Get Mystery Box with random crypto!

_የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፩_ ሲኖዶስ የግሪክ ቋንቋ ሲሆን ትርጉሙ ጉባኤ፣ ሸንጎ፣ የጳጳሳትና የሊ | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

_የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፩_
ሲኖዶስ የግሪክ ቋንቋ ሲሆን ትርጉሙ ጉባኤ፣ ሸንጎ፣ የጳጳሳትና የሊቃውንት ማኅበር ማለት ነው።
፩) የሐዋርያት ሲኖዶስ የሚባሉት አራት መጻሕፍት ናቸው። እነዚህም:-
√ ግጽው (ረስጠጅ)
√ ትእዛዝ (ረስጠብ)
√ ሥርዓተ ጽዮን (ዓይን)
√ አብጥሊስ (ረስጣ/ረስጠአ)
ናቸው። የሲኖዶስ ውሳኔ የቤተክርስቲያኗ ሕግ እና ሥርዓት ሆኖ ይሠራል።
π
፪) በቤተክርስቲያን ታሪክ እንደሚታወቀው ኤጲስ ቆጶስ ድንግል መሆን እንዳለበት የተወሰነው በአልቪራ ጉባኤ ስፔን በ305/6 ዓ. ም ነው። በኋላ በኒቅያው ጉባኤ ቀርቦም ጸድቋል።
π
፫) የኒቅያ ጉባኤ አርዮስን ካወገዘ በኋላ ሌሎች የሥርዓት ጉዳዮችንም ወስኗል።
π
፬) አንዳንድ ሲኖዶሶች ወቅትንና አካባቢን መሠረት አድርገው የተደነገጉ ናቸው።
π
#ግጽው #ሲኖዶስ
ቁጥር ፲፭:- በቅዱስ ጴጥሮስ ጸሎትና ልመና እግዚአብሔር ጠንቋዩን ሲሞንን አጠፋው።
√√√
ትእዛዝ ፩:- ጸሎታችን ወደ ምሥራቅ ይሁን። ምጽአቱ ከምሥራቅ እንደሚሆን በዚህ አወቅን።
√√√
ሰንበት በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል የቃል ኪዳን ምልክት ነው።
√√√
ትእዛዝ ፪:- ለጸሎት፣ መጻሕፍትን ለማንበብና ቁርባን ለማቅረብ በየእሑዱ በሦስት ሰዓት ይሰብሰቡ። በዚህች ቀን መልአኩ ክርስቶስን እንደምትፀንስ ለማርያም አብሥሯታልና። ጌታ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶበታልና።
√√√
ትእዛዝ ፫:- በዕለተ ረቡዕ ተሰብስበው ጸሎት ያድርጉባት። በዚህች ቀን አይሁድ ይዘው እንደሚሰቅሉትና እና በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ ነግሯቸዋልና። በዚህም ቀን አዝነዋል ተክዘዋልና።
√√√
ትእዛዝ ፬:- በዕለተ ዓርብ በዘጠኝ ሰዓት ተሰብስበው ጸሎት ያድርጉ። ክርስቶስ መከራ ተቀብሎበታልና።
√√√
ትእዛዝ ፭-፮:- ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳት፣ ኤጲስ ቆጶሳት ለምእመናን ሊቃውንትን ይሹሙላቸው። ቀሳውስትን፣ ዲያቆናትን፣ ንፍቅ ዲያቆናትን፣ አናጉንስጢሶችን ይሹሙላቸው።
√√√
ትእዛዝ ፰:- የጌታችንን የልደት በዓል በተወለደባት ቀን ታኅሣሥ ፳፱ን አክብሩ። እስመ ውእቱ ርእሰ ኵሉ በዓላት።
√√√
ትእዛዝ ፱:- የጌታችንን የጥምቀት በዓል ጥር 11 ቀን ያድርጉ። የምስጋና ቀን ናትና።
√√√
ትእዛዝ ፲:- በየዓመቱ ፵ ቀን ይጹሙ። የክርስቶስን ሕማሙን፣ ስቅለቱን፣ ሞቱንና ወደ መቃብር መውረዱን ያስቡ። በትንሣኤው ቀንም ፋሲካን ያድርጉ። ከሰንበታት በስተቀር ቅዳሜና ዓርብን ጨምሮ ፵ ቀን ጾመው ሲጨርሱ በዓል ያድርጉ። እሑድ ትንሣኤው ነው። ከእነዚህ ቀናት በኋላ እስከ ኃምሳኛው ቀን መጨረሻ ድረስ ጾም የለም።
√√√
ትእዛዝ ፲፩:- ከትንሣኤው በኋላ በ፵ኛው ቀን ጌታችን ወደ ሰማይ ያረገበትን በዓል አክብሩ።
√√√
ትእዛዝ ፲፪:- ከኦሪት ከነቢያት መጻሕፍት ሁሉ እና የሐዋርያትን ዜና በቤተክርስቲያን በታላቅ አትሮንስ ላይ ያንብቡ። ከዚያ በኋላም የመጻሕፍት ሁሉ ፍጻሜ ነውና ከወንጌል ያንብቡ። ሕዝቡም ሁሉ በእግሩ ቆሞ ይስማ። የሕይወትና የመድኃኒት የምሥራች ነውና።
√√√
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፪ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው