Get Mystery Box with random crypto!

ከአንተ ፡ ማን ቀደመ   ነኝ ያልከው አንተ ፤      እርሱን ማን ገደመ ። በዚያ ፡ የህሊና ፡ | ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

ከአንተ ፡ ማን ቀደመ
  ነኝ ያልከው አንተ ፤
     እርሱን ማን ገደመ ።
በዚያ ፡ የህሊና ፡ ሰላም
   ዘር የለም ፡ የስጋ ደም ።
ላይጠልቅ ፡ እንደ  ወጣ
   ፀሐይ ፡ ፍቅር  ላትጠግብ ፡ ጠጣ።
  ባሕር ነው ፡ ውቅያኖስ
እኔነትን ውጦ ፡ ሰውነት ሲቀመስ ። !!
    ሰው ከመሆን በፈት
       ተሰርተህ ስትቆም ከአምላክ ፈት ፤
በምንነት ፡ ጠራህ?
   የትኛውን ጎሳ ነኝ ፡ ብለህስ ሰማህ ። ?
ሰው ነው መጠሪያ
    አልሆንከውን ሆንኩኝ
    ያለከው ፡ አንተ ነህ እርያ።
ሰውነት ፡ ቀለለ
   መልአክ መሆን ምችል ፤
ፍቃድህን ሸጥከው
        ለጨለማ ፡ ምስል ።

ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ሰኔ 3 2015 ዓ.ም

https://www.facebook.com/100035541834298/posts/974895263705192/?app=fbl