2023-04-22 11:07:27
--------- ቅዳሜ † ቅዱሳት አንስት --------
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ……… በዓቢይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን ………….አግአዞ ለአዳም
ሰላም ………………………እም ይእዜሰ
ኮነ………………………………ፍስሐ ወሰላም
••••••••••••••••••• † •••••••••••••••••
ከትንሳኤ በኋላ ያለው እለተ ቅዳሜ ቅዱሳት አንስት ተብሎ ይጠራል። ይህም ስያሜ በስቅለት ዕለት በልቅሶና በዋይታ የሸኙትን ፤ (ሉቃ. ፳፫፥፳፯) በዕለተ ትንሣኤ ሽቱና አበባ ይዘው ወደ መቃብር የገሰገሱትን ፤ ከሁሉም ቀድሞ ጌታችን በዕለተ ሰንበት ተነሥቶ ለተገለጸላቸው ማርያም መግደላዊት ፤ የታናሹ ያዕቆብ እና የዮሳ እናት ማርያም፤ የዘብዴዎስም የልጆቹ እናት ሰሎሜንም መታሰቢያ ለማድረግ ነው። ከዚህ ባለፈም የቅድስና ስራ የሰሩ ሴቶች ሁሉ በዚህ ዕለት ይታሰባሉ።
«ከሳንምንቱ በመጀመሪያዩቱ ቀን ያዘጋጁትን ሽቶ ይዘው እጅግ ማልደው ወደ መቃብሩ ሄዱ ፤ ሌሎች ሴቶችም አብረዋቸው ነበሩ (ሉቃ. ፳፬ ፥ ፩ )፡፡ በዚህም ምክንያት ቤተክረስትያናችን ዕለቱን ቅዱሳት አንስት ብላ ሰይመዋለች።
ከትንሳኤውም በፊት ከትንሳኤውም በኋላ የሴት ቅዱሳንን የፅድቅ ስራ በዚህ እለት እንዘክራለን። ሴት ቅዱሳን ከትንሣኤ እስከ መስቀል ፍለጋ ድረስ የፅድቅ ስራቸው ሲታወስ ይኖራል።
በመጀመሪያዋ ሔዋን ሞት መጣ ፤ በሁለተኛዋ ሔዋን በድንግል ማርያም አለም ዳነ። የመጀመሪዋ ሔዋን የሞትን ዜና በጆሮዋ ሰማች ፤ እናታችን ድንግል ማርያም ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ የሚለውን የቅዱስገብርኤልን ብስራት ሰማች። የአለም መድኃኒት ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆነ። መድኃኔዓለም ከዳዊት ልጅ ከሴት ተወለደ። ለፍጥረቱ መዳን ተራበ ፥ ተጠማ ፥ መከራን ተቀበለ ፤ ስጋውን ቆረሰ ደሙን አፈሰሰ። በመስቀል ተሰቅሎ ሞተ ፣ ሞትንም ድል አድርጎ ተነሳ!
ቅድስት መግደላዊት ማርያም የጌታን ትንሳኤ ለመመስከር ተመረጠች። ለሐዋርያት ለአለም ትንሳኤውን አበሰረች። ከፈርኦን አምልጠው የኤርትራን ባህር ሲሻገሩ የሙሴ አህት ማርያም ከበሮ አንስታ እንደ ዘመረች ዛሬም የቅድስት መግደላዊት ማርያምን የትንሣኤ ብስራት የሰሙ ሴቶች 'ንሴብሆ' ብለው እየዘመሩ ትንሣኤውን ለአለም ያበስራሉ።
የመስቀሉ ፍቅር ከሁሉ የበዛላት ቅድስት እሌኒ በግፍ ተቀብሮ የኖረውን መስቀሉን አገኘች። የመስቀሉን ዜና ለአለም አበሰረች።
በዚህ እናትነት በዚያ ቅድስና ሰማዕትነት ምንኩስና ድንግልና ለሴቶች የተሰጠ ድንቅ የፈጣሪ ስጦታ ነው።
ቅዱሳኑ ሁሉ የእናቶቻችን ፍሬ ናቸው። ነብያት ፣ ሐዋርያት ፣ ጳጳሳት ፣ ሰማዕታት ፣ ደናግል ፣ መነኮሳት ፣ ቅዱሳን ከእናቶቻችን ተገኙ። ከእናትነት አልፈው ቅድስት ፣ ሰማዕት ፣ ደናግል ፣ መነኮሳያት ለመሆን የተመረጡ እናቶች በአለም እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ እናታችን ቅድስት እሌኒ ፣ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ፣ ቅድስት መስቀል ክብራ……..እናትነትን ከቅድስና ጋር ያስማሙ ናቸው። ከሰማዕታት የትውልዱ መመኪያ እናታችን ቅድስት አርሴማ አንዷ ናት። ሌሌችም ብዙ....ቅድስት ዲቦራ ፣ ቅድስት ሶፍያ...
በመጀመሪያዋ ሔዋን ሞት መጣ፣ በሁለተኛዋ ሔዋን በድንግል ማርያም አለም ዳነ! ዛሬም አለም ያለ ድንግል ማርያም አይድንም! በጥንት ዘመን እንደ ጥፋተኛ ይታዩ የነበሩት ሔዋኖች በሙሉ በድንግል ማርያም እንባቸው ታበሰ! ለምን? የፍጠረት ሁሉ መመኪያ ድንግል ማርያም ስለሆነች። የሁሉን መጋቢ ጡቶቿን አጠባችው። ሁሉን የያዘውን በክንዶቿ አቀፈችው ፤ በጀርባዋ አዘለችው። ፍጥረት በፊቱ መቆም የማይችለውን ሳመችው። እንዲሁም አለም በተስፋ የሚጠብቀውን ዳግም ምጽዓት ሳትጠብቅ ድንግል ማርያም ከሞት ተነስታ አርጋለች።
ከጌታ ትንሣኤ በኋላ ባለው በዚህ በዕለተ ቅዳሜ የቅድስና ስራ ያላቸው ሴቶች በሙሉ ይታሰባሉ። ተዋህዶ ለሴቶች ክብር እንደሌላት የሚናገሩ ሁሉ የሴቶች ቀን ከመከበሩ አስቀድማ ቤተ ክርስቲያናችን የቅዱሳን ሴቶች መታሰቢያ ዕለት አላት።
ዛሬስ? የእመቤታችን ሴቶች ልጆች ህይወታችሁ ማንን ይመስላል? የእመቤታችንን እውነተኛ ልጆች ህይወታችሁ እንዲሆን ቃልኪዳኗ ይርዳን ይርዳችሁ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
Facebook Link follow ያድርጉ
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede
1.4K views£itsum, edited 08:07