ ውዳሴ ሆኖ ወደ ሲኦል ያስገባል። የእናንተ ተግሣጽና ቁጣ ግን ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚመራ ድንቅ መንገድ ነው።

ሰው የሰው አምላኪ መሆን የለበትም። ጳጳስም በለው፣ ንጉሥም በለው፣ መምህርም በለው ይሳሳታል። ሲሳሳት በመንጋነት ስሕተቱን ከማጽደቅ ይልቅ ስሕተቱ ብዙዎችን እንዳያበላሽ መግለጥ ይገባል። እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን ልንፈራ አልተማርንም።

አካፋን ትልቅ ማንኪያ ማለት ትልቅ ነውር ነው። የእውነት ፀር መሆን ነው። ከእውነት ጋር ከምትጣላ ሰው ቢጠላህ ይሻላል።

መምህረ ፌስቡክ ወቴሌግራም በትርሽ
1.3K viewsedited  15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