Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxamero — ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxamero — ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
የሰርጥ አድራሻ: @orthodoxamero
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.89K
የሰርጥ መግለጫ

ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ሀሳብ ካሎዎት @Fisumkeb
facebook Link...
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-18 13:08:47 ማክሰኞ † ቶማስ
-----------------------------
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ……… በዓቢይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን ………….አግአዞ ለአዳም
ሰላም ………………………እም ይእዜሰ
ኮነ………………………………ፍስሐ ወሰላም
••••••••••••••••••• † •••••••••••••••••
እንደ ኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የበዓላት ቀኖና መሰረት ከትንሣኤ በኋላ ያለው ሁለተኛው ዕለተ ማክሰኞ "ቶማስ" በመባል ይጠራል።

ቶማስ ሐዋርያ ሲሆን፣ ቶማስ ማለት ‹‹ፀሐይ›› ማለት ነው። ከክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ ቅዱስ ቶማስ በጦር የተወጋ ጎኑን፤ በቀኖት የተቸነከረው እጁንና እግሩን ካላየሁ አላምንም በማለቱ ክርስቶስም «ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ ፤ እጅህንም አምጣና ወደ ጎኔ አግባ፤ እመን እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን» ብሎታል።

ቶማስም «ጌታዬ አምላኬም»፤ ብሎ በመለሰ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስም «ስለ አየኸኝ አመንህን? ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው» አለው። (ዮሐ ፳፥፳፯-፳፱)፤ ቶማስ የጌታን ፍቅር ተገንዝቦ ትንሣኤውን ስላመነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዕለቱን ቶማስ ብላ ታስበዋለች።

ዲዲሞስ የተባለ ከአሥራ አንዱ ደቀ መዛሙር አንዱ ቶማስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዝግ ቤት ገብቶ «ሰላም ለሁላችሁ ይሁን» ባላቸው ጊዜ ከእርሳቸው ጋራ አልነበረም»። ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ (ማቴ. ፲፥፪-፫) ቶማስ በአራማይክ ዲዲሞስ በግሪክ መንታ ማለት ነው፤ (ዮሐ. ፳፥፳፬)፡፡

ቶማስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በፋርስና በሕንድ ወንጌልን እንዳስተማረ ይነገራል። ለቶማስ ጎኑን እንዲዳስስ የፈቀደው ለሌሎችም ቅዱሳን ሐዋርያት የተቸነከረውን እጅና እግሩን ያሳየው ካህናት ሥጋውና ደሙን እንዲፈትቱ ነው፤ ዮሐንስም በእጃችን ዳሰስነው ብሏል፤ (ሉቃ. ፳፬፥፴፱)፡፡

ለማርያም መግደላዊት ግን የተነሣ ዕለት አትንኪኝ ማለቱ ለሴቶች ሥጋውን ደሙን መፈተት አልተፈቀደም ሲል ነው ብለው ሊቃውንት ያትታሉ፤ «አትንኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሂጅና፡- ወደ አባቴ÷ ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬ÷ ወደ አምላካችሁም አርጋለሁ አለ ብለሽ ንገሪአቸው» አላት፤ (ዮሐ. ፳፥፲፯)።

የሐዋርያ ቶማስ መታሰቢያ በዳግመ ትንሣኤ ላይ የሚነሳ ቢሆንም አባቶች በበዓል ላይ በዓል እንዳይደራረብ ብለው ከትንሣኤ በኋላ ባለው በዕለተ ማግሰኞ ቶማስ ተብሎ እንዲጠራ ስርዓት ሰርተውልናል።

የአባቶቻችን በረከት ይደርብን በእውነት። በዓሉንም በዓለ ደስታና በዓለ ፍስሐ ያድርግልን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
መልካም ቀን!!!!

https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero

Facebook Link   follow ያድርጉ
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede
404 views£itsum, edited  10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 08:41:36 መንታ ወንድና ሴት ቢወለዱ ክርስትና እንዴት ይነሳሉ?

ሴት በወር አበባ ጊዜስ?

ወንድ ህልመ ሌሊት ቢያጋጥመውስ?

ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ዓንፃር መልስ ይመልከቱ
895 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 08:26:02
ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ እንዳላቸው ያውቃሉ 


የዕለተ ሰኞ ስያሜ

የዕለተ ማክሰኞ ስያሜ

የዕለተ ረቡዕ ስያሜ

የዕለተ ሐሙስ ስያሜ

የዕለተ ዓርብ ስያሜ 

የዕለተ ቅዳሜ ስያሜ

የዕለተ እሁድ ስያሜ

ሁሉንም ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ

https://t.me/+RkglPUfilfs4MDFk
https://t.me/+RkglPUfilfs4MDFk
934 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 21:04:36 ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ እንዳላቸው ያውቃሉ 


የዕለተ ሰኞ ስያሜ

የዕለተ ማክሰኞ ስያሜ

የዕለተ ረቡዕ ስያሜ

የዕለተ ሐሙስ ስያሜ

የዕለተ ዓርብ ስያሜ 

የዕለተ ቅዳሜ ስያሜ

የዕለተ እሁድ ስያሜ

ሁሉንም ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ

https://t.me/Amedehayemanote
https://t.me/Amedehayemanote
https://t.me/Amedehayemanote
386 views£itsum, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 14:41:02 ~ሰኞ- ማዕዶት~

ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡
ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

✞ እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡


https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero

Facebook Link   follow ያድርጉ
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede
1.9K views£itsum, edited  11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 12:41:36
ተነስቷል ጌታችን


ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ


https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero

Facebook Link   follow ያድርጉ
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede
2.7K views£itsum, edited  09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 20:39:11 ++ ‹‹ ትንሣኤና ሕይወት ›› ++

ሞት ህይወትን ይየዘው ዘንድ አልተቻለውም ነብሳትን ከመቃብር ያግዝ ሲነጥቅ የነበረው ሞት በክርስቶስ ሞት ግን ነብሳትን እንዲነጠቅ ሆነ ። ውስን ያልሆነ ሕይወት ክርስቶስ በፍጥረቱ ብቻ የተወሰነው ወደ ሆነው ሞት ሄደ ውስኑ ሞት ማይወሰነውን ህይወት ክርስቶስን ይይዘው ዘንድ አልቻለውም ። ትንሣኤና ሕይወት እርሱ ነውና ዮሐ 11፥25 ። በታተመች ድንግል ማኅፀን በጠባብ ደረት የተወሰነ ድንግልናዋን ሳያጠፍ የተወለደ በታተመ በተዘጋ መቃብርም ክፈቱልኝ ሳይል ወጣ ። ሞት በኃያሉ ኃይሉን አጣ ። ትንሣኤ ፦ *መነሣት* ማለት ሲሆን ፍሲካ ፦ *ማለፍ* (መሻገር) ማለት ነው ። እስራኤል ስለልጆቻቸው ፍንታ በግ ሰውተው የበጉን ደም በራቻው ላይ በመቀባት ሞት እንዳለፈላቸው የእኛም ሞት በክርስቶስ ሞት እንዲያልፍልን ሆኗል የበጉን ደም ያልቀቡት ግብፃውያን ግን የበኩር ልጆቻቸውን ሞት ወስዶ ነበር ። በክርስቶስ ሞት ግን ሁሉን አጥቷል ። *ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም* ሁሉን የመነጠኩን የማጣቱን ምሬት ሲገልፅ ‹‹ ሞት እንዲህ አለ ፦ ወደ ሙሴ ዘመን ብመለስ ሳይሻለኝ ይሆን ? ሙሴ እኮ በዓልን ደግሶልኝ ነበር ። በግብፅ ፍሲካ የታረደው በግ ከእያንዳንዱ ግብፃዊ ቤት የበኩር ልጅ ሰጥቶኝ ነበር በሙት ላይ ሙት በሲኦል ደጅ ተከምረውልኝ ነበር ይኅኛው የፍሲካ በግ (ክርስቶስ) ግን ሲኦልን በዘበዘው ሲኦልን ከእጄ ነጥቆ አወጣቸው›› ። እያለ ይገልፃል ። ትንሣኤው እኛ ክርሰቲያንኖች ከሞት በኋላ ህይወት እንዳለ ምናምንበት ነው ። ጥቂት የምድር መከራዎቻችንን ሁሉ በትንሣኤው ተስፍ እንታገሳቸዋለን ሮሜ 8፥18 ። የክርስቶስ ትንሣኤ በክርስቶስ ክርስቲያን ለተሰኘን ለእኛም ትንሣኤ ማስረጃ ስለሆነ ።
‹‹ ሙታን የማይነሱ ከሆነ ክርስቶስ አልተነሳም ክርስቶስ ካልተነሳ እምነታቹ ከንቱ ናት ›› እንተደተባልን ። (1ኛ ቆሮ 15፥16) የሃይማኖት ፍፃሜው ትንሣኤ ነውና ። ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ ማስረጃ ምንድ ናቸው ከተባልም አስቀድሞ በብሉይ በትንቢት በብዙ የተነገሩ እንዲሁም እራሱ ክርስቶስ ስለራሱ ትንሳኤ የተናገራቸው ይሆናሉ ፦ “እግዚአብሔርም ዮናስን የሚውጥ ታላቅ ዓሣ አሰናዳ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣው ሆድ ውስጥ ነበረ።” ዮናስ 2፥1
ዮናስ ሶስት መዓልት እና ሌሊት ህያው ሆኖ በአሳ ሆዱ ውሰጥ መቆየቱ ህያው የሆነ ክርስቶስም በመቃብር ሶስት ቀን የማደሩ ምሳሌ ነው ። ክርስቶስም ፈሪሳውያን ምልክት ሽተው ለጠየቁት ጥያቄ ሲመልስ “ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።” ዮናስ በአሳ አንባሪ ሆድ ውስጥ ሶስት ቀን እና ሌሊት እንደ ቆየ እንዲሁ የሰው ልጅም በምድር ልብ ውስጥ ይኖራል ብሎ ሰው የሆነ እርሱ በመቃብር ሚቆይበትም ተናግሮ ነበር ማቴዎስ 12፥39 ።

