Get Mystery Box with random crypto!

_የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፱__ #አብጥሊስ አብጥሊስ ፪:- ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

_የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፱__
#አብጥሊስ
አብጥሊስ ፪:- ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ ሊሾም የቀረበ ሰው ካለ ይህ በሀገረ ስብከቱ ሰዎች ሁሉ ስምምነት መሆን አለበት።

አብጥሊስ ፫:- ቤተክርስቲያን ውስጥ ከሚያበሩት መብራት፣ ከቅብዐ ሜሮን፣ ከቅብዐት፣ ከዕጣን፣ ከመልካም ሽቱ በስተቀር ምንም ነገር አያስገቡ።

አብጥሊስ ፮:- ቤተክርስቲያንን ለማገልገል የተመደቡ ኤጲስ ቆጶሳት ወይም ቀሳውስት ወይም ዲያቆናት በዚህ ዓለም ተግባር ላይ መሰማራት አይገባቸውም። እንደዚህ ቢያደርጉም ከቤተክርስቲያን ሀብት ይመገቡ እንጂ የትም አይጣሉ።

አብጥሊስ ፱:- በቅዳሴ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን የገባና ቁርባን ያልተቀበለ ከቤተክርስቲያን ይውጣ።

አብጥሊስ ፲:- ከተወገዘ ካህን ጋር የተነጋገረ በድብቅም ከካህናት ጋር ሲጸልይ ያልከለከለ ሰው ቢኖር ከክህነት ይሻር። ከቁርባንም ይከልከል።

አብጥሊስ ፳፩:- በሰዎች ሳይገደድ ራሱን በፍላጎቱ የሰለበ ሰው ክህነት መሾም የለበትም። ራሱን በመግደሉ የራሱ ጠላት ነውና። የእግዚአብሔርንም ፍጥረት የጠላ ነውና።

አብጥሊስ ፳፫:- ራሱን የሰለበ ምእመን ቢኖር ከቤተክርስቲያን ሦስት ዓመት ይሰናበት።

አብጥሊስ ፳፭:- ወደ ቤተክርስቲያን የገባና ክህነትን በእውነት የተቀበለ ሰው ቢኖር ማግባት ቢፈልግ እንዲያገባ እናዛለን።

አብጥሊስ ፳፯:- ባደረገው በደል ከቤተክርስቲያን ያስወጡት ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ወይም ከእርሱ የሚበልጥ ክህነቱን ያሰረበት ካህን ቢኖርና ያደረገው በደል ባያሳዝነው በግድም ያለ ፍርሃት የቤተክርስቲያን አገልግሎት ቢፈጽም ሊፈራቅ ይገባው የነበረው ያ በደልም ባይደንቀው እስከመጨረሻው ከቤተክርስቲያን ይሰናበት።

አብጥሊስ ፴፪:- እንግዳ ሆነው ከሩቅ ሀገር የመጡ ቀሳውስትና ዲያቆናትን ኤጲስ ቆጶስ አይቀበል። የክህነት ሥራንም አይሥሩ። የክህነት ሥራ እንዲሠሩ ደብዳቤ ካላቸው ግን ሥልጣን አላቸው። ደብዳቤ ቢኖራቸውም ምግባራቸውን ይጠይቁ።

አብጥሊስ ፴፫:- ኤጲስ ቆጶስ የሊቃውንት ክብር የሚያውቅ ይሁን። የተሾመላቸው የአገሩ ሰዎች ሁሉ የሚፈልጉትን ያድርግ እንጂ።

አብጥሊስ ፴፭:- ኤጲስ ቆጶስ ሕዝብን ማስተዳደር ባይችል ይህን እስከሚያሻሽል ድረስ ከእነርሱ ይሻር።

አብጥሊስ ፵፩:- የከሓድያንን ጥምቀት የተጠመቀ ወይም ከቁርባናቸው የቆረበ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ቢኖሩ ከሹመታቸው ይሻሩ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፲ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው