Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxamero — ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxamero — ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
የሰርጥ አድራሻ: @orthodoxamero
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.99K
የሰርጥ መግለጫ

Facebook Link
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-04 21:25:20
#ኦርቶዶክሳዊት_ቤተክርስቲያን_እና_ኦርቶዶክሳዊ_ወጣት
ነገ #ሰኔ_28 ከ9:30 - 12:00 በአዶላ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ #እንዳያመልጥዎ
722 viewsወሰንየለው ባህሩ, 18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 19:29:41 +++ "ክረምትን ለምን ፈራሁ?" +++

በጋና ክረምትን እያፈራረቀ የሰውን ልጅ ሁሉ የሚመግብ እግዚአብሔር ነው። በክረምት ገበሬው ይዘራል፣ እግዚአብሔር ደግሞ ከሰማይ ጠሉን ይልክለታል። በክረምቱ ጊዜ ተዘርቶ ያደገው ሰብል እንዲበስል ፈጣሪው የበጋውን ፀሐይ ያወጣለታል። ትጉሁ ገብሬም የደረሰውን አዝመራ ሊሰበስብ በበጋው ማጭዱን ይዞ ይታያል። ክረምት ለገበሬው የሥራ ጊዜ ነው።

ለእኔ ግን ክረምት ያስፈራኛል። እንዳልጽፍ እጆቼ በብርዱ ቆፈን ይያዛሉ፣ እንዳላነብ አይኖቼ በእንቅልፍ ሽፋሽፍት ይፈዝዛሉ። ማልጄ በቤቴ መስኮት የማያት ፀሐይ በደመና ስትሸፈን ቀኑ የጀመረ ሌሊቱም የነጋ አይመስለኝ። ከአልጋዬ ተነሥ ተነሥ አይለኝም።  ውጪው ሲጨልም ቤቴም ይደበዝዝብኛል። ወጥቼ ሥራዬን እንዳልሠራ፣ ከወዳጆቼ ጋር ተገናኝቼ እንዳላወጋ ዝናቡ አላላውስ ይለኛል። ለእኔ ክረምት ያስፈራኛል።

ግን ለምን ክረምትን ፈራሁት? እንደ ገበሬው የዝናብን በረከት ማየት ስላቃተኝ ይሆን? ወይስ የምዘራው ዘር በእጄ ስለሌለ? እንዲጸድቅ የምፈልገው ተክል፣ ልምላሜውን ማየት የሚያጓጓኝ እጽ የለኝ ይሆን?

በሥራ እና በግል ጉዳዮቼ ተጠምጄ ከራቅኋቸው ከቤቸሰቦቼ ልብ ላይ የምዘራው ብዙ የፍቅር ዘርማ አለኝ። በሰዎች ሆታ እና ጩኸት ስከበብ የዘነጋሁት በመልካም ሰብእና እንዲጸድቅና እንዲለመልም የምፈልገው እኔነት አለኝ። ታዲያ ለራሴ የሚሆን በቂ ጊዜ አግኝቼ ውስጤን አርስ፣ እመረምርና አለሰልስ ዘንድ ክረምት የመጣው፣ ዝናቡስ የዘነበው ለእኔ ብሎ አይደል?

ለካ የብርዱ ቆፈን የበረታብኝ፣ የአይኖቼ ሽፋሽፍት በእንቅልፍ የደከሙብኝ ክረምትን ስለማልወደው ሳይሆን የክረምትን በረከት ማስተዋል ስላልቻልኩ ነው። ለካስ ክረምቱ የደበተኝ "ደግሞ ሊመጣ ነው" ብዬ ቀድሜ ስላወገዝኩትና ራሴን ለሥራ ስላላዘጋጀሁ ነው። ሰማዩ ሲደምን እና ዝናቡ አላስወጣ ብሎ ሲዘንብ በእኔ ውስጥ ያለችውን ፀሐይ ፈልጌ እንድገልጣት እድል እየሰጠኝ ነው። ክረምት የደረቀው እጽ መልሶ የሚያቆጠቁጥበት ብቻ ሳይሆን ያረጀውና ሊወድቅ ያዘመመው ውስጤ የሚታደስበትና የሚጠገንበት ጊዜ ነው። ለካስ ክረምት ለገበሬ ብቻ የመሰለኝ ስህተት ነው። ክረምት ለእኔም ነው!