ክርስቶስ ለምንድ ነው በመቃብር ሶስት ቀን ብቻ የቆየው ለምንስ ከዛ በላይ ወይም በታች ሁለት አንድ ቀን ብቻ አድሮ ያልተነሳው ሚሉ ጠያቂዎች ይኖራሉ ። ለዚህ ምላሽ ፦ በእፀ መስቀል ላይ ከድካሙ የተነሳ ተጠማሁ ባለ ጊዜ
‹‹ ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ፥ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ ›› ። መዝ 69-21 ያለው ቃል ይፈፀም ዘንድ በሰፍነግ ሆምጣጤ አጠጥተውት ነበር ። አይሁድ በአንድ ቀን ከመቃብር ቢነሳ ያጠጣነው አስክሮት አደንዝዞት ነው እንጂ በእውነት ሞቶ አይደለም ይሉ ስለ ነበረ ምክንያት ያሳጣቸው ዘንድ ቶሎ ከመቃብር አልተነሳም ። በሶስተኛውም ቀን በመቃብር ካደረ በኋላ የተነሳው በእርሱ መፍረስ መብስበስ እንደሌለ ያሳውቅ ዘንድ ነበር ‹‹ ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንመበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም ›› ። መዝ 16፥10 ዳዊትም ስለራሱ ሳይሆን ስለ ክርስቶስ ሳይፈር ከመቃብር መነሳት የተናገረው በክርስቶስ ትንሣኤ ተረጋገጠ ። በኋላም አስቀድሞ ተናግሮ የታወቀ የተነገረ በመሆኑ ተናግሮም ታውቆም ብቻ አልቀረ ውሸት ይባላልና በኋላም ሲናሳ በዚህ ታውቋል ። ዓለምን
ሁሉ በሚያድን፡ትንሣኤው፡እማፀናለሁ ። እኔንም ፡ከመውደቅ፡ያነሳኝ፡ዘንድ፡ከመቀጥቀጥ፡ልምሾም፡ከመሆን፡ያድነኝ ፡ዘንድ እፈቅዳለሁ። (አርጋኖን አባጊዮርጊስ ዘጋስጫ)** _ ሙታን እንደ ሚነሱ ተስፍ ለሰጠን መሲህ ምስጋ ይገባል እርሱ ሞትን አጥፍቶ ተነስቷል እና በሞት የበሰበሰው ዳግመኛ እንደሚታደስ ለሰው ልጅ ማረጋገጫ ሰጠ ። (ድርሳነ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ )

መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንላቹሁ

ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ሚያዝያ 7 2015 ዓ.ም
ኢትዮጵያ


Facebook Link   follow ያድርጉ
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede
4.0K views£itsum, edited  17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 19:35:18 ሞ-አንበሳ


ሞ-አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ
ንጉሰ ነገስት የታረደ በግ ፍሪዳ
የሞት አበጋዝ ይዞት ሊያስቀረው ያልቻለ
ከአማልኩት እንደ ኢየሱስ ማን አለ

አዝ

በእግዚአብሔር እና በሰው መካከል የነበር
የጥልቁ አሰራር በግዞት ያስቀረን ቀንበር
ዘመኑ ሲደርስ ክርስቶስ ከሴት ተወልዶ
ህይወትን ሰጠን በመስቀል ጥልን አዋርዶ

አዝ

ጥልቁ ተመታ ሲኦልም ተመዘበረ
አርነት ወጣን ዲያቢሎስ ሕልሙ ተሻረ
ሞት ተሸነፈ ሀይሉ ብርታቱ ተሻረ
የሞቱ ዶሴ በሞቱ ተቀዳደደ

አዝ

ሂዱ ጎልጎታ ተነስቷል መቃብሩን እዩ
ምስክር ናቸው እንኳን ሰው ምድር ሰማዩ
የጨለማው ገዥ በትንሳኤው ሀይል ተውጧል
ፅልመት ተገፎ የብርሃን ጨራ ፈንጥቋል

አዝ

ከእርሱ ጋር ለሞትን ከእርሱ ጋር ትንሳኤ አለን
ገና ባርያም በአብ ቀኝ እንከብራለን
ህይወት በዝቶልን ልንዘምር የማይቆም ዜማ
አለን ቅጥሩ በጉ ባለበት ከተማ


ዘማሪ ዘላለም ይንገስ

https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero

Facebook Link   follow ያድርጉ
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede
2.8K views£itsum, edited  16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 19:33:16 በመቃብር የለም


በመቃብር የለም ሞትን ድል ነስቷል
በዋጋ እኛን ገዝቶናል
ዘምሩ ለክብሩ ከበሮውን ምቱ
ተነስቷል እየሱስ አዲስ ሆኗል ፍጥረቱ
ተነስቷል ክርስቶስ አዲስ ሆኗል ፍጥረቱ

አዝ

ፍሲካው ታርዷል ውጡ ከመቃብር
ሰማይን ከፍቶ ወርዷል እዩ ፍቅር
ወደቆምንበት ክብር ደርሰናል እና
ሀሌሉያ ነው ቅኔው ለእርሱ ምስጋና

አዝ

አብ የተከለው ወገን በቅዱሱ እርሻ
ወደበጉ ሰርግ ሆኗል የኛ መድረሻ
ነጩ ልበሱ ውጡ ተነስቷል በሉ
ፈታቹሁ ይሳል ጌታ ከነመስቀሉ

አዝ

በንፁደሙ ገዛን ከሞት አለቃ
አመተ ምህረት ሆነ ኩነኔው በቃ
ሰላማች ነው እና መድኃኒዓለም
መቅሰፍት አለፈ በእርሱ ሆነ ሰላም

አዝ

መቃብር ገብቶ ሞቶ ከወደደን
አለን ምስጋና ለእርሱ ደስ እያለን
የሰማዩን ደጅ አፍቶ ገባን ከእርሱቱ
ወራሽ አረገን ልጆች በመስቀል መቶ


ዘማሪ ዲያቆን ሳምሶን ነጋሽ

https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero

Facebook Link   follow ያድርጉ
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede
2.5K views£itsum, edited  16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 19:08:40 30 ደቂቃ ብቻ ይታገሱን  "follow"

ዛሬ ማታ በዚህ ዓመት ለትንሳኤ የወጡ አዲስ ዝማሬዎችን ይዤላቹሁ እመጣለሁ ይጠብቁኝ ።

1:30 ላይ ይለቀቃል ቶሎ follow
Facebook Link   follow ያድርጉ
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede
2.4K views£itsum, edited  16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