የሰርጥ አድራሻ:
ምድቦች:
ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች:
44.89K
የሰርጥ መግለጫ
ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ሀሳብ ካሎዎት @Fisumkeb
facebook Link...
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede
Ratings & Reviews
Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.
5 stars
1
4 stars
1
3 stars
0
2 stars
1
1 stars
0
የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2
2023-06-08 19:04:19
ለልጅዎ የግእዝ ስም ማውጣት ከፈለጉም እነሆ
ግእዝ
__አማርኛ
፩) መዓርዒር
__ጣፋጭ
፪) አሜር
__ፀሐይ
፫) አርያም
_ሰማይ
፬) አምኃ
_እጅ መንሻ
፭) ብሥራት___የምስራች
፮) ሰሎሜ
_ሰላም
፯) አሜን
__እውነት/ይሁንልኝ
፰) ሠዊት
__እሸት
፱) ጸገየ
___አበበ
፲) አስካል____ፍሬ
፲፩) ልዑል____ከፍ ያለ
፲፪) ሣህሉ____ይቅርታው
፲፫) ቀጸላ
_አክሊል
፲፬) ሐመልማል___የለመለመ
፲፭) ከሃሊ
_የሚችል ቻይ
፲፮) ጸዳሉ
_መብራቱ
፲፯) ፈትለ ወርቅ____የወርቅ ፈትል
፲፰) ፊደል
_ፊደል
፲፱) ማኅተም____ማተሚያ
፳) ሥዩም
__የተሾመ ሹም
፳፩) ስብሐት____ምስጋና
፳፪) ስቡሕ
_ምስጉን
፳፫) ተቅዋም
_መቅረዝ
፳፬) ንጹሕ
_የነጻ
፳፭) ሰላማ
__ሰላም
፳፮) አዳም
__ያማረ
፳፯) ዳግም
_የደገመ
፳፰) ግሩም
_ተፈሪ
፳፱) ጥዑም____የሚጣፍጥ
፴) ፍጹም
__የተቀባ
፴፩) ይኄይስ____ተሻለ
፴፪) ሐዳስ/ሐዲስ___አዲስ
፴፫) ሕዳሴ
__መታደስ
፴፬) ሰንኮሪስ
_መምህር
፴፭) መቅደስ
_ማመስገኛ
፴፮) ሞገስ
__ባለሟል የተወደደ
፴፯) ትዕግሥት
_መቻል
፴፰) ንጉሥ
__የነገሠ
፴፱) ወራሲ
__ወራሽ
፵) ውዳሴ
__ምስጋና
፵፩) ጌራወርቅ____የወርቅ ሥራ
፵፪) ማኅደር
_ማደሪያ
፵፫) ምሕረት
_ይቅርታ
፵፬) መሓሪ
__ይቅር ባይ
፵፭) ሠምረ
__ወደደ
፵፮) ሥሙር
_ተወዳጅ
፵፯) ሥምረት____መወደድ
፵፰) ነጸረ
__ተመለከተ
፵፱) ምሥጢሩ____ምሥጢሩ
፶) መራሒ____መሪ
፶፩) ፍሥሓ
_ደስታ
፶፪) አእመረ____አወቀ
፶፫) አእምሮ____እውቀት
፶፬) ፍቅር
__መውደድ
፶፭) ክቡር
__የከበረ
፶፮) ደብሩ
__ተራራው
፶፯) ተግባር
_ሥራ
፶፰) ረቂቅ
__ረቂቅ
፶፱) መብረቁ____መብረቁ
፷) ነጸብራቅ
__ነጸብራቅ
።
፷፩) ይባቤ
___እልልታ
፷፪) ጥበቡ
___ብልሃቱ
፷፫) መሠረት
__መሠረት
፷፬) ብሑት
___ስልጡን
፷፭) ትሕትና
___ትሕትና
፷፮) ተከሥተ
__ተገለጠ
፷፯) ሃይማኖት
_ሃይማኖት
