Get Mystery Box with random crypto!

_____መምህር ሐዋዝ ሐጎስ____ ከጦርነቱ ወዲህ የኔታን ማግኘት አልቻልኩም። ቅኔን ያስተማሩኝ እ | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

_____መምህር ሐዋዝ ሐጎስ____
ከጦርነቱ ወዲህ የኔታን ማግኘት አልቻልኩም። ቅኔን ያስተማሩኝ እሳቸው ነበሩ። የታላቁ ገዳም የደብረ ሊባኖስ ገዳም የቅኔ መምህር ነበሩ። ከጦርነቱ በፊት ወደክፍለ ሀገራቸው ወደ ትግራይ ከሄዱ በኋላ በኋላ ስልካቸውም ጠፋኝ እሳቸውም ጠፉኝ። ይደውሉልኝ ነበረ።

የኔታ ጸሎትን የሚያበዙ ደግ መምህር ናቸው። ይህ ክፉ ጦርነት አልፎ ወደፊት እንደምንገናኝ ተስፋ አደርጋለሁ። ኢትዮጵያን ወደ መቀመቅ የከተታት ጦርነት በታሪክ በክፉ ሲወሳ ይኖራል። የሀገራችንን ቀውስ ያበዛነው እኛ ልጆቿ ነን። ሁሉም ራስ ወዳድ ነው። ለሀገር ለእውነት ለፍቅር የሚቆም የለም። በሌላው ጉዳት መጠቀምን የሚፈልጉ ፖለቲከኞች ሀገራችንን አደቀቋት። የሀገር መሪ ሆነው ለተወለዱበት ክልል የሚሠሩ ድኩማን ለዚህ አበቁን።

ሀገራችንን ማዳን ከሁላችንም ይጠበቃል።