(ክረምት ሲገባ እና ፀሐይ አዘውትራ መታየት ስታቆም ከዚህ ጋር ተያይዞ  "Seasonal affective disorder" የተባለ ድባቴ ውስጥ ለሚገቡ ሁሉ መታሰቢያነት የተጻፈ)

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ሰኔ 26፣ 2013 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
1.1K views£itsum, edited  16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 12:23:39 ብቻቸውን ሲኖዶስ የነበሩት ብፁዕ አባታችን፦

ከ1960 መባቻ እስከ 1998 ዓ.ም የካሪቢያንና ጃማይካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው አገልግለዋል።
ከመደበኛ ሀገረ ስብከታቸው ውጭ ያጠመቁት ሕዝብ ሳይቆጠር፥155 ሺህ ምእመናናንን አስተምረው አጥምቀው አቁርበዋል። ከሰባ በላይ አብያተ ክርስቲያናትን አሳንጸዋል።
'የአገሩን ሰርዶ በአገሩ በሬ' እንዲሉ ካስተማሩት ሕዝብ አብራክ የተገኙ 300 የሚሆኑ መምህራንን በክህነትና ስብከተ ወንጌል እንዲያገለግሉ አሠልጥነው ሾመዋል።
ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ፥ ብቻቸውን ሲኖዶስ የነበሩ አባት!

ሰሞኑን ባነበብኩት ጽሑፍ፥ ማኀበረ ቅዱሳን እንኳ እንደ ግዙፍ ተቋምነቱ፣ እንዳለው የሰው ኀይልና የተሻለ አደረጃጀት፥
እስከአሁን ባለው አገልግሎቱ ወደ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የሰበሰባቸው ነፍሳት 350 ሺህ ናቸው።
ሆኖም፥እኛን በበላይነት ከሚመራን ተቋም አንጻር፥ የተቀመጠና የሚሮጥ ሰውን ያህል ልዩነት አለን።
እንደ ተቋም፣ የጠፉትን መፈለግ፣ የአሉትን አማኞች ማጽናት የተተወ ነገር ሆኗልና።
ተቋሙ ከመሠረታዊው የክህነት አገልግሎት አፈንግጦ፤ በግለሰባዊና ቡድናዊ ትብትቦች የሚያባክነው ዘመን ያሳዝናል።

ለዚህ አይነቱ ተቋማዊ ድንዛዜ፥ ፍቱን መፍትሔ የሚሆን አምጦ መውለድ ነው።
ቤተክርስቲያን እንደ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ያሉትን አምጣ ካልወለደች የወላድ መካንነቷ ይቀጥላል።
እንደ እርሳቸው ያሉትን አባቶች ሲሾሙ ማየት ያልቻልን፥ሰዎቹ ስለሌሉ አይመስለኝም፤ ስላልቀረቡ እንጂ።
አዎ! እነሱ ራሳቸውን ለቤተክርስቲያን የሠጡ እንጂ ቤተክርስቲያንን ለራሳቸው የቀሠጡ አይደሉም።
እናም ቤተክህነቱን ለሥልጣን ደጅ አይጠኑም፤አሹሙን እያሉ በብፁዓን አባቶች ደጅ አይኳትኑምና ብዙ አናውቃቸውም።

የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ ከወንዝ አልፎ ውቅያኖስን ተሻግሮ እንደ ቀድሞው በክብርና በሞገስ ይቀጥል ዘንድ
ይስሐቆችን ለሹመት አምጦ መውለድ የብፁዓን አባቶች ድርሻ ብቻ አይደለም። ምእመናን መምህራን ሁሉ ድርሻ አላቸው።


(ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው)

https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
1.4K views£itsum, edited  09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 12:22:57
1.2K views£itsum, 09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 09:30:55
በፈረሰው በኩል እንቁም!

በትግራይ ክልል ባሉ አህጉረ ስብከቶችና ዋግኽምራ ሀገረ ስብከት በርካታ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች የዓለም አቀፍ ድጋፍ ሰጭ ተቋማት መውጣትን ተከትሎ ከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛሉ።

ማኅበረ ቅዱሳንም በትናንትው ዕለት አስቸኳይ የሰባዊና ማኅበራዊ ድጋፍ ጥሪ አድርጓል።

ድጋፍ ለማድረግም፡- በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
2. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
3. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
4. በአዋሽ ባንክ 5 ኪሎ ቅርንጫፍ- 01329817420400 መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ለበለጠ መረጃ
• 09 84 18 15 44
• 09 43 00 04 03
• ማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 1ኛ ወለል

https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
1.3K views£itsum, edited  06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 22:56:24 የዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ድንቅ አዲስ ዝማሬዎች ናቹው share share share
1.5K views£itsum, 19:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 12:32:12
የንጉሥ ሥልጣን በሥጋ ላይ ነው፤ የካህን ሥልጣን ግን በነፍስ ላይ ነው፡፡ ንጉሥ ይቅር ቢል የገንዘብን ዕዳ ነው፤ ካህን ይቅር ሲል ግን የበደል የኃጢአት ዕዳን ነው፡፡

ንጉሥ ያዝዛል፤ ካህን ግን ያስተምራል ይዘክራል፡፡ ንጉሥ ያስገድዳል፤ ካህን ግን ነጻ ፈቃድን ያያል፡፡

ንጉሥ ቁሳዊ የጦር ዕቃ መሣሪያ አለው፤ ካህን ግን ረቂቅ (መንፈሳዊ) የጦር ዕቃ መሣሪያ አለው፡፡ ንጉሥ የጦር ዕቃ መሣሪያውን ቢሰብቅ አንገዛም ብለው ባመፁት (እንዲሁም ከወራሪዎች ሥጋውያን ደማውያን) ላይ ነው፤ ካህን ግን ውጊያው ከጨለማ አበጋዞች ከአጋንንት ጋር ነው፡፡

ስለዚህ ሥልጣነ ክህነት ከሥልጣነ መንግሥት ይበልጣል፡፡ እንዲህም በመኾኑ ንጉሥ አንገቱን ለካህናት እጅ ያጎነብሳል፡፡

አባቶች ካህናትን እግዚአብሔር ይጠብቅልን !

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
1.8K views£itsum, edited  09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 20:39:56 በትግራይ ክልል ከሚገኙ አባቶች ጋር ውይይት
ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቀቀ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በግንቦት ወር ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
ባካሔደው የርክበ ካህናት ጉባኤ በትግራይ ክልል ከሚገኙ አባቶች ጋር የሚደረገው ውይይት ቀደም ሲል በቋሚ ሲኖዶስ በተሰየመው የልዑካን ቡድን አማካኝነት በአስቸኳይ እንዲቀጥል መወሰኑ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ኮሚቴው ውይይቱን በተሳካ ሁኔታ ለማካሔድ የሚያስችለውን በእቅድ ላይ የተመሰረተ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሲያከናውን የቆየ ሲሆን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ውይይቱ በተሳካ ሆኔታ መካሔድ የሚችልበትን ሁኔታ እንዲያመቻች በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተጻፈ ደብዳቤ ጥያቄውን አቅርቧል።የልዑካን ቡድኑ አባላትም ከቅዱስ ፓትርያርኩ የተጻፈውን ደብዳቤ በአካል በመገኘት ለክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት በማቅረብ ከሚመለከታቸው የክልሉ የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር የክልሉ ጊዚያዊ መንግስት ለውይይቱ መሳካት በሚያደርገው ድጋፍ ዙሪያ ውይይት በማድረግ ተመልሷል።

