በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw — የቴሌግራም ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ betremariyamabebaw — በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw
የቴሌግራም ቻናል አርማ betremariyamabebaw — በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw
የሰርጥ አድራሻ: @betremariyamabebaw
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 48.65K
የሰርጥ መግለጫ

አቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር

የቻናል ስታትስቲክስ
5.1% የተሳትፎ መጠን
2,467 እይታዎች / ልጥፍ
0 ልጥፎች / ቀን

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

6 juuni 2023
ማር ይስሐቅ ፬፣፮
ጾም
√የጸሎት እናት (እማ ለጸሎት)
√የአንብዕ መገኛ (ወነቅዓ ለአንብዕ)
√ዝምታን የምታስተምር (ወመምህራ ለአርምሞ)
ለበጎ ሥራ ሁሉ የምታነቃቃ ናት።

ንጹም ጾመ
ወናፍቅር ቢጸነ
ወንትፋቀር በበይናቲነ
3.7K views12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
26 apr 2023
_ዲድስቅልያ ክፍል ፩_
ስምንቱ የሕግና የሥርዓት መጻሕፍት የሚባሉት:-
፩) ሥርዓተ ጽዮን
፪) ትእዛዝ
፫) ግጽው
፬) አብጥሊስ
፭) ፩ኛ መጽሐፈ ኪዳን
፮) ፪ኛ መጽሐፈ ኪዳን
፯) ቀሌምንጦስ
፰) ዲድስቅልያ
ናቸው። አራቱን ከዚህ ቀደም ተማምረናቸዋል። ዲድስቅልያ ማለት ትምህርት ማለት ነው። የጽርእ ቃል ነው። ዮሐንስ ቅዱስ ጴጥሮስን አበ ዓለም ይለው ነበር። ይህንን ዲድስቅልያ የተባለ መጽሐፍ ሐዋርያት በኢየሩሳሌም ከተማ ተሰብስበው ሠርተውታል።
_አንቀጽ ፩_√
፪:- በቤተክርስቲያን ያሉ የሹመት መዓርጋት በሰማያት ባለው አምሳል እንዲሆን አዘዝን።
፬:- ኤጲስ ቆጶሱ እንደ ጠባቂ ነው። ቀሳውስትም መምህራን ናቸው። ዲያቆናትም አገልጋዮች ናቸው። ንፍቀ ዲያቆናትም ረዳቶች ናቸው። አናጉንስጢሳውያንም በማስተዋል የሚያነቡ ናቸው። አብስሊድሳውያን መዘምራን ናቸው።
፭:- (ምእመናን) የትምህርቱን ቃል ያስተውሉ።
፱:- ለእግዚአብሔር ደስ የማያሰኘውን ሥራ አትሥራ።
፲:- ለራሳችሁ የሚበልጠውን ክፍል መውሰድን፣ ለወንድሞቻችሁ ግን ጥቂት መስጠትን አትውደዱ።
፲፰:- የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው ብሩህ ሕጉን የሚጠብቁ ሰዎች ይቅርታንና ምሕረትን ያገኛሉ። ለራስህ የምትጠላውን በባልንጀራህ ላይ አታድርግ። አንተ ሌላው ሰው ሚስትህን ያይ ዘንድ ማንም በተንኮል ያስታት ዘንድ እንደማትወድ እንደዚሁ አንተም የሌለውን ሚስት በክፉ ሕሊና አታስብ። ለራስህም መርገምን ስድብንና መመታትን እንደማትወድ እንደዚሁ አንተም በሌላው አታድርግ።
፲፱:- የረገመህም ቢኖር አንተ ግን መርቀው።
፳፪:- ወዳጆቻችን ሆይ የብርሃን ልጆች እንሆን ዘንድ ትእዛዛትን እናስተውል። እርስበእርሳችን ትዕግሥትን እንያዝ።
፳፫:- ወንድ ሚስቱን ይታገሣት። ትዕቢተኛና ግብዝም አይሁን። ነገር ግን የሚራራና ቅን ይሁን። ለብቻዋም በፍቅርና በትሕትና ደስ ያሰኛት።
፳፮:- የራስህን ጠጉር አታሳድግ፣ ጠጉርህን ቁረጥ።
፳፱:- ጽሕማችንን እንላጭ ዘንድ ለእኛ አይገባም።
፴:- እግዚአብሔርን ደስ ታሰኘው ዘንድ ከወደድህስ ክፉ ሥራን አትሥራ። ፈጣሪህም የሚጠላውን ሁሉ ከአንተ አርቅ። ሰካራም አትሁን። በእጆችህ ሥራ ትረህ ግረህ ተመገብ።
_አንቀጽ ፪_√
፩:- ሥራ ፈት ሆነህ አትኑር። በነገሥትና በነቢያት መጽሐፍ ውስጥ ያለውንም ተመልከት። የምስጋና መዝሙርን ዘምር። የሕግ ሁሉ ፍጻሜ የሚሆን የወንጌልንም ቃል ስማ።
፪:- ለማይረባ ለማይጠቅም ለከንቱ ነገር ሁሉ አትጨነቅ። ከወንጌል ልዩ የሚሆን ሕግንና ሃይማኖትን ለውጠው የሚያጠፉ ሐሰተኞች መምህራንን አትሻ።
፴፰:- በሃይማኖትና በጎ በመሥራትም እንጽና። ከክፉ ሥራም ሁሉ እንራቅ።
_አንቀጽ ፫_√
፩:- ሴት ለባሏ በትሕትና ትታዘዝ።
፳፰:- ክፉ ሴት ለራሷ ውርደትን ታመጣለች።
፴፪:- ያመኑ ሴቶች ራሳቸውን በንጽሕና ሊከናነቡ ይገባል። የፊታቸውን ውበት በማሳመርና ቀለም በመቀባት አይደለም። እግዚአብሔር በፈጠረው መልክ ውስጥ ጥቅም በሌለው ኩል መኳልና ማጌጥም አይደለም። እንዲህ ያለውን ሁሉ አይሥሩ። ነገር ግን እነርሱ ተከናንበው በጎዳና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ይሂዱ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፪ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
4.1K views06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
8 veebr 2023
__ ባሕረ ሐሳብ ክፍል ፫ __
የበዓላትና የአጽዋማት ተውሳክ።መባጃ ሐመር 29 እንደመጣ ክፍል ፪ ላይ አይተናል።ይኽውም ጥር 29 ቀን የነነዌ ጾም ትገባለች ማለት ነው።ሌሎቹ መቼ እንደሚውሉ ለማወቅ ይህን መባጃ ሐመር ከተውሳኮቻቸው ጋር እየደመርን እናገኘዋለን።የአጽዋማትና የበዓላት ተውሳክ እነሆ
የዐቢይ ጾም ተውሳክ 14
የደብረ ዘይት ተውሳክ 11
የሆሳእና ተውሳክ 2
የስቅለት ተውሳክ 7
የትንሳኤ ተውሳክ 9
የርክበ ካህናት ተውሳክ 3
የዕርገት ተውሳክ 18
የጰራቅሊጦስ ተውሳክ 28
የጾመ ሐዋርያት ተውሳክ 29
የጾመ ድኅነት ተውሳክ 1
ነው።ስለዚህ እኒህን ተውሳኮች ከመባጃ ሐመሩ ጋር እየደመርን በአላቱ አጽዋማቱ መቼ እንደሚውሉ ያሳውቁናል።ስለዚህ
ዐቢይ ጾም=14+መባጃ ሐመር
=14+29
=43
ስለዚህ ዓቢይ ጾም የካቲት 13 ይውላል ማለት ነው።መጥቅእ ጥቅምት ውሎ ስንደምረው ከ30 በላይ ከሆነ በ30 ገድፈን መጋቢት ላይ ይውላል።በ2015 ዐቢይ ጾም የካቲት 13 ይውላል።
ደብረ ዘይት=11+መባጃ ሐመር
=11+29
=40
መጋቢት 10 ደብረ ዘይት ይውላል ማለት ነው።መጥቅእ ጥቅምት ውሎ ይህ ድምር ከ30 ከፍ ካለ ግን በ30 ገድፈን ሆሳእና ሚያዝያ ላይ ይውላል ማለት ነው።
ሆሣዕና=2+መባጃ ሐመር
=2+29
=31
ሚያዝያ 1 ሆሳእና ይውላል ማለት ነው።
ስቅለት=7+መባጃ ሐመር
=7+29
=36
ሚያዝያ 6 ስቅለት ይውላል ማለት ነው
ትንሳኤ=9+መባጃ ሐመር
=9+29
=38
ሚያዝያ 8 ትንሳኤ ይውላል ማለት ነው።
ርክበ ካህናት=3+መባጃ ሐመር
=3+29
=31
ግንቦት 1 ቀን ርክበ ካህናት ይሆናል ማለት ነው
ዕርገት=18+መባጃ ሐመር
=18+29
=47
47 ከ30 በላይ ስለሆነ በ30 ስንከፍለው አንድ ደርሶ 17 ይተርፋል።ይህም ዕርገት ግንቦት 17 ይሆናል ማለት ነው።
ጰራቅሊጦስ=28+መባጃ ሐመር
=28+29
=57
ይህ ከ30 በላይ ስለሆነ በ30 ስናካፍለው 1 ደርሶ 27 ይተርፋል።ስለዚህ ጰራቅሊጦስ ግንቦት 27 ይውላል ማለት ነው።
ጾመ ሐዋርያት=29+መባጃ ሐመር
=29+29
=58
ይሆናል በ30 ስንገድፈው 1 ጊዜ ደርሶ 28 ይተርፋል።ስለዚህ ግንቦት 28 ጾመ ሐዋርያት ይገባል ማለት ነው።
ጾመ ድኅነት=1+መባጃ ሐመር
=1+29
=30
ስለዚህ ጾመ ድኅነት ግንቦት 30 ይጀምራል ማለት ነው።

__ ኢየዐርግ እና ኢይወርድ __
እነዚህ በዓላት ኢየዐርግ (አይወጣም) ናን ኢይወርድ (አይወርድም) አላቸው ለምሳሌ የነነዌ ጾም ቢወርድ ቢወርድ ጥር 17 ይሆናል እንጂ ጥር 16 አይሆንም።እንዲሁም ቢወጣ ቢወጣ የካቲት 21 ይሆናል እንጂ የካቲት 22 ሊሆን አይችልም።ይህ ማለት የነነዌ ጾም ከጥር 17 እስከ የካቲት 21 ባለው ብቻ ይውላል ማለት ነው።በዚህ መሰረት የሌሎችንም እንመልከት
ኢይወርድ.......ኢየዐርግ
የነነዌ ጾም.............ጥር 17........የካቲት 21
ዓቢይ ጾም..............የካቲት 1......መጋቢት 5
ደብረ ዘይት.............የካቲት 28....ሚያዝያ 2
ሆሳእና....................መጋቢት 19...ሚያዝያ 23
ስቅለት...................መጋቢት 24....ሚያዝያ 28
ትንሳኤ..................መጋቢት 26.....ሚያዝያ 30
ርክበ ካህናት.........ሚያዝያ 20.......ግንቦት 24
ዕርገት..................ግንቦት 5..........ሰኔ 9
ጰራቅሊጦስ............ግንቦት 15.......ሰኔ 19
ጾመ ሐዋርያት...........ግንቦት 16.......ሰኔ 20
ጾመ ድኅነት.............ግንቦት 18..........ሰኔ 22
የበዓላትና የአጽዋማት ኢየዐርግና ኢይወርድ ይህንን ይመስላል።

