Get Mystery Box with random crypto!

በትረማርያም አበባው

የቴሌግራም ቻናል አርማ betremariyamabebaw — በትረማርያም አበባው
የቴሌግራም ቻናል አርማ betremariyamabebaw — በትረማርያም አበባው
የሰርጥ አድራሻ: @betremariyamabebaw
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.25K
የሰርጥ መግለጫ

አቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-24 16:51:27 _የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፲_
#አብጥሊስ
አብጥሊስ ፵፪:- ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ከአበደረው ዘንድ ወለድ ቢፈልግ ከመዓርጉ ይሻር።

አብጥሊስ ፶፪:- ከካህናት ወይም ከሕዝባውያን መካከል በሰው ላይ የተሳለቀ ወይም የሳቀ ቢኖር ይሻር። ከአጋጠመው ችግር ተነሥተህ ማንንም አትሳደብ።

አብጥሊስ ፶፭:- ኤጲስ ቆጶስ ወይም አገርን የሚያስተዳድር ከካህናት የተቸገረን ሰው በድብቅ ዐይቶ ለችግሩ የሚፈልገውን ባይሰጠው ችግሩንም ባይቀርፍለት ይሻር።

አብጥሊስ ፶፯:- ከምእመናን መካከል ዝሙት በማብዛት የወደቀ ካለ ይህም የዘወትር ልማድ ቢሆነው ወይም ግብረ ሰዶም የሚፈጽም ሰው ቢኖር ስለ ነፍሱና ስለ ንስሓው ልቅሶ ያብዛ። ከክህነት መዓርግ በየትኛውም አይሾም።

አብጥሊስ ፷፬:- በመዓርጉ ከመሾሙ በፊት ሁለት ያገባ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ቢኖር ይሻር። የሾመውም ይሻር። የሾመው ኤጲስ ቆጶስ ለሹመት ያበቃው ግብሩን ሳያውቅ ከሆነ ግን የተሾመው ብቻ ይሻር።

አብጥሊስ ፷፮:- ከካህናት ወይም ከሕዝባውያን ከአይሁድ ጋር ጾማቸውን የሚጾም ፋሲካንም ከእነርሱ ጋር የሚያደርግ ወይም ከበዓላቸው ስጦታ ወይም ቂጣና የመሳሰለውን የተቀበለ ካህን ቢኖር ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነ ከቤተክርስቲያን ይሰናበት።

አብጥሊስ ፷፰:- የቤተክርስቲያን የሆነ ንዋየ ቅድሳት ወይም የብር ዕቃ ማንም ወደቤቱ ወስዶ ሊጠቀምበት አይገባም።

አብጥሊስ ፸፪:- ሐሜት፣ ስድብ፣ ሽንገላ፣ መሳለቅ፣ የሰውን ስም ማጥፋት፣ ለራሳቸው በእነርሱ ዘንድ የሌለውን መልካም ዜና አግዝፎ መናገር ይህ ሁሉ እግዚአብሔርን የመሳደብ ምሳሌ ነው።