፷፰) በየነ
__ፈረደ
፷፱) መኰንን____ገዢ
፸) በጽሐ
__ደረሰ
፸፩) መስፍን____የሚገዛ
፸፪) ምስፍና____ግዛት
፸፫) ክርስቲያን____ክርስቲያን
፸፬) ወሰን
__ድንበር
፸፭) መዋዒ
_አሸናፊ
፸፮) ትንሣኤ
_መነሳት
፸፯) ነቅዐ ሕይወት
_የሕይወት ምንጭ
፸፰) ገዛኢ
__ገዢ
፸፱) ምሕርካ ክርስቶስ___የክርስቶስ ምርኮ
፹) ባራኪ____የሚባርክ
፹፩) መልአክ____አለቃ
፹፪) በረከት____በረከት
፹፫) ህላዌ
_መኖር
፹፬) ኂሩት
_ቸር የሆነች
፹፭) ልባዌ
_ማስተዋል
፹፮) ቤዛዊት
_ያዳነች የምታድን
፹፯) ስርጋዌ____ሽልማት
፹፰) ስርጉት____የተሸለመች
፹፱) ተስፋ
_ተስፋ
፺) ኬንያ
__ብልሃተኛ
፺፩) ኖላዊ
__ጠባቂ
፺፪) መርዓዊ____ሙሽራ
፺፫) ማዕዶት____መሻገሪያ
፺፬) ወልታ____መከታ/ጋሻ
፺፭) ሐዋዝ____ያማረ
፺፮) ግእዛን____ነጻነት
፺፯) ሕሊና____ሕሊና
፺፰) ማኅሌት____ምስጋና
፺፱) ኅሩይ
__ምርጥ
፻) ሲሳይ
__ምግብ
፻፩) ሠናይ____ያማረ
፻፪) ፈታሒ____የሚፈርድ
፻፫) ሐሴት____ደስታ
፻፬) ትርሲት
_ሽልማት
፻፭) ተዋናዪ
_ተጫዋች
፻፮) ዐቢይ
___ከፍ ያለ
፻፯) ትውፊት
_ስጦታ
፻፰) ኃያል
_የበረታ
፻፱) ጽጌ
__አበባ
፻፲) ፍሬሕይወት____የሕይወት ፍሬ
፻፲፩) ምዕዳን
_ምክር
፻፲፪) ንኡድ
___ያማረ
፻፲፫) ነገደ
___ሄደ
፻፲፬) ነጎድጓድ____ነጎድጓድ
፻፲፭) ጸዓዳ
_ነጭ
፻፲፮) ሠረጸ
_በቀለ
፻፲፯) ደምፀ____ተሰማ
፻፲፰) ሮሐ
_ወለወለ/አራገበ/አናፈሰ
፻፲፱) ናርዶስ
_ሽቱ
፻፳) እፀ ሕይወት___የሕይወት እንጨት
።
በትረማርያም አበባው (በነገራችን ላይ በትረ ማርያም ማለት የማርያም ወገን ማለት ነው። በትር ወገን ተብሎ እንደሚተረጎም አስተውል)
።
በትረማርያም አበባው
2.8K views£itsum, edited 16:04
2023-06-07 22:41:59
+++ የጀማሪ ጠባይ +++
መንፈሳዊ ሕይወትን ገና ስትጀምረው ለፍጹምነት ጥቂት የቀረህ ያህል ይሰማሃል። አንተ ጋር ያለው ደስታ እና ሰላም ሌሎች ጋር የሌለ ይመስልሃል። በዚህች ሁከት በሞላባት ዓለም አንተ ብቻ ክርስቶስን እንዳገኘኸው ታስባለህ። የቀረው ሕዝበ አዳም እንዲሁ በከንቱ ሲርመሰመስ የሚውል ባካና ሆኖ ይታይሃል። ታዝንለታለህ፣ አይይይ ይህ ኃጢአተኛ ሕዝብ ምን ይሻለዋል? ትላለህ።
የእውነተኛ መንፈሳዊ እድገት መገለጫ ግን ይህ አይደለም። ሰው ወደ እግዚአብሔር እየቀረበ ሲመጣ ከሌላው ሰው ይልቅ የራሱ ጉድለት ይታየዋል። መንፈሳዊነት የሚገልጥልህ ሰዎችን ተመልክተህ የምትፈርድበትን ውጫዊ ዓይንህን ሳይሆን ራስህን አይተህ የምትወቅስበት የውስጥ ዓይንህን ነው። መንፈሳዊ ሕይወትህ ሲጎመራ "አይ ሰው" ሳይሆን "አይ እኔ!" ያሰኝሃል። አባ ማቴዎስም እንዲህ ይላል "ሰው የበለጠ ወደ እግዚአብሔር ሲቀርብ ይበልጥ ኃጢአተኛ መሆኑ እየታየው ይመጣል። ነቢዩ ኢሳይያስ እግዚአብሔርን ካየ በኋላ ከንፈሮቼ የረከሱብኝና የጠፋሁ ሰው ነኝ እንዳለ።"