የዘመን መለወጫ መስከረም ወይስ ጥር
በነገራችን ላይ የእኛ የዘመን መለወጫ መስከረም 1 ቀን ነው። እስራኤላውያንን በኦሪት እንደተጻፈው ጌታ ከግብጽ የወጣችሁበት ወር ሚያዝያ የዘመን መለወጫ ይሁናችሁ ብሏቸዋል። በእስራኤል ጥር የካቲት መጋቢት ክረምት ነው።ሚያዝያ የክረምት መውጫ ነው።የእኛ ክረምት ግን ሰኔ ሐምሌ ነሐሴ ነው። ክረምት የሚወጣበት መስከረም ስለሆነ
የዘመን መለወጫችን መስከረም ነው። ፈረንጆቹ ደግሞ ጌታ የተወለደበትን ታህሣስ 29 ጀምረው ዘመንን ይለውጣሉ። ያም ሆነ ይህ በአቡሻኽር ትምህርት እንደምናገኘው በዓለም ላይ በጣም ብዙ የዘመን አቆጣጠሮች አሉ። ስለዚህ የሁሉንም ከመቀበል ውጭ ይህ ስህተት ነው ይህ ልክ ነው ማለት አንችልም።ጌታ ግን የዘመን መለወጫ በሚያዝያ ይሁን ብሎ ስለዘመን መለወጫ የተናገረው ብቸኛው ቃል በኦሪት ይገኛል።
ይህ ሁሉ መደከሙ የዘመናትን ባለቤት እግዚአብሔርን ዘመኑን እያስታወስን ለማመስገን (ለአሥርቆት) ነው።ሁልጊዜ ቢሆን ጸሎታችንን የምንጀምረው ከዚህ በኋላ በሚገኘው መንገድ ነው። ውዳሴ ማርያምም ይሁን ሌላ ጸሎት ከአሥርቆት በኋላ ነው።አሥርቆቱም ይህ ነው።
ሃሌ ሉያ በዘንዜከር ሐሳባተ ሕጉ ወትእዛዛቲሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐሳበ ነቢያት ወሐዋርያት ሐሳበ ጻድቃን ወሰማእት ሐሳበ ደናግል ወመነኮሳት ሐሳበ ኄራን መላእክት እንዘ ሀሎነ በዘመነ ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ (አስተውል ሉቃስ ጸሎት እያደረግክበት ያለው ዘመን ነው) ቡሩክ ያብጽሐነ እስከ ዘመነ ዮሐንስ ዜናዊ።ካልክ በኋላ ያለህበትን ዘመን ዓመተ ምህረት ዓመተ ዓለም አስበህ በ፸፻ወ፭፻፲፭ ኮነ ዓመተ ዓለም።በ፶፻ወ፭፻ ኮነ ዓመተ ኩነኔ ዓመተ ፍዳ።በ፳፩፲፭ ኮነ ዓመተ ምሕረት።ትልና በመቀጠል ያለህበትን ወር አንስተህ ለቀጣዩ ወር በሰላም ያድርሰኝ ለማለት ዮም ሠረቀ ለነ ወርኀ መስከረም (በመስከረም ወር ከሆነ እየጸለይክ ያለኽው) ቡሩክ ያብጽሐነ እስከ ወርኀ ጥቅምት በሰላመ እግዚአብሔር አብ አሜን ትላለህ።በመቀጠል የእለቱ ሠርቀ መዓልት ሠርቀ ሌሊት እና ሠርቀ ወርኅ አስበህ እንዲህ ትላለህ።መስከረም 1 ላይ ከሆነ እየጸለይክ ያለኽው አሚሩ (፩) ሠርቀ መዓልት። አሡሩ ወአሚሩ (፲፩) ሠርቀ ሌሊት (11ን ያገኘነው አበቅቴ+ሠርቀ መዓልት+ሕጸጽ አድርገን ነው) አሡሩ ወኀሙሱ (፲፭) ሠርቀ ወርኅ።ሠርቀ ወርኅን ያገኘነው ሠርቀ ሌሊት ላይ 4 በመጨመር ነው።ከዚያ እየጸለይክ ያለኽው እሑድ ከሆነ ኀሙሱ ጥንተ ዖን አሚሩ ጥንተ ዕለት ሰዱሱ ጥንተ ቀመር
336 views04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
7 veebr 2023
መጥቅእ በዓላትና አጽዋማት መቼ እንደሚውሉ ሲያሳውቁን አበቅቴ ደግሞ ሠርቀ ወርኅ እና ሠርቀ ሌሊትን ለማግኘት ይጠቅመናል።

