2023-05-15 20:29:06
ጥፋቱ የማን ነው?
(መምህር ገብረ መድኅን እንደጻፉት
ከየንታ ገብረ መድኅን)
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የጠራ ትምህርት የታወቀ ሥራዓት ያላት በምድር ያለች ሰማያዊት ዓለም ናት።
ዘመን በወለደው ንጉሥ በወደደው መሄድ አትችልም፦ከአባቶቿ በተቀበለችው እውነት ጸንታ ትኖራለች እንጂ።
የማይናወጽ ዶግማ ፣ዶግማዊ ቀኖና፣ይትበሀል ሥርዓት፣ቅዱስ ትውፊት ያላት እንደመሆኗ መጠን ተመቸኝ ብለን የምንለውጠው አይደለም። ይልቁንም ፦ከትናንት ተቀብለን የምንጠብቀው ለመጻኢው ትውልድም የምናስረክበው ነው እንጂ።
ሐዋርያት የሠሩትን ሠለስቱ ምእት የወሰኑትን አፍርሼ የአበውን ሃይማኖት ይጃለሁ ማለት አይቻልሞ።
ምን አልባት እግዚአብሔር በቸርነቱ ከቅዱሳኑ ማኅበር ቢያደርሰን አባቶቻችንም ለምን የሠራነውን አፈረሻችሁ ብለው ቢጠይቁን መልስ እናገኝ ይሆን? ልጆቻቸው እኛ በስንፍናችን ማፈር አንፈልግም።
ቤተ ክርስቲያን ርትዕት የምትባለውም ባልተቋረጠ ርቱዕ ቅብብሎሽ የመጣች ሐዋርያዊት ስለሆነች ነው።
የሐዲስ ኪዳን ነቅዕ ተቀባዮች ሐዋርያት እና ሐዋርያትን የመሰሉ አበው በውግዘት የሠሩትን ሥርዓት ማስጠበቅ ካንድ ኦርቶዶክሳዊ ሰው የግድ የሚጠበቅ ነው።
ቅዱስ ሲኖዶስም ይሄንን
የመቀበል፣የመጠበቅ፣ለሚመጣው ቅዱስ ጉባኤ የማስረከብ ሀለፊነት አለበት።ይሄንን የሚጋፋ ሲመጣም በጥብዓት አርዓያ በመሆን ምሥክርነትን ሊቀበል ይገባዋል።
አማኞችም ከላይ ከቅዱሳን የወረደውን ፦መቀበል፣መጠበቅ፣መስጠት ይኖርባቸዋል።የጉባኤው አካል ናቸውና በኦርቶዶክሳዊ ሐዋርያዊ ቅብብሎስ ቀኖና የማያገባቸው ምእመናን የሉም።
አንሳሳትም እኛን ብቻ ስሙን የሚባል ከሆነ ስፍር ቁጥር የሌለው ይሄ ሁሉ ስህተት ከየት መጣ?
ያለግዘት በተሠሩ ቀኖናዎች ላይ ግን ቅዱስ ሲኖዶስ የመቀበል ብቻ ሳይሆን የማሻሻልም ሥልጣንም አለው ይሄ ማለትም ሐዋርያት ይለይ ይወገዝ ብለው የሠሩትን ያሻሽላል ማለት አይደለም።
በዚህ ዓመት የገጠመን ግን ሐዋርያት እና ሦስቱ ዓለም አቀፍ ጉባኤ አውግዞ የሰጠንን አትቀበሉ የተባልነውን ከሐዋርያት ይልቅ ጠቅላዩ ያሉት ይበልጣልና ይሁን ተቀበሉ የሚል ስለሆነ በተቃውሞ ላይ እንገኛለን።
በራሳቸው ተሹመናል ብለው ከነበሩት አንድ ሰው እንኳን ወደዚህ ቅዱስ ጉባኤ መግባት አይችልም። ቢገባ ግን ከሐዋርያት እና ከቅዱሳን ሊቃውንት አባቶቻችን ጉባኤ መለየታችን እንደሆነ መታወቅ አለበት።
ዘመን ተመችቶናል በማለት ሞትም ሕይወትም እጃችን ላይ ነው ፣እረፉ በማለት በማስፈራራት ዝም በሉ የሚሉን ግን ፦ለእናንተው ይብሳል እንጂ ለእኛ የአባቶቻችን ውጉዝ ቀኖና ፈርሶ ከምናይ ሰማዕትነትን በናፍቆት እንጠብቃለን።
ይሄንን ነውር ካልተቃወምን ምኑን መምህር ሆንነው? ምኑንስ አስተማርነው?
ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ተዋርዳ ከማየት ሺህ ጊዜ መሞት ሺህ ጊዜ መታሠር ይሻለናል።
መምህሬ ኃይለ ማርያም የታሠሩትም ይሄንን ስላሉ ነው
#ለመሆኑ ጥፋቱ ማን ነው?
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
Facebook Link follow ያድርጉ
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.keb
2.0K views£itsum, edited 17:29