ከብቃት ደርሰህ መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ቢታዩህ እንኳን ሁሉ እንዳንተ ስለሚመስልህ እንደ ዮሐንስ ሐጺር "ሚካኤል ይበልጣል ወይስ ገብርኤል?" እያልህ ከአጠገብህ የቆመውን ትጠይቃለህ እንጂ "አይይ አንተ እንኳን ገና አልበቃህም። ብዙ ይቀርሃል" ብለህ ወዳጅህን አታናንቅም። ይልቅ "ለእኔ ብቻ ገልጦ ለሌላው እንዲሰውር የሚያደርገው ምንም ቁም ነገር የለኝም" በማለት ከወንድምህ የተሻልህ እንዳልሆንክ በፍጹም ልብህ ታምናለህ።
ለመንፈሳዊ ሕይወት አዲስ ስትሆን ገና ጥቂት ጸልየህ፣ ጥቂት ጾመህ፣ ጥቂት መጽውተህ ሳለ ግን ሩጫህን ወደ መጨረሱ የተቃረብህ ይመስልሃል። ጉዞህን በግማሽ እርምጃ ከመጀመርህ ከፍጻሜው ላይ የደረስህ ያህል ይሰማሃል። "እኔን ምሰሉ" ማለት ያምርሃል። ነገር ግን መንፈሳዊ ሕይወት የቱንም ያህል ብትሮጥበት ሁል ጊዜ እንደ ጀማሪ የሚያደርግ ረጅም ጎዳና ነው። ሰማንያ ዓመት በገዳም ሲጋደል የነበረው አባ ሲሶይ ነፍሱ ከሥጋው ልትለይ በቀረበች ጊዜ ብዙ መነኮሳት በአልጋው ዙሪያ ከበውት ሳለ ቅዱሱ "አምላኬ ሆይ፣ እባክህ ለንስሐ የሚሆን ጥቂት ጊዜን ስጠኝ?" እያለ በልቅሶ ሲማጸን ሰሙት። በዚህ የተገረሙት መነኮሳቱ አባ ሲሶይን "አባታችን አንተ እድሜ ልክህን በንስሐ የኖርህ መምህረ ንስሐ ሆነህ ሳለ እንዴት አሁን ጥቂት የንስሐ ጊዜን ትለምናለህ?" ቢሉት፣ ቅዱሱም "ልጆቼ ይህን መንፈሳዊ ጥበብ (ንስሐን) ገና አሁን መጀመሬ ነው" አላቸው።
ጌታ ሆይ መንፈሳዊ ሕይወት እኖር ዘንድ አስጀምረኝ፤ ገና ጀማሪ ሳለሁ ደርሻለሁ ከማለትም ሰውረኝ። እንድቆም አትፍቀድልኝ፤ ወደ አንተ ሳበኝ፣ አሳድገኝ።
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
3.0K views£itsum, 19:41
2023-06-06 08:55:00
➦ የሰኔ ጾም የቄሶች ጾም ነውን
➦ የ2014 ፆመ ሐዋርያት(የሰኔ ፆም) መቼይገባል
➦ ለምንስ ይፆማል
➦ የሰኔ ፆም የሚጾምበት ጊዜያት
➦ ፆመ ሐዋርያት ለምን የቄሶች ፆም በመባል ይጠራል
➦ በሰኔ ፆም ሐዋርያት ሲፆሙ ይጠቀሙበት የነበረው ህግ ምን ነበረ
➦ ፆመ ድኅነት ከትንሳኤ እስከ ጰራቅሊጦስ ለምን አይጾምም ......ሙሉውን መልስ ለማግኘት
አስገራሚ ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፎችን ፣ ምክረ አበው ፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን የምትማሩበት በአንድ ዓመት ብቻ ከ62,000 ተማሪዎችን ያፈራውን ቻናል ለመቀላቀል!!
https://t.me/+7Itsth8QSrY2Y2Q0
https://t.me/+7Itsth8QSrY2Y2Q0
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር
ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ በPDF
ኦርቶዶክሳዊ ግጥም
የግእዝ ትምህርት
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘
3.2K viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 05:55
2023-06-05 18:08:18
#መልካም ዜና
የቤተ ክርስቲያን እውነተኛ አባት የሆኑት ግፈኛው ግዞተኛ መ/ር ኃይለ ማርያም በ20 ሺ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ በዛሬው እለት ውሳኔ አስተላልፏል።
3.5K views£itsum, edited 15:08
2023-06-05 12:54:09
#ጾመ ሐዋርያት
#በወርኃ ሰኔ የሚጾም በመሆኑ ይህ ጾም በተለምዶ የሰኔ ጾም በመባል ይታወቃል፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡ ጾመ ሐዋርያትን ለመጀመሪያ ጊዜ የጾሙት ቅዱሳን ሐዋርያት ሲሆኑ የጾሙበትም ዋና ምክንያት በሃምሳኛው ቀን ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ስለተቀበሉና እግዚአብሔር ስላደረገላቸው መልካም ነገር ለማዘከር ነው፡፡
ጾመ ሐዋርያት በዓለ ጰራቅሊጦስ በመጀመሪያው ሰኞ ይውላል፡፡ ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ደቀ መዛሙርቱን ይህን ጾም እንደሚጾሙት እንዲህ ተናግሮ ነበር፡፡ ‹‹በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። ‹‹እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ እንጾማለን፥ ደቀ መዛሙርትህስ ለምን አይጾሙም? አሉት፡፡›› (ማቴ.፱፥፲፬) ደቀ መዛሙርቱ ይህንን በጠየቁት ጊዜ ጌታችን እንዲህ ብሎ መልሶላቸው ነበር፡፡ ‹‹ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ የሙሽራው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ አይችሉም፤ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ ያንጊዜም ይጾማሉ፡፡›› (ማቴ.፱፥፲፭)
በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ ያደረው ጸጋ መንፈስ ቅዱስና ሀብተ መንፈስ ቅዱስ በእኛም ላይ እንዲያድር፣ ከቅዱሳን ሐዋርያቱ በረከት እንድንሳተፍ፣ አገልግሎታችን በስኬት እንዲቃና እና ወርኃ ክረምቱ በሰላም ያልፍልን ዘንድ ጾመ ሐዋርያትን መጾም አስፈላጊ ነው፡፡ ከጸሎትና ምጽዋትን መንፈሳዊ እድገትን በጾም አስምረን ከራሳችንን እና ከእግዚአብሔር አምላካችን ጋር የምንታረቅበት እንዲሆንልን የቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት በረከትና ጸሎትም አይለየን፡፡
የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነት፣ የቅድስት ድንግል ማርያም እና የቅዱሳን ሐዋርያት አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ አሜን!
#ከማሕበር ቅዱሳን ቴሌግራም የተወሰደ!!