አብጥሊስ ፸፮:- ኤጲስ ቆጶስ ከመኳንንት ሥራ በምን ላይ አይሾም። ለሁለት ጌታ መገዛት የሚችል የለምና።

አብጥሊስ ፹:- ምእመናን እነዚህን (ቀጥለው ያሉትን) መጻሕፍት ይጠብቁ። ቁጥራቸውም 81 ነው።
፩ ኦሪት ዘፍጥረት
፪ ኦሪት ዘጸአት
፫ ኦሪት ዘኍልቍ
፬ ኦሪት ዘሌዋውያን
፭ ኦሪት ዘዳግም
፮ መጽሐፈ ኢያሱ
፯ መጽሐፈ ሩት
፰ መጽሐፈ ነገሥት (፬ቱ)
፱ መጽሐፈ ዕዝራ (፪ቱ)
፲ ትንቢተ ሶፎንያስ
፲፩ ትንቢተ ሚልክያስ
፲፪ ትንቢተ ሚኪያስ
፲፫ ትንቢተ ኢዩኤል
፲፬ መጽሐፈ መክብብ
፲፭ መጽሐፈ ኢዮብ
፲፮ መዝሙረ ዳዊት
፲፯ መጽሐፈ ምሳሌ
፲፰ መኃልየ መኃልይ
፲፱ ትንቢተ ዕንባቆም
፳ ትንቢተ ሆሴዕ
፳፩ ትንቢተ ዘካርያስ
፳፪ ትንቢተ ኢሳይያስ
፳፫ ትንቢተ ኤርምያስ
፳፬ ትንቢተ ሕዝቅኤል
፳፭ ትንቢተ ዳንኤል
፳፮ መጽሐፈ ጥበብ
፳፯ መጽሐፈ ዮዲት
፳፰ መጽሐፈ ሲራክ
፳፱ መጽሐፈ ኩፋሌ
፴ የማቴዎስ ወንጌል
፴፩ የማርቆስ ወንጌል
፴፪ የሉቃስ ወንጌል
፴፫ የዮሐንስ ወንጌል
፴፬ የሐዋርያት ሥራ
፴፭ የጴጥሮስ መልእክታት (፪)
፴፮ የዮሐንስ መልእክታት (፫)
፴፯ የያዕቆብ መልእክት
፴፰ የይሁዳ መልእክት
፴፱ የጳውሎስ መልእክታት (፲፬)
፵ ራእየ ዮሐንስ
፵፩ የቀሌምንጦስ መጻሕፍት
አብጥሊስ ፹፩:- ቅዱሳት መጻሕፍትን ከጠበቃችኋቸው ድኅነት ታገኙባቸዋላችሁ። በመካከላችሁ ሰላምና አንድነት ይሆናል። ባትጠብቋቸው ግን ይፈረድባችኋል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
መ/ር በትረማርያም አበባው
2.2K views13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 10:31:10 _የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፱__
#አብጥሊስ
አብጥሊስ ፪:- ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ ሊሾም የቀረበ ሰው ካለ ይህ በሀገረ ስብከቱ ሰዎች ሁሉ ስምምነት መሆን አለበት።

አብጥሊስ ፫:- ቤተክርስቲያን ውስጥ ከሚያበሩት መብራት፣ ከቅብዐ ሜሮን፣ ከቅብዐት፣ ከዕጣን፣ ከመልካም ሽቱ በስተቀር ምንም ነገር አያስገቡ።

አብጥሊስ ፮:- ቤተክርስቲያንን ለማገልገል የተመደቡ ኤጲስ ቆጶሳት ወይም ቀሳውስት ወይም ዲያቆናት በዚህ ዓለም ተግባር ላይ መሰማራት አይገባቸውም። እንደዚህ ቢያደርጉም ከቤተክርስቲያን ሀብት ይመገቡ እንጂ የትም አይጣሉ።

አብጥሊስ ፱:- በቅዳሴ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን የገባና ቁርባን ያልተቀበለ ከቤተክርስቲያን ይውጣ።

አብጥሊስ ፲:- ከተወገዘ ካህን ጋር የተነጋገረ በድብቅም ከካህናት ጋር ሲጸልይ ያልከለከለ ሰው ቢኖር ከክህነት ይሻር። ከቁርባንም ይከልከል።

አብጥሊስ ፳፩:- በሰዎች ሳይገደድ ራሱን በፍላጎቱ የሰለበ ሰው ክህነት መሾም የለበትም። ራሱን በመግደሉ የራሱ ጠላት ነውና። የእግዚአብሔርንም ፍጥረት የጠላ ነውና።

አብጥሊስ ፳፫:- ራሱን የሰለበ ምእመን ቢኖር ከቤተክርስቲያን ሦስት ዓመት ይሰናበት።

አብጥሊስ ፳፭:- ወደ ቤተክርስቲያን የገባና ክህነትን በእውነት የተቀበለ ሰው ቢኖር ማግባት ቢፈልግ እንዲያገባ እናዛለን።

አብጥሊስ ፳፯:- ባደረገው በደል ከቤተክርስቲያን ያስወጡት ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ወይም ከእርሱ የሚበልጥ ክህነቱን ያሰረበት ካህን ቢኖርና ያደረገው በደል ባያሳዝነው በግድም ያለ ፍርሃት የቤተክርስቲያን አገልግሎት ቢፈጽም ሊፈራቅ ይገባው የነበረው ያ በደልም ባይደንቀው እስከመጨረሻው ከቤተክርስቲያን ይሰናበት።

አብጥሊስ ፴፪:- እንግዳ ሆነው ከሩቅ ሀገር የመጡ ቀሳውስትና ዲያቆናትን ኤጲስ ቆጶስ አይቀበል። የክህነት ሥራንም አይሥሩ። የክህነት ሥራ እንዲሠሩ ደብዳቤ ካላቸው ግን ሥልጣን አላቸው። ደብዳቤ ቢኖራቸውም ምግባራቸውን ይጠይቁ።

አብጥሊስ ፴፫:- ኤጲስ ቆጶስ የሊቃውንት ክብር የሚያውቅ ይሁን። የተሾመላቸው የአገሩ ሰዎች ሁሉ የሚፈልጉትን ያድርግ እንጂ።

አብጥሊስ ፴፭:- ኤጲስ ቆጶስ ሕዝብን ማስተዳደር ባይችል ይህን እስከሚያሻሽል ድረስ ከእነርሱ ይሻር።

አብጥሊስ ፵፩:- የከሓድያንን ጥምቀት የተጠመቀ ወይም ከቁርባናቸው የቆረበ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ቢኖሩ ከሹመታቸው ይሻሩ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፲ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
625 views07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 10:27:18 _የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፰_
#ሥርዓተ #ጽዮን
ቁጥር ፴፮) የኤጲስ ቆጶሳት ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜ ትደረግ። አንደኛው በአራተኛው የጰንጠቆስጤ ሳምንት ይደረግ። ሁለተኛው በጥቅምት ፲፪ ቀን ይደረግ።
~
ቁጥር ፴፰) ቀሳውስትና ዲያቆናት ከኤጲስ ቆጶስ ምክር ውጭ ምንም አያድርጉ።
~
ቁጥር ፴፱) ኤጲስ ቆጶስ ሀብት ካለው የእርሱ ለብቻ የታወቀ ይሁን። የቤተክርስቲያን ተለይቶ የታወቀ ይሁን።
~
ቁጥር ፵) ኤጲስ ቆጶስ በቤተክርስቲያን ሀብት ላይ ሥልጣን ያገኝ ዘንድ እናዛለን።
~
ቁጥር ፵፩) በዘፈንና በስካር ላይ የሚገኝ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ይተው። አለበለዚያ ይሻር።
~
ቁጥር ፵፭) ካህን ከከሓድያን ጥምቀት ቢቀበል ወይም መሥዋዕትን ቢቀበል ይሻር ዘንድ እናዛለን።
~
ቁጥር ፶) መንገድ ሲሔድ ደክሞት ለማረፍ ብሎ ካልሆነ በስተቀር ሹም ሆኖ በጠጅ ቤት የሚበላ ቢኖር ይታገድ።

ቁጥር ፶፰) ከኃድያንን በመፍራት የክርስቶስን ስም የካደ ይባረር። ከሹመቱ ስምም ይሻር።

ቁጥር ፶፱) ለአምልኮ ባዕድ የተሠዋውን የሚበላ፣ ወይም ነፍስ ያልተለየውን ሥጋ የሚበላ ወይም በአውሬ ተነክሶ የሞተን የሚበላ ወይም በክት የሚበላ ካህን ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነም ይታገድ።

ቁጥር ፷፩) ከከኃድያን ጋር ቤተ ጸሎት ገብቶ የሚጸልይ ተሿሚ ቢኖር ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነም ይታገድ።

ቁጥር ፷፭) ደዌ ሥጋ ካልከለከለው በስተቀር የተቀደሰችውን የፋሲካን ጾም ረቡዕና ዓርብን የማይጾም ካህን ቢኖር ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነም ይታገድ።

ቁጥር ፷፮) ከአይሁድ ጋር የሚጾም ወይም ከእነርሱ ጋር በዓላቸውን የሚያከብር ወይም ከበዓላቸው ቂጣም ሆነ ወይም ሌላ የሚመስለውን ስጦታ የሚቀበል ኤጲስ ቆጶስ ወይም ሌላ ሹም ቢኖር ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነም ይታገድ።

ቁጥር ፹፩) መጻሕፍት አምላካውያት
፩) ኦሪት ዘፍጥረት
፪) ኦሪት ዘጸአት
፫) ኦሪት ዘሌዋውያን
፬) ኦሪት ዘኍልቍ
፭) ኦሪት ዘዳግም
፮) መጽሐፈ ኢያሱ
፯) መጽሐፈ መሳፍንት
፰) መጽሐፈ ሩት
፱) መጽሐፈ ነገሥት (፬ቱ)
፲) ሕጹጻን (፪ቱ)
፲፩) ዕዝራ (፫ቱ)
፲፪) መዝሙረ ዳዊት
፲፫) መጽሐፈ ምሳሌ
፲፬) መጽሐፈ መክብብ
፲፭) መኃልየ መኃልይ
፲፮) መጽሐፈ ኢዮብ
፲፯) ንኡሳን ነቢያት (፲፪ቱ)
፲፰) ትንቢተ ኢሳይያስ
፲፱) ትንቢተ ኤርምያስ
፳) ትንቢተ ሕዝቅኤል
፳፩) ትንቢተ ዳንኤል
፳፪) ወንጌል (፬ቱ)
፳፫) የሐዋርያት ሥራ
፳፬) የጳውሎስ መልእክት (፲፬ቱ)
፳፭) መልእክታተ ሐዋርያት (፯ቱ)
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፱ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
553 views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 10:26:04 _የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፰_
#ሥርዓተ #ጽዮን
ቁጥር ፴፮) የኤጲስ ቆጶሳት ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜ ትደረግ። አንደኛው በአራተኛው የጰንጠቆስጤ ሳምንት ይደረግ። ሁለተኛው በጥቅምት ፲፪ ቀን ይደረግ።
~
ቁጥር ፴፰) ቀሳውስትና ዲያቆናት ከኤጲስ ቆጶስ ምክር ውጭ ምንም አያድርጉ።
~
ቁጥር ፴፱) ኤጲስ ቆጶስ ሀብት ካለው የእርሱ ለብቻ የታወቀ ይሁን። የቤተክርስቲያን ተለይቶ የታወቀ ይሁን።
~
ቁጥር ፵) ኤጲስ ቆጶስ በቤተክርስቲያን ሀብት ላይ ሥልጣን ያገኝ ዘንድ እናዛለን።
~
ቁጥር ፵፩) በዘፈንና በስካር ላይ የሚገኝ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ይተው። አለበለዚያ ይሻር።
~
ቁጥር ፵፭) ካህን ከከሓድያን ጥምቀት ቢቀበል ወይም መሥዋዕትን ቢቀበል ይሻር ዘንድ እናዛለን።
~
ቁጥር ፶) መንገድ ሲሔድ ደክሞት ለማረፍ ብሎ ካልሆነ በስተቀር ሹም ሆኖ በጠጅ ቤት የሚበላ ቢኖር ይታገድ።

ቁጥር ፶፰) ከኃድያንን በመፍራት የክርስቶስን ስም የካደ ይባረር። ከሹመቱ ስምም ይሻር።

ቁጥር ፶፱) ለአምልኮ ባዕድ የተሠዋውን የሚበላ፣ ወይም ነፍስ ያልተለየውን ሥጋ የሚበላ ወይም በአውሬ ተነክሶ የሞተን የሚበላ ወይም በክት የሚበላ ካህን ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነም ይታገድ።

ቁጥር ፷፩) ከከኃድያን ጋር ቤተ ጸሎት ገብቶ የሚጸልይ ተሿሚ ቢኖር ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነም ይታገድ።

ቁጥር ፷፭) ደዌ ሥጋ ካልከለከለው በስተቀር የተቀደሰችውን የፋሲካን ጾም ረቡዕና ዓርብን የማይጾም ካህን ቢኖር ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነም ይታገድ።

ቁጥር ፷፮) ከአይሁድ ጋር የሚጾም ወይም ከእነርሱ ጋር በዓላቸውን የሚያከብር ወይም ከበዓላቸው ቂጣም ሆነ ወይም ሌላ የሚመስለውን ስጦታ የሚቀበል ኤጲስ ቆጶስ ወይም ሌላ ሹም ቢኖር ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነም ይታገድ።

ቁጥር ፹፩) መጻሕፍት አምላካውያት
፩) ኦሪት ዘፍጥረት
፪) ኦሪት ዘጸአት
፫) ኦሪት ዘሌዋውያን
፬) ኦሪት ዘኍልቍ
፭) ኦሪት ዘዳግም
፮) መጽሐፈ ኢያሱ
፯) መጽሐፈ መሳፍንት
፰) መጽሐፈ ሩት
፱) መጽሐፈ ነገሥት (፬ቱ)
፲) ሕጹጻን (፪ቱ)
፲፩) ዕዝራ (፫ቱ)
፲፪) መዝሙረ ዳዊት
፲፫) መጽሐፈ ምሳሌ
፲፬) መጽሐፈ መክብብ
፲፭) መኃልየ መኃልይ
፲፮) መጽሐፈ ኢዮብ
፲፯) ንኡሳን ነቢያት (፲፪ቱ)
፲፰) ትንቢተ ኢሳይያስ
፲፱) ትንቢተ ኤርምያስ
፳) ትንቢተ ሕዝቅኤል
፳፩) ትንቢተ ዳንኤል
፳፪) ወንጌል (፬ቱ)
፳፫) የሐዋርያት ሥራ
፳፬) የጳውሎስ መልእክት (፲፬ቱ)
፳፭) መልእክታተ ሐዋርያት (፯ቱ)
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፱ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
574 views07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 18:17:38 Channel photo updated
15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 18:16:32 Channel photo removed
15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 17:44:33 በቅርብ ሲኖዶስ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳትን እንደሚሾም ሰምተናል። ነገር ግን በመሾም ሂደት ምእመኑም የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን በቀን ብዙ ብዙ ክፍሎችን እንማማራለን። ፍት. ነገ.፭፣ ፴፮ "ኤጲስ ቆጶስ በሚሾምባቸው ሕዝብ ፈቃድና በሊቀ ጳጳሱ ፈቃድ ይሾም" ስለሚል ሕዝቡ ያልፈቀደለት ሰው ጵጵስና መሾም አይችልም። ስለዚህ በጳጳሳት ሹመት ሕዝቡም ድርሻ ስላለው ድርሻውን ሊወጣ ይገባልና። የሥርዓት መጻሕፍቶችን እንማማራለን። በቀን ብዙ ብዙ ክፍል የምለቀው እስከ ሲኖዶስ ስብሰባ የሥርዓት መጻሕፍትን ተማምረን እንድንጨርስ ብየ ነው።
__የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፯__
#ሥርዓተ #ጽዮን
ቁጥር ፩) ኤጲስ ቆጶስ ሁለት ወይም ሦስት ኤጲስ ቆጶሳት ባሉበት እሑድ ቀን ይሾም።
~
ቁጥር ፪) ቄስ ዲያቆንና ሌሎች እሑድ ቀን በአንድ ኤጲስ ቆጶስ ይሾሙ።
~
ቁጥር ፮) ፋሲካን ከአይሁድ ጋር ያደረገ ካህን ይሻር።
~
ቁጥር ፲) በቤት የሚጸልይ ቢኖር ቆሞ ይጸልይ።
~
ቁጥር ፲፰) ሁለት እህትማማቾችን ወይም የወንድሙን ልጅ ወይም የእህቱን ልጅ ያገባ መሾም አይችልም።
~
ቁጥር ፳፬) በዝሙት ወይም በሐሰት በመማል ወይም በሌብነት የተገኘ ካህን ይሻር።
~
ቁጥር ፳፫) ሕዝባዊ ሆኖ ራሱን የሰለበ ለሦስት ክረምቶች ይታገድ ለራሱ ሕይወት ጠላት ነውና።
~
ቁጥር ፳፮) ለመፈራት የሚደባደብ ካህን ይሻር ዘንድ እናዛለን።
~
ቁጥር ፳፯) በታወቀ በደል በትክክል የተሻረ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ቢኖርና ቀድሞ በተሰጠው ሥልጣን ለመሥራት ቢደፋፈር ፈጽሞ እንደዚህም ቢያደርግ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ከቤተክርስቲያን ይሻር።
~
ቁጥር ፳፰) በገንዘብ ሹመት ያገኘ ካህን ይሻር።
~
ቁጥር ፳፱) ቤተክርስቲያን የያዙ የዓለም ሰዎች የሆኑ መኳንንትን የሚያገለግል ኤጲስ ቆጶስ ቢኖር ይሻር። ይታገድም። ከእርሱ ጋር የተባበሩት ሁሉም ይታገዱ።
~
ቁጥር ፴፪) ደብዳቤ ካልያዘ በስተቀር እንግዳ የሆኑ ኤጲስ ቆጶስን ወይም ቄሶችን ወይም ዲያቆናትን አይቀበሉ።
~
ቁጥር ፴፭) የተሾመ ኤጲስ ቆጶስ ቢኖር የተሰጠችውን ሀገረ ስብከት ሕዝብ ልብና እሺ በጎ ብሎ መገዛት ካላገኘ እስቀሚቀበሉት ድረስ ታግዶ ይቆይ።
~
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፰ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
2.0K views14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 17:12:40
"ማስታዎሻ"
ዛሬን የመጻሕፍት ቀን ብለው የሚያከብሩ ሰዎችን አየሁ። መጻሕፍት የሰው ልጅ አእምሮውን የሚያጠራባቸው ሰውን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡ ደጋግ መምህራን ናቸው። መጻሕፍትን ስናነብ ማስታዎሻ መያዝን መልመድ አለብን። ማስታዎሻ መያዝ ያነበብነውን መጽሐፍ ፍሬ ነገሩን ለማስፈር ይረዳል። መጻሕፍትን ሳነብ ከ30 በላይ የማስታዎሻ አጀንዳ ጨርሻለሁ። ሳነብ ማስታዎሻ ካልያዝኩ ያነበብኩ አይመስለኝም። የገዛሁትን መጽሐፍ እንኳ ማስታዎሻ እየያዝኩ ነው የማነበው። ክቡር መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ከመንፈሳዊ መጻሕፍት ባሻገር ዓለማዊ መጻሕፍትን ያነቡ ነበር ይባላል። ማንበብ አእምሮን ስል ያደርጋል።