ስለሆነም ለክልሉ መንግስት በቀረበው ጥያቄ መሰረት ሁለቱም አካላት በሚያመቻቹት ጊዜና ቦታ ውይይቱ የሚካሔድ ይሆናል።

በዚህም መሰረት የጠቅላይ ቤተክህነት ልዑካን ቡድን ውይይቱን ውጤታማ ለማድረግ ይቻል ዘንድ እስከ አሁን ያከናወናቸውን ተግባራትና ወደፊት ውይይቱን ስኬታማ በሆነ መንገድ ማካሔድ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ሰኞ ሰኔ ፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ይፋዊ መግለጫ ይሰጣል።መግለጫውን ተከትሎም ጉዳዩ በቀኖና ቤተክርስቲያን መሰረት የመጨረሻ እልባት እንዲያገኝ በፍጥነት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በመግባት በሒደቱ የሚመዘገቡ ለውጦችን ሁሉ በመገናኛ ብዙሃን የሚያሳውቅ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሰኔ ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
880 views£itsum, 17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 17:35:21
ከአንተ ፡ ማን ቀደመ
  ነኝ ያልከው አንተ ፤
     እርሱን ማን ገደመ ።
በዚያ ፡ የህሊና ፡ ሰላም
   ዘር የለም ፡ የስጋ ደም ።
ላይጠልቅ ፡ እንደ  ወጣ
   ፀሐይ ፡ ፍቅር  ላትጠግብ ፡ ጠጣ።
  ባሕር ነው ፡ ውቅያኖስ
እኔነትን ውጦ ፡ ሰውነት ሲቀመስ ። !!
    ሰው ከመሆን በፈት
       ተሰርተህ ስትቆም ከአምላክ ፈት ፤
በምንነት ፡ ጠራህ?
   የትኛውን ጎሳ ነኝ ፡ ብለህስ ሰማህ ። ?
ሰው ነው መጠሪያ
    አልሆንከውን ሆንኩኝ
    ያለከው ፡ አንተ ነህ እርያ።
ሰውነት ፡ ቀለለ
   መልአክ መሆን ምችል ፤
ፍቃድህን ሸጥከው
        ለጨለማ ፡ ምስል ።

ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ሰኔ 3 2015 ዓ.ም

https://www.facebook.com/100035541834298/posts/974895263705192/?app=fbl
1.2K views£itsum, edited  14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 13:35:52 በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፱ ኤጲስ
ቆጶሳትን መልምሎ እንዲያቀርብ የተመረጠው
ኮሚቴ ሥራውን በማከናወን ላይ ነው።
****
ሰኔ ፪ ቀን ፳፻ ፲ወ ፭ ዓ.ም
****
አዲስ
አበባ -ኢትዮጵያ
"""""""""""""""""""""
የግንቦት ፳፻ ፲፭ ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ በኦሮሚያና በደቡብ ኢትዮጵያ የሚሾሙ ፱ አባቶችን መልምሎ የሚያቀርብ ኮሚቴ ማቋቋሙ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ የተቋቋመው ኮሚቴ ግንቦት ፳፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የመጀመሪያ ስብሰባውን በተሳካ ሁኔታ ያከናወነ ሲሆን ግንቦት ፳፰ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ባኬሔደው ስብሰባ የኮሚቴው ሰብሳቢ እንዲሆኑ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን የመረጠ ሲሆን የኮሚቴው ጸሐፊ በመሆን እንዲያገለግሉ ደግሞ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን በመምረጥ ሥራውን በይፋ ጀምሯል።

ኮሚቴው ምልመላውን ለማከናወን የሚያስችለውን መስፈርት በማዘጋጀት ከሐሙስ ከሰኔ ፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ጀምሮ ጥቆማ በማከናወን ላይ ይገኛል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ርም በአስረጂነት በኮሚቴ ውስጥ የሚሳተፉ ሲሆን ለኤጲስ ቆጶስነት የሚታጩ መነኮሳትም በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተሳትፎ በመጠቆም ላይ ናቸው።


https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
2.0K views£itsum, edited  10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