4.2K views£itsum, 09:54
2023-06-04 17:17:14
3.7K views£itsum, 14:17
2023-06-04 17:04:00
የቦሩ ሜዳ ደብረ ብርሃን ሥላሴ እና የደብረ ታቦር ደ/ልዑላን መድኃኔ ዓለም ጉባኤ ቤቶች 49 ደቀ መዛሙርቶቻቸውን አስመረቁ።
ቦሩ ሜዳ ደብረ ብርሃን ሥላሴ 27 ማለትም 10 የብሉይ ኪዳን፣ 17 ሐዲስ ኪዳን መምህራን ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፣ ሊቀጳጳስ እና የሀገረ ስብከቱ ልዩ ልዩ የመምሪያ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ደብረ ታቦር ደ/ልዑላን መድኃኔ ዓለም የካቲት 25/2011 ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተማራቸውን 22 መምህራንን ብፁዕ አቡነ ሚካኤል የደ/ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት አስመርቋል።
በትናንትናው ዕለትም ተመራቂዎቸ ለመመረቂያ ሃይማኖታዊ ፍልስፍና እና ውዳሴ ማርያም በመጽሐፍ ቅዱስ የሚሉ ጥናታዊ ጽሑፎች አቅርበዋል።
የደብረ ታቦር ጉባኤ ቤት ጉባኤውን ለማስፋፋትና ለማጠናከር ኘሮጀክት ቀርጾ እየሠራ በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽዖ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።።
3.5K views£itsum, 14:04
2023-06-04 14:58:29
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ አሁንም ግፍን እያወገዙ ነው።
ቅዱስነታቸው በተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች አቡዳቢ ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም የመቃረቢያ ቤተ ክርስቲያን የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ በአስተላለፋት አባታዊ መልእክት ላይ እንዲህ ብለዋል።
". . . [ልጆቻችን] እናት ዕድለኞች ናችሁ። ለዚህም እግዚአብሔርን ልታመሰግኑ ይገባል። [ይህ] አሁን በሀገራችን ካለው የተለየ ነው። በሀገራችን ያሉት [ልጆቻችን] ይህን ዕድል አላገኙም። [እነርሱ] ዜግነታቸው፣ መብታቸውና ንብረታቸው ሁሉ ተወስዷል። የማይገባ ሥራ እየተሠራ ነው። ተገቢም ያልሆነ ነገር እየተሠራ ነው። የሰው ሀገር መቶ ፕርሰንት ይመቻል ባይባልም፤ እናተ ግን በሰው ሀገር በጃችሁም አልበጃችሁም ቢያንስ በሰላም ትኖራላችሁ ። ይህ ልዮነት የለውም ? እኛ እንኳን በሀገራችን ሁሉ ተውስዶብናል። መብቱ፣ ዜግነቱ፣ ሀብቱ፣ ንብረቱ ሁሉ ተወስዷል። ለምን ቢባል ማነው ተጠያቂው ? ማን ጠያቂ፤ ማን ተጠያቂ ይሆናል። በጭራሽ የሚቻል አልሆነም። . . . "
ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም
በተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች አቡዳቢ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን
ዲያቆን ታደሰ ወርቁ
3.0K views£itsum, edited 11:58
2023-06-04 01:13:15
እውነትም ድንቅ ልጅ "የቀደሙ አባቶች እጃቸው ታስረው ነበረ የሚሾሙት...ዘንድሮ ግን!
ኮሜዲያን እሸቱን ጭንቅላቱን ያስያዘው ድንቅ ኦርቶዶክሳዊ ልጅ
ግቡና እዩት SUBSCRIBE LIKE SHARE እንዳይረሳ የተዋህዶ ልጆች
2.3K viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 22:13
2023-06-03 13:16:53
“የሐሰት ምስክሮችና ዓመፀኞች ተነሥተውብኛልና ለጠላቶቼ ፈቃድ አትስጠኝ።”
— መዝሙር 27፥12
Facebooke link
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.keb
3.0K views£itsum, edited 10:16