ሳይንሳዊ መጻሕፍትንም፣ የስነ ልቡና መጻሕፍትንም፣ የፍልስፍና መጻሕፍትንም ማንበብ ለሰው ልጅ አስተሳሰብ ወሳኝ ናቸው። እንደ ግል ማስታዎሻ የምይዝባቸው:-
፩) መንፈሳዊ መጻሕፍት
፪) ዓለማዊ መጻሕፍት
፫) መንፈሳዊ ፊልሞችን ሳይ ጭብጡን
፬) ዓለማዊ ፊልሞችን ሳይ ጭብጡን
፭) ምሁራን ቀርበው በቴሌቭዥን ወይም በሬድዮ ሐሳብ ሲሰጡ፣ ሽማግሌዎች በቀድሞ የነበረ መልካም ገጠመኝ ሲያወሩ ስሰማ እጽፋለሁ። ይህ የእኔ የማስታዎሻ አያያዝ መንገድ ነው። እስኪ የተሻለ የማስታዎሻ አያያዝ ካለ ጠቁሙኝ። ከታች ከፎቶው የምታዩት እስከዛሬ ያነበብኳቸውን መጻሕፍት በኮምፒውተር ጽፌ አዘጋጅቼው ነው። ይህን የሚያህል ሌላም አለ።

ይች ልምድ የምትጠቅመው ካለች ብየ ነው ያከፈልኳት። በእርግጥ ማስታዎሻ የመያዝ ልምድህን ንገረኝ ያላችሁኝም ስለነበራችሁ ለመታዘዝ ያህል ነው።
1.7K views14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 16:08:10 __የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፮__
#ትእዛዝ #ሲኖዶስ
ትእዛዝ ፶፬-፶፭:- ሕዝባውያን ሆይ ቀጥለው ያሉት መጻሕፍት በእናንተ ዘንድ ሁሉም ተቀባይነት ይኑራቸው።
፩) ኦሪት ዘፍጥረት
፪) ኦሪት ዘጸአት
፫) ኦሪት ዘሌዋውያን
፬) ኦሪት ዘኍልቍ
፭) ኦሪት ዘዳግም
፮) መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ
፯) መጽሐፈ መሳፍንት
፰) መጽሐፈ ሩት
፱) አንደኛ ነገሥት (፩ኛ ሳሙኤል)
፲) ሁለተኛ ነገሥት (፪ኛ ሳሙኤል)
፲፩) ሦስተኛ ነገሥት (፩ኛ ነገሥት)
፲፪) አራተኛ ነገሥት (፪ኛ ነገሥት)
፲፫) መጽሐፈ ዕዝራ (፩&፪)
፲፬) መጽሐፈ ኢዮብ
፲፭) መጽሐፈ አስቴር
፲፮) መጽሐፈ ጦቢት
፲፯) መጽሐፈ መክብብ
፲፰) መዝሙረ ዳዊት
፲፱) መጽሐፈ ምሳሌ
፳) መኃልየ መኃልይ
፳፩) ፲፪ቱ ንዑሳን ነቢያት
፳፪) ትንቢተ ኢሳይያስ
፳፫) ትንቢተ ኤርምያስ
፳፬) ትንቢተ ሕዝቅኤል
፳፭) ትንቢተ ዳንኤል
፳፮) መጽሐፈ ጥበብ
፳፯) መጽሐፈ ዮዲት
፳፰) ሦስቱ የኩፋሌ መጻሕፍት
፳፱) መጽሐፈ ሲራክ
፴) የማቴዎስ ወንጌል
፴፩) የማርቆስ ወንጌል
፴፪) የሉቃስ ወንጌል
፴፫) የዮሐንስ ወንጌል
፴፬) የሐዋርያት ሥራ
፴፭) አንደኛ ጴጥሮስ
፴፮) ሁለተኛ ጴጥሮስ
፴፯) አንደኛ ዮሐንስ
፴፰) ሁለተኛ ዮሐንስ
፴፱) ሦስተኛ ዮሐንስ
፵) የያዕቆብ መልእክት
፵፩) መልእክተ ይሁዳ
፵፪) ራእየ ዮሐንስ
፵፫) ፲፬ቱ የጳውሎስ መልእክት
፵፬) ፪ቱ የቀሌምንጦስ መልእክታት
፵፭) ሕጹጻን (፪ቱ)