ሠርቀ መዓልት የሚባለው ራሱ ቀኑ ነው።ለምሳሌ የመስከረም 1 ሠርቀ መዓልት ራሱ 1 ነው።
ሠርቀ ሌሊት=አበቅቴ+ሠርቀ መዓልት+ሕፀፅ
=9+1+1
=11
ሠርቀ ወርኅ=ሠርቀ ሌሊት+4
=11+4
=15
ሕጸጽ ያልነው።
የመስከረምና የጥቅምት 1
የህዳርና የታህሳስ 2
የጥር እና የየካቲት 3
የመጋቢት እና የሚያዝያ 4
የግንቦትና የሰኔ 5
የሐምሌ እና የነሐሴ 6 ነው

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
መ/ር በትረማርያም አበባው
1.6K views05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
23 okt 2022
#ድርሳነ #ቄርሎስ #ወጰላድዮስ #ክፍል5
ይህ መጽሐፍ በዋነነት ከቀድሞ ጀምሮ የተነሱ ከሃድያንንን እና ስህተታቸውን አንጠርጥሮ የሚያሳይ መጽሐፍ ነው።በከሃድያን ክህደት እንዳንወሰድ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። ክርስቶስን ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ ያለ ንስጥሮስ፣ ቃለአብን ዝርው የሚሉ እነ መርቅያን፣ በነፍሱ ምትክ ቃል ሆነው የሚሉ እነ አቡሊናርዮስ እና ሌሎችም ከሃድያን ያነሷቸውን ጥያቄዎች በደንብ የሚመልስ መጽሐፍ ነው።ነገረ ክርስቶስ ነገረ ሥጋዌ በሰፊው የተዳሰሰበት መጽሐፍ ነው።እስከ ክፍል 5 የጻፍኩት መጽሐፉን ለመጠቆም ያህል ብቻ እና እንድታነቡት እንጂ እስከ ክፍል 1000 ቢጻፍም አያልቅም።

ቄርሎስ 21 በነፍሱ ምትክ መለኮት ሆነው ያለ አቡሊናርዮስ ክርስቶስ በመስቀል ሞተ በሚለው ቃል ይረታል።ሞት ማለት መለየት ማለት ነው።ይኽውም የነፍስ ከሥጋ መለየት ማለት ነው።ከሥጋ መለኮት ነው የተለየው እንዳይባል ቅዱስ ዳዊት ውስተ ኩሉ በሐውርት መለኮቱ።መለኮቱ በሁሉ ቦታ ነው ስለሚል።ከሥጋ ተለየ ከተባለ መለኮት ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን በሥጋ የልነበረበት ጊዜ ነበረ የሚያሰኝ ታላቅ ክህደት ነው።መለኮት ምሉእ በኩለሄ በሁሉ ያለ ነው የሚለውን የሚቃወም ክህደት ነው። መለኮት በሁሉ ቦታ ይኖራል። መለኮት የሌለበት ቦታ የለም።

ቄርሎስ 23 ላይ እኛስ ከተዋሕዶ በኋላ ሁለት አንልም።ንህነሰ ኢንቤ ክልኤቱ እምድኅረ ትድምርት።እንዲል ንሥጥሮስ ግን ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ ብሎ ከመጽሐፍ ያልተገኘ ልብወለድ ይናገራል። ሐዋርያው ጠላቶቹ ስንሆን እግዚአብሔር በልጁ ሞት ይቅር አለን ብሏል።ንሥጥሮስ ማርያም የወለደችው ሌላ ነው አብ የወለደው ሌላ ነው ከማርያም የተወለደው ይራባል ይጠማል ይሞታል ከአብ የተወለደው ግን አይራብም አይጠማም አይሞትም እያለ ይናገራል።ነገር ግን ይህንን ሀሳቡን የሐዋርያው ቃል ያፈርስበታል እግዚአብሔር በልጁ ሞት ይቅር አለን ብሏል።የእግዚአብሔር ልጅ ወልድ በሥጋ መሞቱን በልጁ ሞት ብሎ ስለገለጠበት ንስጥሮስ ይህን እና ይህን በመሳሰሉ ቃላት ይረታል። መጻሕፍትም ወልድ ዋሕድ አንድ ልጅ እያሉ አንድ አንድ እያሉ በነጠላ ቅጽል ተናገሩ እንጂ ክልኤቱ ብለው አልተናገሩም።

ማጠቃለያ፦ሃይማኖት በግል ፍልስፍና እና በይመስለኛል እንዲሁም በልብወለድ አይመሰረትም።ከአበው የተቀበልነውን ሳንበርዝ ሳንከልስ ለልጅ ልጆቻችን እናወርሳለን እንጂ የምንጨምረውም የምንቀንሰውም አይኖርም።ሃይማኖት አንዲት ናት። ኤፌ.4፥4።እስከ ምጽአት ድረስ ከስንዴው ጋር ተቀላቅለው የበቀሉ እንክርዳዶች እና ሌሎች አረሞች ይኖራሉ።በምጽአት ጊዜ ግን ስንዴውን ወደ ጎተራው (መንግሥተ ሰማያት) ጌታው ያስገባዋል። እንክርዳዱንና ሌሎችን አረሞችን ደግሞ በእሳት (በገሀነም) ያቃጥላቸዋል።እስከዚያው ግን ተዋቸው ይኑሩ ብሎ ለመላእክቱ ስለተናገረ።በዚች ዓለም ላይ እስከ ምጽአት ድረስ አማኙም፥ ከሀዲውም፣ አረሚውም፣ደጉም፥ ሌባውም፥ ገዳዩም፣ ጻድቁም በአንድነት ተቀላቅለው ይኖራሉ።በምጽአት ጊዜ ግን አምነው ምግባር የሰሩት ወደዘላለም ደስታ ከዚህ ውጭ የሆኑት ደግሞ ወደዘላለማዊ መከራና ጭንቅ ይገባሉ።

አነሳስቶ ላስጀመረን
አስጀምሮ ላስፈጸመን
ልዑል እግዚአብሔር
ምስጋና ይገባል።
8.8K views04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ

ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች

ስለ በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw 48.65K ተመዝጋቢዎች ያሉት የቴሌግራም ቻናል ነው። በዚህ ገጽ ላይ የቅርብ ጊዜ ልጥፎችን ማንበብ፣ ግምገማዎችን ማየት እና ዝርዝር ስታትስቲክስን መመልከት ይችላሉ።
በዚህ ገጽ ላይ "ወደ ቻናል ይሂዱ" የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ ወይም @betremariyamabebaw ን በቴሌግራም መተግበሪያ ውስጥ ይፈልጉ። እንዲሁም የቻናሉን የተጠቃሚ ስም ገልብጠው በቴሌግራም መፈለጊያ ውስጥ መለጠፍ ይችላሉ።
አዎ፣ በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw ነፃ የቴሌግራም ቻናል ነው። ሁሉንም ልጥፎች ያለምንም ክፍያ መከታተል እና ማንበብ ይችላሉ።
የበትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw ቻናል በአሁኑ ጊዜ 48.65K ተመዝጋቢዎች አሉት። የተመዝጋቢዎች ቁጥር በመደበኛነት ይዘመናል።
በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw ይዘቱን በዋናነት በአማርኛ ቋንቋ ያትማል። የቅርብ ጊዜ መልዕክቶችን በዚህ ገጽ ላይ አስቀድመው ማየት ይችላሉ።
አዎ፣ ተመሳሳይ የሃይማኖት ቻናሎችን ከታች "ተመሳሳይ ቻናሎች" በሚለው ክፍል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ። ተዛማጅ የቴሌግራም ቡድኖችን፣ ቦቶችን እና ተለጣፊዎችንም እናሳያለን።
አዎ፣ ቻናሉን በቴሌግራም ላይ ሳይመዘገቡ የበትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw የቅርብ ጊዜ መልዕክቶችን እዚሁ Telegram Store ላይ አስቀድመው ማየት ይችላሉ።
በትረማርያም አበባው Betrema... avatar
በትረማርያም አበባው Betrema... @betremariyamabebaw
በቴሌግራም ይክፈቱ