በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፱ ኤጲስ ቆጶሳትን መልምሎ እንዲያቀርብ የተመረጠው ኮሚቴ ሥራውን በማከናወን ላይ ነው። **** ሰኔ ፪ ቀን ፳፻ ፲ወ ፭ ዓ.ም **** አዲስአበባ -ኢትዮጵያ """"""""""""""""""""" የግንቦት ፳፻ ፲፭ ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ በኦሮሚያና በደቡብ ኢትዮጵያ የሚሾሙ ፱ አባቶችን መልምሎ የሚያቀርብ ኮሚቴ ማቋቋሙ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ የተቋቋመው ኮሚቴ ግንቦት ፳፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የመጀመሪያ ስብሰባውን በተሳካ ሁኔታ ያከናወነ ሲሆን ግንቦት ፳፰ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ባኬሔደው ስብሰባ የኮሚቴው ሰብሳቢ እንዲሆኑ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን የመረጠ ሲሆን የኮሚቴው ጸሐፊ በመሆን እንዲያገለግሉ ደግሞ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን በመምረጥ ሥራውን በይፋ ጀምሯል። ኮሚቴው ምልመላውን ለማከናወን የሚያስችለውን መስፈርት በማዘጋጀት ከሐሙስ ከሰኔ ፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ጀምሮ ጥቆማ በማከናወን ላይ ይገኛል። የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ርም በአስረጂነት በኮሚቴ ውስጥ የሚሳተፉ ሲሆን ለኤጲስ ቆጶስነት የሚታጩ መነኮሳትም በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተሳትፎ በመጠቆም ላይ ናቸው። https://t.me/OrthodoxAmero https://t.me/OrthodoxAmero https://t.me/OrthodoxAmero 2.0K views£itsum, edited 10:35