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።
ክፍል ፯ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
1.6K views13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 12:38:23 የቤተክርስቲያን ያልሆነን ትምህርት የቤተክርስቲያን እያስመሰሉ ማቅረብ ይቅር። ቤተክርስቲያን አስተምህሮዋ ከወርቅ የጠራ ነው። በነቢያት የተነገረ፣ በሐዋርያት የተሰበከ፣ በሊቃውንት የተመሠጠረ ትምህርት አላት። ከዚያ ውጭ የራስን ግላዊ እይታ አስተምህሮዋ አስመስሎ ማቅረብ አይገባም። አርዮስ በመሰለኝ በካደ ጊዜ ሊቃውንቱ "ከመጽሐፍ አላገኘኽው፣ ከመምህር አልተማርከው እባክህ ይቅርብህ። አስብኽው ከሆነ አትናገረው፣ ተናግረኽው ከሆነ አትድገመው" ብለውት ነበር። እርሱ ግን ስላልሰማቸው ራሱን ጎዳ። በክፋት እና በስሕተት ጎዳና ያለ ሰው መጀመሪያ የሚጎዳው ራሱን ነው። በሰው ጭብጫቦ ሰክሮ እውነትን መጨቆን አይገባም። የሰውን ጩኽት ፈርቶም እውነትን መደበቅ አይገባም። ሰው መዋቲ ነው። ፈራሽ በስባሽ የሆነ ሰውን መፍራት አይገባም። ነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ እንኳ ንጉሡ ዖዝያንን ፈርቶ እውነትን ቢሸሻት ለምጻም ሆኗል። በዓመተ ሞተ ዖዝያን ንጉሥ ብሎ ራሱ ያመጣዋል። ያ የምትፈራው የምታፍረው ንጉሥ ሞተ ለማለት። የማይሞተው አምላክን መፍራት እንደሚገባው ለማመልከትም ቀጥሎ ርኢክዎ ለእግዚአብሔር እንዘ ይነብር ዲበ መንበሩ ነዊኅ ብሎ ያመጣዋል።

ሰው ቤተክርስቲያንን ሊከተል ይገባዋል። አስተምህሮዋን መጠንቀቅ ይገባዋል። እውነት በአጨብጫቢ ብዛት አትለካም። የእውነት ልኳ ራሱ ክርስቶስ ነው። በምጽአት ጊዜ ለሁሉ በአደባባይ ትገለጣለች። እስከዚያው ግን ኃጥአን ጻድቃን መስለው ሊኖሩ ይችላሉ። ጻድቃንም ኃጥአን ተብለው ሊኖሩ ይችላሉ። ያች የእውነት ቀን ስትመጣ ሁሉ ይገለጣል። እርሱ ሞቶ እኛን ያዳነን መድኃኔዓለምን እናስበው። ፍቅርን በተግባር አሳየን። እውነት እርሱ ነው። እርሱን እንከተል።
1.8K views09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